የ መ/ር ነፃነት ስብከቶች እና ዝማሬዎች

የ መ/ር  ነፃነት ስብከቶች እና ዝማሬዎች የዘማሪ መ/ር ነፃነት የመዝሙር እና የስብከት ትምህርቶችን ለማግኘት ፔጁን ይውደዱት። Like my page to be a member of my family .

የደከሙትን በእግዚአብሔር ቃል እናበረታለን።ሳይንሳዊ እና መንፈሳዊ ስልቶችን በመጠቀም ከዚህ ዓለም ጋር እንደት መኖር እንዳለብን ጭምር ምክር እንለግሳለን።

 #ማንም  #የቆመ  #መስሎት  #እንዳይወድቅ  #ይጠንቀቅ  #ነፍስ  #ይማር ዛሬ እጅግ አሳዛኝ ዜና ቤተክርስቲያን ሰማች። ወዳጆቼ በቤተክርስቲያን የተመሰገነ እና የተወደሰ ትሁት የሆነ የቅድ...
27/08/2025

#ማንም #የቆመ #መስሎት #እንዳይወድቅ #ይጠንቀቅ
#ነፍስ #ይማር
ዛሬ እጅግ አሳዛኝ ዜና ቤተክርስቲያን ሰማች። ወዳጆቼ በቤተክርስቲያን የተመሰገነ እና የተወደሰ ትሁት የሆነ የቅድስት ስላሴ ዩኒቨርሲቲ የጥናት /research ክፍል ሀላፊ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ክፍል ሀላፊ የሆነውን ረዳት ፕርፌሰር አብነትን አጣን በጣም የሚያሳዝን ህልፈት ነው ነፍሱን በአፀደ ነፍስ ያሳርፍልን።

 #ፍልሰታ  #ለማርያም --------------------              እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍቷ በሆነ 21 ቀን በጌቴሴማኒ ሥርዓተ ቀብሩ አልተፈጸመም ነበር። ምክንያቱ...
22/08/2025

#ፍልሰታ #ለማርያም
--------------------

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍቷ በሆነ 21 ቀን በጌቴሴማኒ ሥርዓተ ቀብሩ አልተፈጸመም ነበር። ምክንያቱም አይሁድ በምቀኝነት ተነሣሥተው በፈጠሩት ሁከት የእመቤታችን ሥጋዋ ወደ ገነት ተሠውሮ በዕፀ ሕይወት ሥር ከቆየ በኋላ ሐዋርያት ለሁለት ሱባኤ ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ በ14 ኛው ቀን ( ከነሐሴ 1-14 ነው) ሥጋዋን ሰጥቶአቸው በጌቴሴማኒ ቀበሩአት። ከዚያም ነሐሴ 16 በሦስተኛው ቀን ማለት ነው ተነሥታ ዐርጋለች።
#እንኳን #አደረሰን #አደረሳችሁ

Dear GOD, thank you for being beside me for the past and for the coming amazing years of my life. AND Thank you for bles...
10/09/2024

Dear GOD, thank you for being beside me for the past and for the coming amazing years of my life. AND Thank you for blessing me with a very bright future.

04/09/2024

የሰው ልጅ የሚተነፍስ አፈር ነው።

19/08/2024
ነገረ ስላሴ በተዋህዶ
02/08/2024

ነገረ ስላሴ በተዋህዶ

05/01/2024

" ትእምርተ ሰላምነ ወልድ ተወለደ ለነ:
የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነው ወልድ ወይም ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተወለደልን"
✥ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ✥

11/12/2023

የሰው ልጅ ዓላማ እግዚአብሔርን መምሰል ነው።

03/12/2023

ነገረ መለኮት ምንድነው?
What is Theology?
፨ነገረ-መለኮት የሃይማኖት እምነቶች፣ ጽንሰ-ሐሳቦች፣ ልምምዶች እና የእግዚአብሔር ወይም የመለኮት ተፈጥሮ ጥናት ነው። ከአማልክት ህልውና፣ ከእግዚአብሄር ባህሪ፣ ከሃይማኖታዊ ጽሑፎች ትርጓሜ፣ ከሃይማኖታዊ ወጎች አመጣጥ እና እድገት፣ እንዲሁም በሰው ልጅ እና በመለኮታዊ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከቱ ጥያቄዎችን የሚዳስስ አካዳሚክ ትምህርት ነው።

