ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa

ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!
(1)

ከ‎ጁኦ ስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና በሚል መሪ ቃል የሚሰጠው ስልጠና በሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀን 23/03/2018 በሶስት ቡዱን ተከፋፍሎ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ።‎‎ #...
02/12/2025

ከ‎ጁኦ ስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና በሚል መሪ ቃል የሚሰጠው ስልጠና በሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀን 23/03/2018 በሶስት ቡዱን ተከፋፍሎ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ።

‎ #ሶዶ ከተማ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግኑኝነት

‎በቡድን መሪዋች አማካይነት ውይይቱ በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን የገለፁት የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ
‎ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ናቸው ።

‎ውይይቱ በተከፋፈለው ቡድን መሠረት እንደምቀጥል ኮማንደሩ ገልጸዋል ።

‎@

የወላይታ ሶዶ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ  መምርያ ለፖሊስ አመራሮች እና አባላት "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና እንደ ሀገር ለመገንባት ወጥ የሆነ የጋራ ግንዛቤ በሀገራዊ ቁጭትን ...
01/12/2025

የወላይታ ሶዶ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ መምርያ ለፖሊስ አመራሮች እና አባላት "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና እንደ ሀገር ለመገንባት ወጥ የሆነ የጋራ ግንዛቤ በሀገራዊ ቁጭትን የፈጠረ ነው" በሚል ሀሳብ ስልጠና ማስመጀሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

ወላይታ ሶዶ ከተማ ፤ህዳር 22/2018 ወላይታ ሶዶ ከተማ ለፖሊስ አመራሮች እና አባላት "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ሀሳብ ስልጠና ማስመጀሪያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ክልላዊ፣ ቀጠናዊ፣ አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የፖሊስ አመራሩና አባሉ ራሱን ብቁ በማድረግ ለቀጣይ ምዕራፍ ዝግጁ እንዲሆን የሚያስችል መድረክ ነው።

በለውጡ መንግስት እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ለቀጣይ ተልዕኮ ብቁ ለማድረግና አቅምን ለመገንባት ያለመ ስልጠና መድረክ እንደሆነም ተገልጿል።

ስልጠናው የፖሊስ አባላት ለህሊናቸውና ለሕገ-መንግስቱ የታመኑ፤ በሙያዊ ስነ-ምግባራቸው የታነጹና እና የህብረተሰቡን ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት መፈጸም የሚችሉ ፖሊሶችን ለማብቃት የሚያግዝ ይሆናል።

በስልጠናው መድረክ ምክትል ከንቲባ አቶ መንግስቱ ትግሮ ጨምሮ የክልል የፖሊስ ኮሚሽን አመራር የሰልጠና አሰተባባር ኮማንደር ዘገዬ መኮንን እና ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምርያ አዛዥ ስልጠና እየሰጡ ናቸው።

በአከባቢው ጸጥታ ዙሪያ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት መደረጉን  የድል በጌሬራ  ቀበሌ ፖሊስ አስታወቀ።(ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ህዳር 21/03/2018ዓ.ም )ዎላይታ ሶዶ ከተማ...
30/11/2025

በአከባቢው ጸጥታ ዙሪያ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት መደረጉን የድል በጌሬራ ቀበሌ ፖሊስ አስታወቀ።

(ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ህዳር 21/03/2018ዓ.ም )

ዎላይታ ሶዶ ከተማ የድል በጌሬራ ቀበሌ ፖሊስ በአከባቢው ጸጥታ ዙሪያ ከአከባቢው ሊንታላ ቀጠና ነዋሪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብራሃም ባሣገልጸዋል።

በቀን 20/03/2018 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ወንጀል መከላከል እና የሮንድ ጥብቃ አተገባበሮች ቀዳሚ አጀንዳዎች ነበሩ።

የአከባቢው ነዋሪዎችም ወንጀለኞችን አሳልፎ ከመስጠት ረገድ የድርሻቸውን በተገቢው እየተወጡ መሆናቸውን የቀበሌው ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ሃላፊ ዋ/ሳጂን አድማሱ ሶማኖ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በበኩላቸው ለአከባቢው ሰላምና ጸጥታ ከፖሊስ አካላት ጋር በመስራት የተሻሉ ለውጦችን እየተመለከትን ነው በማለት በውይይቱ ላይ አብራርተዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

