
23/09/2025
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን !
የሰዑዲያ ታላቁ ዓሊም ሙፍቲ እና ለረጅም ዓመታት በሀጅ ላይ የዐረፋን ኹጥባ በማቅረብ የሚታወቁት ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አል ሸይኽ ወደ ማይቀረው ጉዞ መሄዳቸው የሙስሊሙን ኡማ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ከቶታል።
ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አል ሸይኽ በሰፊ እውቀታቸው በታታሪነታቸው ይታወቁ ነበር። የሱናን ትምህርት በማስፋፋት እና ሙስሊሞችን በመምከር ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ታላቅ ክብር ይገባቸዋል። በተለይም ለዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሐጅ ተጓዦችን ስሜት የሚነካ የዐረፋን ኹጥባ በመስጠት ከኡማው ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ ነበራቸው።
የእኚህ ታላቅ ዓሊም ሞት ለመላው የእስልምና ዓለም ትልቅ ኪሳራ ሲሆን ትምህርታቸውና አበርክቶዎቻቸው ግን ይኖራል። ለመላው ቤተሰቦቻቸው ለተማሪዎቻቸው እና ለመላው የሙስሊም ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የመጨረሻ ማረፊያቸውን ጀነት ያድርግላቸው። አሚን! በዱዓአችን አንርሳቸው።