Yederaw

Yederaw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yederaw, Media/News Company, Bole, Addis Ababa.

''IshowSpeed'' ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹📌ታዋቂው የማህበራዊ ገጾች ኮከብ አይሾው ስፒድ (IshowSpeed) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ እንደሆነ ተገለጸ🔴 በ'የደራው መጽሔት    | በዓለም አቀፍ ...
31/12/2025

''IshowSpeed'' ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹

📌ታዋቂው የማህበራዊ ገጾች ኮከብ አይሾው ስፒድ (IshowSpeed) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ እንደሆነ ተገለጸ

🔴 በ'የደራው መጽሔት

| በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉትና በከፍተኛ ጉልበት በሚያቀርባቸው የቀጥታ ስርጭት (Livestream) ቪዲዮዎቹ የሚታወቀው አሜሪካዊው የዩቲዩብ ኮከብ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር (IshowSpeed) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን ፍንጭ ሰጥቷል።

ተጫዋቹ በቅርቡ በተለያዩ የዓለም ሀገራት እያደረገ የሚገኘውን የጉብኝት አካል አድርጎ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንደሚያቀና ተነግሯል።

ስፒድ በተለይም በተለያዩ ሀገራት በሚያደርጋቸው ቆይታዎች የሀገሪቱን ባህል፣ ምግብና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በቀጥታ ስርጭት ለዓለም በማስተዋወቅ ይታወቃል።

ስፒድ ወደ አዲስ አበባ በሚመጣበት ወቅት በከተማዋ የተለያዩ ስፍራዎች በመዘዋወር ከደጋፊዎቹ ጋር እንደሚገናኝና ይህም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ተመልካቾቹ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ይጠበቃል።

ይህ ዜና በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ ዕለት ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና የዩቲዩብ ተከታዮች ከፍተኛ ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

በቆይታው የአዲስ አበባን ውበት ፣ የኢትዮጵያን ቡና፣ ባህላዊ ምግቦችና ታዋቂ የቱሪስት መስህቦችን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሊያስተዋውቅ እንደሚችል ይገመታል።

አይሾው ስፒድ በቅርቡ በኖርዌይ፣ ጣሊያንና አልባኒያ ባደረጋቸው ጉብኝቶች እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አቀባበል አድርጎለት እንደነበር ይታወሳል። የኢትዮጵያው ጉብኝትም በተመሳሳይ መልኩ ደጋፊዎቹን ወደ አደባባይ እንደሚያወጣ ተገምቷል።

የደራው መጽሔት
''ፀሐይ አትጠልቅም''

31/12/2025
ዶ/ር ቴድሮስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ምስጋና አቀረቡበ'የደራው መጽሔት  | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባህላዊ ሕክም...
21/12/2025

ዶ/ር ቴድሮስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ምስጋና አቀረቡ

በ'የደራው መጽሔት

| የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባህላዊ ሕክምናን በዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ውስጥ የላቀ ቦታ እንዲይዝ ላደረጉት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ህንድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በጤናው ዘርፍ እያሳየች ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ለዚህም እንደ ማሳያ የጠቀሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

* የአዩሽ (Ayush) ሚኒስቴር መቋቋም፦ ባህላዊ ሕክምናን በሳይንሳዊ መንገድ ለማሳደግና ለማስተዋወቅ የተቋቋመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለዘርፉ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

* የዓለም አቀፍ የባህላዊ ሕክምና ማዕከል፦ በህንድ ጃምጋር (Jamnagar) ከተማ የዓለም ጤና ድርጅት የባህላዊ ሕክምና ማዕከል እንዲቋቋም ህንድ ላደረገችው ከፍተኛ ድጋፍ አድናቆታቸውን ችረዋል።

የህንድ ተሞክሮ ጥንታዊ ወጎች ከዘመናዊ ፈጠራዎች ጋር፣ እንዲሁም የታሪክ ቅርስ ከሳይንስ ጋር ተቀናጅተው ሊራመዱ እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም፣ ዶ/ር ቴድሮስ የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲን "አንድ ምድር፣ አንድ ጤና" (One Earth, One Health) የሚለውን መርህ እንደሚጋሩና ለዚህም ስኬት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የደራው መጽሔት
''ፀሐይ አትጠልቅም''

13/04/2025

ቻልኩበት!

ኩኩ ከሁሉ ጋር በጥበብ መኖርን ትችልበታለች
ትንሽ ትልቁንም ማክበር መገለጫዋ ነው!
ቻልኩበት ብላ ያዜመችልን ስርአቱን፣ሰው ማክበሩን፣አስውቦ ማዜሙንም ጭምር ሳይሆን አይቀርም

ኩኩ ሰብስቤ ከዝነኛው ቴድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ ጋር የጣመሩበት ልዩ ስራ "ደጃዝማች"...

የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ በደጆ ነው!!

📌ያማረሩን የሰፈር ጫኝ አውራጆች
📌የአዲስ አበባ የባቡር ሃዲድ ሊፈርስ ይሆን?
📌አሜሪካ ያሉ ስደተኞች ስጋት
📌የዋጋ ግሽበቱ ነገር
📌የደራው ሰሌዳ
📌ኦን ላይን ሽቀላ

እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw

05/04/2025

እናንተዬ ዱባይን አይታችኋታል?

ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ሊዲያና ሰለሞን ቪዚት ዱባይ በተሰኝው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዙፍ ኢኒሼቲቭ ሰዎች ዱባይን ይጎበኙ ዘንድ በትጋት እየሰራች ነው::

አሁን ደግሞ ሌላ ታሪክ..ዝርዝሩን ይዘናል

የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ይዞ በደጆ ነው!!

📌በአዲስ አበባ በሰማይ በራሪ ታክሲዎች
📌የአሜሪካው ታሪፍ
📌የቲክቶክ ውለታ
📌ወደብ ማግኝት
📌መርካቶ እንሂድ
📌በBig Habesha የሙዚቃው ዓለም ጦርነት

እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw

05/04/2025

እናንተዬ ዱባይን አይታችኋታል?

ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ሊዲያና ሰለሞን ቪዚት ዱባይ በተሰኝው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዙፍ ኢኒሼቲቭ ሰዎች ዱባይን ይጎበኙ ዘንድ በትጋት እየሰራች ነው::

አሁን ደግሞ ሌላ ታሪክ..ዝርዝሩን ይዘናል

የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ይዞ በደጆ ነው!!

📌በአዲስ አበባ በሰማይ በራሪ ታክሲዎች
📌የአሜሪካው ታሪፍ
📌የቲክቶክ ውለታ
📌ወደብ ማግኝት
📌መርካቶ እንሂድ
📌በBig Habesha የሙዚቃው ዓለም ጦርነት

እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw

29/03/2025

ዳግም ተገናኝን:
በነፃ ይኮምኩሙ!!

አሻም!!የተወደዳችሁ!!
ዛሬ ቅዳሜ ነው!የደራው ቅዳሜ!!🔥🔥

የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ይዞ በደጆ ነው!!

📌የቤተ መንግስቱ የቀድሞ እመቤት
📌ባንኮቹ ሁሉ እስከ ምሽት ሶስት ሰዓት
📌የጎደለው ግማሽ ቢልዮን ብር
📌በ150 ብር የጾም ቡፌ
📌የመርካቶ አንባ
📌Big Habesha ሴቲንጉን እንድናስተካክል ነግሮናል

እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw

Address

Bole
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yederaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share