MINOTETTAN NAAGOOS ASUMMATETTAN HAGGAAZOOS

ፖሊስ ከአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ጋር የሚያደርገው ህዝባዊ ዉይይቶች ተጠናክሮ መቀጠላቸውን የዋዱ ቀበሌ ፖሊስ አስታወቀ።(ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፣  ህዳር 21/2018 ዓ.ም)በወ...
30/11/2025

ፖሊስ ከአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ጋር የሚያደርገው ህዝባዊ ዉይይቶች ተጠናክሮ መቀጠላቸውን የዋዱ ቀበሌ ፖሊስ አስታወቀ።

(ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፣ ህዳር 21/2018 ዓ.ም)

በወላይታ ሶዶ ከተማ ቀበሌ ፖሊስ በአከባቢው ጸጥታ ዙሪያ ህዝባዊ ውይይቶችን ማካሄዱን የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ተገኝ ወንጃሎ ገለጹ።

በቀን 20/03/18 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ውይይት ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር ያለውን ቁርኝት ማጠናከር ፤ አካባቢውን ከወንጀልና ከቆሻሻ የፀዳ ማድረግ ፤ ህዝባዊ ሮንድ ማጠናክር እና በየወቅቱ ውይይት መካሄድ ቀዳሚ አጀንዳዎች ነበሩ።

በአከባቢው የማታ ሮንድ ስራ እና ወንጀል መከላከያ መንገዶች ዙሪያ እንዲሁም በቀጠናው አመራርና ደምብ አስከባሪዎች ቅንጅት ዙሪያ ትኩረት ያደረገው ይሄ ውይይት ለቀጣይ የአከባቢዉን ሰላም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የቀበሌው ማህበረሰብ አቀፍ ማስተባበሪያ ሃላፊ ዋ/ሳጅን ተለሞስ ታፈሴ ጠቅሰዋል።

በአከባቢው ጸጥታ ረገድ የሮንድ ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱም በውይይቱ ተገምግሟል።

የአከባቢያችንን ሰላም ለማስጠበቅ ከፖሊስ አባላት ጋር ከመቼውም ጊዜ በላይ በጥምረት እየሰራን ነው ሲሉም የቆንቶ ልዩሃይል አከባቢ ነዋሪዎች ሀሳባቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የአከባቢዉን ሰላም ለማስጠበቅ የሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ተገኝ ወንጃሎ አሳስበዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

MINOTETTAN NAAGOOS ASUMMATETTAN HAGGAAZOOS!

ባደረግነው ድንገተኛ ፍተሻ የሺሻ ተጠቃሚዎችን ከነ ንብረታቸውና ተጠቃሚ ግለሴቦችበቁጥጥር ስር አውለናል፤ የመሃል ቀበሌ እና አራዳ ቀበሌፖሊስ (የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ ህዳር 20...
30/11/2025

ባደረግነው ድንገተኛ ፍተሻ የሺሻ ተጠቃሚዎችን ከነ ንብረታቸውና ተጠቃሚ ግለሴቦችበቁጥጥር ስር አውለናል፤ የመሃል ቀበሌ እና አራዳ ቀበሌፖሊስ

(የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ ህዳር 20/2018ዓ.ም)

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የመሐል ቀበሌ እና አራዳ ቀበሌፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ አደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚዎችን ከነንብረቶቻቸው ቁጥጥር ስር ማዋሉን የመሃል ቀበሌ ፖሊስ ማህበሬሰብ አቀፍ ማሰተባበርያ ሃላፊ ረ/ኢንስፔክተር ተሻገረ ታፈሴ ገለፁ።

በቀን 20/03/18ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት በመሃል ቀበሌ ግዶ ቀጠና ጫት ተራ አከባቢ አራዳ ቀበሌ ገናመ ወ/ሮ ሊደት ጌታሁን በተደረገው በዚህ ድንገተኛ ፍተሻ 21 ሺሻ ተጠቃሚዎችን ከ25 የሺሻ ዕቃ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው ረ/ኢንስፔክተር አክልሉ ከበደ የአራዳ ቀበሌ ማህበረሰብ አቀፍ ማሰተባበርያ ሃላፊ ገለፁት።

ፖሊስ በከተማዋ የሚያደርገው ድንገተኛ ፍተሻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማህበረሰብ አቀፍ ድቭዥን ሃላፊ ረ/ኢንሰፔክተር ምትኩ ማሞ አሳስበዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

MINOTETTAN NAAGOOS ASUMMATETTAN HAGGAAZOOS!

