04/04/2026
ህወሓት የትግራይን ወጣቶች ለአል ቡርሃን ጦር ሽጧል !!
ህወሓት ማለት የትግራይን ህዘብ ለሚፈልገው ዓላማና የፖለቲካ ትርፍ ከተጠቀመ በኋላ ዞር ብሎ የማያይ የትግራይ ህዘብ ታሪካዊ ጠላት ነው። የትግራይ ወጣቶችን ላለፉት ሃምሳ እና ከዛ በላይ ለሆኑ ዓመታት የአፈሙዝ እራት በማድረግ የትግራይ እናቶች ካለልጅ እንዲቀሩ ፣ የትግራይ አባቶችንም ያለ ጧሪ ቀባሪ ያስቀረ የአረመኔዎች ስብስብ ነው ህወሓት። አሁንም ድመት መልኩሷ አመሏን አትረሳ ነውና ነገሩ ፣ ህወሓት በትግራይ እናት ልጆች የራሱን ከርስ እየሞላ ይገኛል ፤ ህወሓት የትግራይ ወጣቶችን በግዳጅ በማፈስ ለሱዳኑ አልቡርሃን ጦር በዶላር እየሸጠ እንደሚገኝ ታውቋል።
የትግራይ ወጣቶች ራሳቸውን ከህወሓት ለማስመለጥ ሲሉ ተሰደዋል ፣ በማያቁት ሃገር ሄደዋል ፤ ይሁን እንጂ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ወረርሽኝ በመሆን የትግራይን ወጣቶች በለጋ እድሜያቸው የበላ ስብሰበ ነው ፤ ይሄ አልበቃ ያለው ህወሓት የትግራይን ወጣቶች በመሸጥ ሆዱን እየሞላ ፣ ኪሱን እያደለበ ይገኛል።