Ever Light

Ever Light Updates on different situations You can get what you want,if you put here.

02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት። ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች። ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል። ዛሬ የተደገመውም ይኸው ነው።

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች። ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር።

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል። እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው።

ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም። ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል። ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች።

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣ አዲስአበባ፣ ኢትዮጵያ

 #ተጨባበጡ=========🗳️ ከምርጫ ውጤት በኋላ ዴሞክራሲን ማጽናት የሁላችንም ኃላፊነት ነው!ምርጫ የሚጠናቀቀው በድምጽ አሰጣጥ ብቻ ሳይሆን ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ በሚታየው የፖለቲካ ብስለት...
01/06/2026

#ተጨባበጡ
=========

🗳️ ከምርጫ ውጤት በኋላ ዴሞክራሲን ማጽናት የሁላችንም ኃላፊነት ነው!

ምርጫ የሚጠናቀቀው በድምጽ አሰጣጥ ብቻ ሳይሆን ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ በሚታየው የፖለቲካ ብስለት ነው።

✅ የምርጫ ውጤትን በህግ አግባብ መቀበል
✅ ሰላምና መረጋጋትን ማስቀደም
✅ የጥላቻ ንግግርና ግጭትን ማስወገድ
✅ ለሀገር ጥቅም በጋራ መስራት
✅ የዴሞክራሲ ተቋማትን ማክበር
✅ ግንባታዊ ተቃዋሚነትን ማጠናከር

🇪🇹 ጠንካራ ዴሞክራሲ የሚገነባው በመቻቻል፣ በህግ የበላይነት እና በሰላማዊ የፖለቲካ ባህል ነውና ተጨባበጡ።

#ዴሞክራሲ #ምርጫ #ሰላም

01/06/2026

"ምርጫው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው"
የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ

01/06/2026
01/06/2026

"የሚመጣውን ውጤት ለመቀበል በእኛ በኩል ዝግጁ ነን ፤ ያሸነፉ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ፤የተሸነፉ ውጤቱን በፀጋ እንዲቀበሉ ማሳሰብ እፈልጋለው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)"

 #የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ሊኖራቸው የሚገባ ሚና======================የፀጥታ አካላት በምርጫ ዕለት ዋና ኃላፊነታቸው ሕግና ሥርዓት...
01/06/2026

#የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ሊኖራቸው የሚገባ ሚና
======================
የፀጥታ አካላት በምርጫ ዕለት ዋና ኃላፊነታቸው ሕግና ሥርዓትን ማስከበር፣ የመራጮችን ደህንነት መጠበቅ እና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ከማንኛውም ጫና፣ ረብሻ ወይም ሕገ-ወጥ ተግባር ነፃ ሆኖ እንዲካሄድ ማረጋገጥ ነው።
ዋና ዋና ሚናዎች
ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ
-------------------
በምርጫ ጣቢያዎችና በአካባቢያቸው ሰላምና ሥርዓት እንዲጠበቅ መሥራት።
ረብሻ፣ ግጭት ወይም ሌሎች የፀጥታ ስጋቶችን መከላከል።
የመራጮችን ነፃነት መጠበቅ
-------------------
መራጮች ያለ ፍርሃት፣ ማስፈራራት ወይም ጫና ድምጻቸውን እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
የማስገደድ ወይም የተጽዕኖ ተግባራትን መከላከል።
ሕግና ሥርዓት ማስከበር
-----------------
የምርጫ ሕግን የሚጥሱ ድርጊቶች ሲፈጸሙ በሕግ መሠረት እርምጃ መውሰድ።
የምርጫ ጣቢያዎችን ከሕገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት መጠበቅ።
ፖለቲካዊ ገለልተኝነት መጠበቅ
-------------------
ለማንኛውም ፓርቲ ወይም እጩ አድልዎ ሳያደርጉ በገለልተኛነት መሥራት።
የሕዝብ እምነትን የሚያጎድሉ ተግባራትን ማስወገድ።
ከምርጫ አስፈጻሚ አካላት ጋር መተባበር
ከምርጫ አስፈጻሚዎች ጋር በቅርበት በመስራት የሚፈጠሩ ችግሮችን በፍጥነት መፍታት።
የምርጫ ቁሳቁሶችና ሰነዶች በደህና እንዲጠበቁ ድጋፍ ማድረግ።
መልዕክት
"የፀጥታ አካላት በሙያዊነት፣ በገለልተኝነት እና በሕግ አክባሪነት በመሥራት ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ታማኝ የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።"

01/06/2026

ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ በትውልድ አካባቢያቸውና ዕጩ ሆነው በቀረቡበበት በሻሻ ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሲሰጡ

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

29/05/2026

በጎጃም አንድ ተረት አለ።
ሀብታሙ የሚባል ልጅ ማግባት የለበትም ብለው የሠፈር ጎረምሶች ቡራ ከረዩ አሉ። ሚስቱን እንገላለን፤ ሚዜዎቹን እንመታለን፤ ድግሱን እናበላሻለን፤ ሠርገኛውን እንገርፋለን ብለው አስፈራሩ።

ሀብታሙ ግን ሞያ በልብ ብሎ ሚስቱን አጨ። ድግሡን ደገሠ፤ የሀገር ሽማግሌዎችንና ነፍስ ያላቸውን ሰዎች ጠርቶ አማከረ። እነሱም " ለሀብታሙ ሠርግ ያልመጣ ቡዳ ነው" ብለው አወገዙ። ሰዉም ተጠራርቶ ሠርጉ ላይ መጣ። ጎረምሶቹ እንኳን ሳይቀሩ "ቡዳ" መባል ፈርተው መጡ። መቼስ ሕዝብ ካወገዘው ምን ያደርጋሉ።

በኋላ ጭፈራው ላይ አዝማሪዋ:-

ያም በየ ሠፈሩ ፎከረ አስፎከረ
ያም በየገበያው ፎከረ አስፎከረ
ጮማና ብርንዶው እየተመተረ
እንጀራ እንደ ኩበት እየተከመረ
ድል ባለ ድግስ ሀብታሙ ተዳረ።

ብላ ዘፈነች አሉ።

Daniel Kibret

Words in action
26/05/2026

Words in action

Address

Bole

1000

Telephone

+251924542559

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ever Light posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share