ሀሰተኛ መረጃ በመያዝ የኩላሊት በሽተኛ ይዘናል ብለው ህብረተሰብን እርዳታ ሲጠየቁ የነበሩ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።(የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ ህዳር 20/2018ዓ.ም)በ...
29/11/2025

ሀሰተኛ መረጃ በመያዝ የኩላሊት በሽተኛ ይዘናል ብለው ህብረተሰብን እርዳታ ሲጠየቁ የነበሩ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

(የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ ህዳር 20/2018ዓ.ም)

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የመሃል ቀበሌ ፣ በከተማዋ ውስጥ ሀሰተኛ መረጃ በመያዝ የኩላሊት በሽተኛ ይዘናል ብለው ህብረተሰብን እርዳታ ሲጠየቁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ብረሃኑ ባልቻ ገለፁ።

ኢንስፔክተሩ እንደገለፁት 8 ተጠርጣሪዎች ጀሚል ዝያድ ፣ አብርሃም ነቢ ፣ ሞጎስ ቡጋለ ፣ ስጦታ ጎንተ ፣ ማሙሽ ማቴዎስ ፣ ወርቅነህ ሻላሞ ፣ መሳይ ጎኖስ እና የአብስራ ኢያሱ የተባሉት እነኚ ግለሰቦች በቀን 19/03/2018 ዓ.ም ሶዶ ከተማ መሀል ቀበሌ ውስጥ ምንም መረጃ ሳይኖራው ሀሰተኛ ደብዳቤ በማዘጋጀት ኩላሊት በሽተኛ ይዘናል በማለት መኪናና ስፒከር ተከራይተው ከተማ እየዞሩ ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ ነበር የተያዙት።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ በበኩላቸው ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሰር ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ከመሰል ተግባራት እንዳይጭበረበር መረጃዎችን ማጣራት እንደሚያስፈልግ ኮማንደሩ ጨምረው አሳስበዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

MINOTETTAN NAAGOOS ASUMMATETTAN HAGGAAZOOS

የወንድማማችነት መርህን በማጉላት የህዝቦችን አንድነትና ሰላም ማረጋገጥ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የወንድማማችነት መርህን በማጉላት የህዝቦችን አንድነትና ሰላም ማረጋገጥ ይ...
29/11/2025

የወንድማማችነት መርህን በማጉላት የህዝቦችን አንድነትና ሰላም ማረጋገጥ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

የወንድማማችነት መርህን በማጉላት የህዝቦችን አንድነትና ሰላም ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን የገለጹት የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የፀጥታ ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነዉ።

በመክፈቻ ንግግራቸው ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የወንድማማችነት መርህን በማዳበር የህብረተሰቡን አንድነትና ሰላም ለማረጋገጥ ሁሉም መትጋት እንዳለበት አንስተው እንደ ሲዳማ ክልል መንግስትና ህዝቡ በጋራ ተቀናጅተው በመሥራታቸው ሰላማዊ ክልል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።

አያይዘውም የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሠራ ሥራ በመሆኑ ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየተሰራ ያለው ሥራና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ብለዋል።

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ኢታማጆር ሹም አማካሪ የሆኑት ጄኔራል አለምሸት ደግፌ እንደገለፁት፤ የሶስቱም ክልሎች የጸጥታ ሁኔታ ያለበትን በጋራ በመገምገም የአካባቢውን ጸጥታ የሚያናጉ ጉዳዮችን ለቅሞ በመለየት ከህብረተሰቡ እና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት ለመፍታት መድረኩ መመቻቸቱን ገልጸዋል።

