09/10/2025
እስራኤልና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ
++++++++++++
| በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሲደረግ የቆየው ድርድር በስምምነት ተጠናቋል።
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በተካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ሸምጋዮች ሁለቱ ወገኖች በጋዛ ሰርጥ ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሐሙስ ማለዳ ላይ አስታውቀዋል ሲል ሪወተርስ ዘግቧል።
የተኩስ አቁሙ ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን፤ በ72 ሰዓታት ውስጥ የእስረኞች ልውውጥ እንደሚደረግም ታውቋል።
በስምምነቱ የመጀመርያ ምዕራፍ ከሁለቱም ወገን እስረኞች ይለቀቃሉ ሲሉ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ሃማስ በህይወት ያሉ የእስራኤል 20 እስረኞች በአንድ ጊዜ ይፈታሉ፤ በአምስት አቅጣጫ ወደ ጋዛ ሰርጥ ሰብዓዊ እርዳታን የጫኑ መኪኖች መግባት ይጀምራሉ ተብሏል በስምምነቱ ላይ።
ሃማስን ትጥቅ ማስፈታትና የጋዛ ሰርጥን ማን ያስተዳድር የሚለው ጉዳይ ሁለተኛው የድርድር ምዕራፍ ተደርጓል።
ሁለተኛው ምዕራፍ ድርድር ከመጀመርያው አፈፃፀም በኋላ እንደሚቀጥል አል አረቢያ ዘግቧል።
የሐማስ ተጨማሪ የልዑካን ቡድን ማምሻውን በምክትል ዋና ጸሃፊው እየተመራ ግብፅ ገብቷል።
ልዑካኑ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም በሚደረገው ድርድር ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በአረቡ ሙህየ
+++++++++++++++
Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