፨ነገረ-መለኮት ብዙውን ጊዜ ከተደራጁ ሃይማኖቶች ጋር የተያያዘ ነው, ለምሳሌ ክርስትና, እስልምና, ይሁዲነት, ሂንዱይዝም, ቡዲዝም እና ሌሎችም. ሆኖም፣ ከባህላዊ ሃይማኖታዊ ማዕቀፎች ውጭ መንፈሳዊ እና ሜታፊዚካል ፅንሰ-ሀሳቦችን ማጥናትንም ሊያካትት ይችላል።

፨የነገረ መለኮት መስክ ሂሳዊ ትንታኔን፣ ትርጓሜን እና ስልታዊ የሃይማኖት ትምህርቶችን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን፣ የአምልኮ ሥርዓቶችን፣ ስነ-ምግባሮችን እና የእምነት ፍልስፍናዊ ገጽታዎችን ያካትታል። የሃይማኖት ሊቃውንት ስለ ሃይማኖታዊ እምነቶች እና ልማዶች ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ለማግኘት ሃይማኖታዊ ጽሑፎችን፣ ታሪካዊ ሁኔታዎችን፣ ፍልስፍናዊ ክርክሮችን እና ባህላዊ ተጽዕኖዎችን መመርመር ይችላሉ።

፨ነገረ-መለኮትን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማለትም ፍልስፍናዊ፣ ታሪካዊ፣ ሥነ-ምግባራዊ፣ ንጽጽር እና ተግባራዊን ጨምሮ ማቅረብ ይቻላል። የነገረ መለኮት ጥናቶች በአካዳሚክ ተቋማት፣ ሴሚናሮች ወይም የሃይማኖት ማሰልጠኛ ማዕከላት ሊደረጉ ይችላሉ፣ እና በነገረ መለኮት ጥያቄ የሚሳተፉ ግለሰቦች ብዙ ጊዜ የነገረ መለኮት ሊቃውንት ተብለው ይጠራሉ።

፨ ነገረ መለኮት የአካዳሚክ ዲሲፕሊን መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፣ እና ሃይማኖታዊ እምነቶችን ማጥናትን የሚያካትት ቢሆንም፣ የግድ የግል ሀይማኖታዊ እምነትን ወይም የተለየ ሃይማኖታዊ ወግ ማመንን አይፈልግም።
ቀጣይ ስለ ምስራቅ( Eastern) ወይም ኦርየንታል ኦርቶዶክስና ምዕራባውያን አብያተ ክርስቲያናት በነገረ መለኮት ያላቸውን አተያይ ይዤ እቀርባለው----
ላይክ ማድረግ እንዳይረሳ
ይቆየን።

 #ዶክተር  #ሰለሞን  #በርሄ በቃሉ መሠረት  #2400 እና የስለት 100 ብር አጠቃላይ  #2500 ብር በጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት በመሎ ላሃ ወረዳ ለሚገኘው  ለ #ማይዘሎ ደብረ ሰላም መድኃኔ...
06/12/2022

#ዶክተር #ሰለሞን #በርሄ በቃሉ መሠረት #2400 እና የስለት 100 ብር አጠቃላይ #2500 ብር በጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት በመሎ ላሃ ወረዳ ለሚገኘው ለ #ማይዘሎ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ህንጻ ማሰርያ ኮሚቴ ገቢ አድርጓል።
እግዚአብሔር ባለበት ቦታ በሰላም ያኑርልን በሉ።
እግዚአብሔር ይስጥልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን።

Address

Bole
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የ መ/ር ነፃነት ስብከቶች እና ዝማሬዎች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category