አስተማማኝ ሰላም በማስፈን የህብረተሰቡን የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ፍጹም ሰላማዊ ለማድረግ ዘወትር መትጋት ይገባል ብለው የሶስቱም ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች የየክልሎቹን አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታን የሚገልጽ ሪፖርት እንዲያቀርቡ አድርገዋል።

የእያንዳንዱ ክልል ሪፖርት በዝርዝር ከቀረበ በኋላ ውይይት ተደርጎ በተለይ በድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች፣ በማህበራዊ ሚዲያ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ችግር ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላት፣ በሀይማኖት ጥላ ሥር የሚሠሩ የተሳሳቱ ድርጊቶች እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ውስጥ በመደበቅ የጥፋት ሥራ የሚሠሩ አካላትን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላትን በማቀናጀት ጠንካራ ሥራ በመስራት ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ በመድረኩ ላይ መግባባት ላይ መደረሱ ተመላክቷል።

የሲዳማ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በመድረኩ የሲዳማና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም አማካሪ፣ በኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የደቡብ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ከሶስቱም ክልሎች የመጡ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ራሳቸውን ጫኚና አውራጅ ነን በማለት ተቋም ላይ ሁከት የፈጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።(የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፤ ህዳር 19/2018ዓ.ም)በዎላይታ ሶዶ ከተማ ዋዱ አምባ ቀበሌ ...
28/11/2025

ራሳቸውን ጫኚና አውራጅ ነን በማለት ተቋም ላይ ሁከት የፈጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

(የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፤ ህዳር 19/2018ዓ.ም)

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ዋዱ አምባ ቀበሌ ውስጥ ራሳቸውን ጫኚና አውራጅ ነን በማለት ተቋም ላይ ሁከት የፈጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ተገኝ ዎንጃሎ ገለፁ።

ፍፁም አየሌ፣ አማኑኤል በቀለ ፣ ታሪኩ ሞርጋ እና ጥላሁን ጮሌ የተባሉት እነኚ ግለሰቦች በቀን 19/03/2018 ዓ.ም ራሳቸውን ጫኚ እና አውራጅ ነን በማለት በዋዱ አምባ ቀበሌ ዋዱ ቀጠና 1 እንድሪያስ ያያ ሆቴል ሕንፃ ግቢ ወስጥ ሁከት ፈጥረዋል።

ግለሰቦቹ ተቋሙ ውስጥ በመግባት የቢሮ ዕቃ ለማውረድ 15,000 በመጠየቅ ሁከት መፍጠራቸውን ነበር ረ/ኢንስፔክተር ተገኝ ዎንጃሎ የተናገሩት።

በመሆኑም የተቋሙ የህግ ክፍል ለዋዱ ፖሊስ ባደረሰው ይድረሱልን ጥሪ መሠረት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ገልጸዋል።

ኮማንደር ሀብታሙ አክለውም በተለያዩ አከባቢዎች ራሳቸውን ጫኚ እና አውራጅ ነን በማለት ህብረተሰቡን የሚያጭበረብሩ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

MINOTETTAN NAAGOOS ASUMMATETTAN HAGGAAZOOS!

በወላይታ ሶዶ ከተማ በድል በጌሬራ ቀበሌ ላይ ካፈቶስ በጎ አድራጎት ማህበር ከድል በጌሬራ ቀበሌ አሰተዳደር ጋር አንድ ላይ በመሆን የበጋ በጎ  የአረጋውያን ቤት ግንባታ ተግባራትን አከናወኑ ...
28/11/2025

በወላይታ ሶዶ ከተማ በድል በጌሬራ ቀበሌ ላይ ካፈቶስ በጎ አድራጎት ማህበር ከድል በጌሬራ ቀበሌ አሰተዳደር ጋር አንድ ላይ በመሆን የበጋ በጎ የአረጋውያን ቤት ግንባታ ተግባራትን አከናወኑ

