03/12/2025
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ ውቡን የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት ጎበኙ
(ሀረር-ዴይሊ፤ ህዳር 24/ 2018) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
አባድር ፕላዛ በሀረር የጀጎል አጥር ከዝነኛውና ታሪካዊው አስመዲን በሪ (ሸዋበር) መግቢያ ጀምሮ እስከ ሌላኛው የጀጎል አምስት በሮች አንዱ የሆነው በድሪ በሪ (ቡዳበር) ድረስ የሚዘልቅ የተዋበ የኮሪደር ልማት ስራ ነው።
ይህን ፕሮጀክት አመሻሽ ላይ የጎበኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን እንዳሉት የአባድር ፕላዛና ሌሎች በከተማው እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን ገፅታ የሚቀይሩ ናቸው።
በተለይም ከተማዋ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች የበለጠ ምቹ እንድትሆን የሚያስችሉ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንደ ክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዘገባ ከህዝባችን ጋር በመቀናጀት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችም ከአሁኑ ትውልድ ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ መሰረት የሚጥሉ ናቸው ሲሉ ርዕሰመስተዳድሩ አመልክተዋል።
ከተማዋ ወደኋላ የቀረችባቸው አመታትን በሚክስ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ ኦርዲን አረጋግጠዋል።
#ሀረር