ወላይታ ሶዶ ህዳር 18/03/2018 ዓ/ም በዚህ በበጋ
በጎ ተግባር ተግባር ላይ በመገኘት መክፈቻ ያደረጉት ኮሚሽነር ፍሳሐ ጋረደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አንደገለጹት ከዚህ ቀደምት ካፈቶስ በጎ አድራጎት ማህበር ዘርፍ ቡዙ የበጎ ተግባር ሥራ ስሰሩ እንደነበር ገለጸዋል።

ዛሬ በድል በጌሬራ ቀበሌ ቀጠና አንድ ላይ የተጀመረው የአረጋውያን የመኖሪያ ግንባታ ካፈቶስ በጎ አድራጎት ማህበር በአጭር ቀናት ውስጥ ገንብቶ ለአቅም ደካማ አባት ሰርቶ እንደሚያስረክቡ አልጠራጠርም እኔም ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ስሉ ኮሚሽነር ፍሰሃ ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የድል በጌሬራ ቀበሌ አስተዳደር አቶ መድህን አደለ በዛሬው እለት በቀበሌያችን የበጋ በጎ ተግባር ለመፈጸም የካፈቶስ በጎ አድራጎት ማህበር አባላትን አመሰግነዋለሁ።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በዛሬው እለት የግንባታ ሥራ የሚከናወንላቸው እኚሁ አባት አቅም ደካማ ከመሆናቸው የተነሳ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ መኖር በመረዳት የቤት ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሰለመጣችሁ እያመሰገንን እንዲቀበል አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጅ መሆናቸው አሰረድተዋል።

በዚህ መድረክ ላይ የተገኙ ወ/ሮ ትህትና ስሞኦን የወላይታ ሶዶ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍና የካፈቶስ ቦርድ አባል እንድሁም የካፈቶስ ማህብር አባላት አጠቃላይ ወጣቶች የቀበሌው አጠቃላይ አመራሮች ተገኝተዋል

በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው 11 ተጠርጣሪዎች ክስ ተመስርቶባቸዋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  ‎ወላይታ ሶዶ ከተማ፣ ሕዳር 18፣ 2018 በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተ...
27/11/2025

በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው 11 ተጠርጣሪዎች ክስ ተመስርቶባቸዋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

‎ወላይታ ሶዶ ከተማ፣ ሕዳር 18፣ 2018 በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው 11 ተጠርጣሪዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ክስ የተመሰረተባቸውም፡-
‎1ኛ ተከሳሽ አቶ ክፍሌ ወ/ማርያም ጋዎ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበረ፤

‎2ኛ ተከሳሽ አቶ ወልደአብ ደምሴ ክብረት በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ግብዓት ምርትና አቅርቦት ዐብይ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረ፣

‎3ኛ ተከሳሽ አቶ ተንሳይ ሜጫ ወ/ስላሴ በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ሀብት አመራር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ አባል የነበረ፤

‎4ኛ ተከሳሽ ወ/ሪት መንበረ ኃ/ማርያም ነጋሳ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የኮርፖሬሽኑ የግዢ ኮሚቴ አባል የነበረች፤

‎5ኛ ተከሳሽ አቶ ሚሊዮን ገረመው እሸቱ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የግዢ ባለሙያ እና የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ አባልና ፀሀፊ የነበረ፤

‎6ኛ ተከሳሽ አቶ ሰለሞን ገብሬ መላክ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ፣ የኮርፖሬሽኑ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ አባል፣ የብሄራዊ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ ፀሀፊ የነበረ፤

‎7ኛ ተከሳሽ አቶ መንግስቱ ተስፋ ላቀ በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የግብዓት አቅርቦት መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የብሄራዊ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረ፤

‎8ኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ዳኜ ሮሪሳ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ግዢ እና ትራንዚት ክፍል ስራ አስኪያጅ የነበረ፤

‎9ኛ ተከሳሽ ካፒቴን ወንድወሰን ካሳ አሰፋ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የነበረ፤

‎10ኛ ተከሳሽ አቶ ጸጋዬ በርሀ ኪዳኑ በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበረ፤

‎11ኛ ተከሳሽ አቶ አለባቸው ሞልቶት ዳኜ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ

‎በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ‎እነዚህ ተከሳሾች በጋራና በተናጠል የተሰጣቸውን ስልጣን ያለ አግባብ በመጠቀም የክልል መንግስታት ለኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የዓለም አቀፍ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈፅም የሰጡትን ውክልና እና የኮፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔዎች፣ የግዢ መመሪያዎችን፣ ውሎችና ድንጋጌዎችን በመጣስ ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ተከሳሾቹ የተጋገረውን ማዳበሪያ ማስከስከሻ ወጪ 204 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ያለአግባብ በመክፈል፣ ከመቀሌ መርከብ ጊር ተነቀለ በማለት ኮርፖሬሽኑ 100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ የማጓጓዣ ወጪ እንዲያወጣ በማድረግ፤ ጥራት የሌለው ማዳበሪያ የተጓጓዘበት ወጪ 39 ሚሊየን 992 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላርን ጨምሮ በድምሩ 40 ሚሊየን 296 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላር ወይም 5 ቢሊየን 681 ሚሊየን 857 ሺህ 260 በመመዝበር በሕዝብና በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዋናነትም በወንጀል አድራጊነት እና ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከባድ የሙስና ወንጀል የምርመራ መዝገብ አጣርቶ በፍትሕ ሚኒስቴር ለዐቃቤ ህግ ከላከ በኋላ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንደተመሰረተባቸውም አስታውቋል።

መንግሥት በሰጠው አቅጣጫ እና በተደረገ ሰፊ ጥናት ‎በአጭር ጊዜ ውስጥ ወንጀሉን አጣርቶ ተከሳሾች ለሕግ እንዲቀርቡ ያደረገው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቀጣይም በከባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ የጀመረውን ክትትልና ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር በመሆን ለተሾሙት ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ በኮሚሽኑ ማኔጅመንት አቀባበል ተደረገላቸው።ወላይታ ሶዶ ህዳር ...
27/11/2025

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር በመሆን ለተሾሙት ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ በኮሚሽኑ ማኔጅመንት አቀባበል ተደረገላቸው።

ወላይታ ሶዶ ህዳር 18/2019 ዓ/ም (ደኢፖኮ)

በቀድሞው ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ያገለገሉትና ባለፉት ሁለት አመታት የደቡብ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር ሆነው በሀላፊነት የሠሩት ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ወደ ቀድሞው ተቋማቸው በመመለስ ተቋሙን በእውቀታቸውና ልምዳቸው ተጠቅመው የክልላችን ፖሊስ አመራርና አባላትን ወደ ሚፈለገው አቅምና እውቀት ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ኮሚሽነሩ ያግዙናል ያሉት ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው ዳግም ወደ ቀድሞ ተቋሞ እንኳን ደህ መጡ ባለዋል።

የኮሚሽኑ ማኔጅመንት አባላት ኮሚሽነሩ ዳግም ወደ እናት ክፍሎ እንኳን ደህና መጡ ያሉ ሲሆን ለተቋማዊ ለውጥ በጋራ እንደሚሠሩም ገልጸውላቸዋል።

በተቋሙ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ በበኩላቸው የክልሉ ፖሊስን ዳግም እንዳገለግል እድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ያሉ ሲሆን በቀጣይ ተቋሙ ላቀዳቸው መደበኛና ሪፎርም ስራዎች ስኬታማነት የድርሻዬ ለመወጣት እጥራለሁ ብለዋል።

በኮሚሽኑ ማኔጅመንት አባላት ስለተደረገላቸው አቀባበልም አመስግነዋል።

በአስር አመት ህፃን ላይ እገታ እና በአሰቃቂ ሁኔታ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ  በሞት እንዲቀጣ ተወሰነአርባምንጭ፦ ህዳር 18 /2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)  የአቀ...
27/11/2025

በአስር አመት ህፃን ላይ እገታ እና በአሰቃቂ ሁኔታ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

አርባምንጭ፦ ህዳር 18 /2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)

የአቀቤ ሕግ የክስ ቻርጅ እንደሚያሳየው፣ ተከሳሽ ወርቅነህ አሰፋ ደርሰው የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ ቁጥር 539(1) (ሐ) እና 590/2//ሠ/ ስር የተደነገገውን ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የአስር አመት ታዳጊን በማገትና በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል።

ተከሳሽ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቻ ክፍለ ከተማ ዶይሳ ቀበሌ በተለምዶ ኒው ቪዥን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቀን 03/03/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ አስቀድሞ ማነኛውንም ህፃን ልጅ ጠልፎ በመያዝ ከተጠላፊው ቤተሰብ ገንዘብ በመውሰድ የራሴን ኑሮ እቀይራለሁ በሚል አደገኛ አስተሳሰብ ይሄንኑ አላማ ለመፈፀም እንዲያስችለው ፕላስቲክ ማሸጊያ እቤቱ አዘጋጅቶ ማኖሩን የአቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ያሳያል።

በእለቱ ተከሳሽ የሚያስተምርበት ት/ቤት ተማሪ የሆነውን የአስር አመት ህጻን ልጅ ሟች ናትናኤል ማይክል ከት/ቤት ሲመለስ መንገድ ላይ አስቁሞ እያዋራው ቆይቶ ተከራይቶ ወደ ሚኖርበት ግቢ ሟች እንዲመጣ ካደረገው በኋላ፤ ሟችን በቀኝ ግንባሩ ላይ በቦክስ በመምታት በአፍንጫውና በአፉ ደም እንዲፈስ በማድረግ መሬት ላይ ከጣለው በኃላ ሟችን ተሸክሞ ወደ ሚኖርበት ቤት ክፍል ውስጥ በማስገባት የሟችን አፍ እና አፍንጫ ከማጅራቱ ጋር አጥብቆ በፕላስተር ማሸጊያ ካጠበቀው በኃላ የቤቱን በር በሟች ላይ ቆልፎ መውጣቱም በክስ ዝርዝሩ ተካቷል

ተከሳሽ ሟችን ይዞ ከአከባቢው ለመሰወር እንዲያመቸው የአከባቢውን ሁኔታ ሲቃኝ ሟች የታሸገበትን ፕላስተር ታግሎ በመፍታት ራሱን ለማትረፍ የድረሱልኝ ጩኼት በማሰማቱ ተከሳሽ ተመልሶ በመምጣት በድጋሚ አፍና አፍንጫውን አጥብቆ በማፈን ካሸገው በኃላ ሟችን በሕይወት እያለ ፎቶ ግራፍና ተንቀሳቃሽ ቪድዮ በስልኩ በመቅረጽ አመች ቦታ ሲደርስ ከሟች ቤተሰብ ጋር ገንዘብ ለመደራደር በማሰብ የሟችን አንገት በአንሶላ አንቆ ሕይወቱን እንዲያልፍ ካደረገ በኃላ አስክሬኑን የገደለበት ቤት መፀዳጃ ቤት ውስጥ እንደከተተውም በክስ ዝርዝሩ ተገልፆል።

ተከሳሽ አስክሬኑ እንዳይታይ የአንሶላ ጨርቅ ከላይ በመጣልና በመሰወር ከሚኖርበት ቤትና አከባቢ ሸሽቶ በቀን 05/03/2018 ዓ.ም በመኪና ተሳፍሮ ወደ ምዕራብ አባያ ወረዳ አቅጣጫ በማምለጥ ላይ እያለ ፉራ ቀበሌ ውስጥ በሕብረተሰቡ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ሊያዝ ችሏል።

በመሆኑም ተከሳሽ ሌላ ወንጀል ለመፈፀምና የፈፀመውን ወንጀል ለመደበቅ ጭካኔ በተሞላው መንገድ ተማሪውንና ራሱን መከላከል የማይችል ህፃን አስቦ በመግደል እና ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህፃን ልጅ በመጥለፍ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡

በዚህም መሰረት የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን ክስ ፣ የሰውና የሰነድ የኤግዚቢት ማስረጃዎች በመሰማት ዐቃቤ ህግ በሁለቱም ክሶች ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ በተከሳሽ ላይ በማስረዳቱ ተከሳሽ እንዲከላከል ሲል ብይን ሰጥቷል።

በመሆኑም ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ሲል መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በቀን 18/3/2018 ዓ.ም በወዋለው ችሎት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share