WMCC AddisWalta - AW
አዲስ ዋልታ
Walta Media and Communication Corporate Who We Are
Walta Media and Communication Corporate S.C.

(WMCC) is a broadcast media company based in Addis Ababa, the political capital of Africa. The company which owns TV and Radio Stations aspires to become a pan African media company currently disseminating information in local and international languages. Walta has built its reputation through covering all aspect of Ethiopia and beyond in its professional news, documentary and programs reporting.

Hard work, commitment to change, sincerity, customer respect, and respect to diversity are the hallmark of our institution. Since the founding of our corporation in 1986, we have been striving to be equipped with state-of-the-art media technology that tailored to the needs of 21 century media landscape. Major Functions
Apart from producing and disseminating professionally crafted news, documentary and programs through our broadcast stations and digital media platforms, our corporation is engaged in top notched research, public relations and event organizing, media training, digital signage, and outdoor advertising. For any inquiry you might have, please do not hesitate to reach out to us through the following contact address. If you wish to visit our head office physically, we are located on Sierra Leone Street/ Debrezeit Road, Behind Commercial Bank of Ethiopia Temenja Yaji Branch. Contacts
Head Office: +251114670303
Fax: +251114670302
Email: [email protected]
Customer Service
Cell: +251944959595
Office: +251114705971
Email: [email protected]
Fax: +251114670302
Documentary
Office: +251114704229
Program
Office: +251114704952
Human Resource
Office: +251114670453
Fax: +251114670302
TV News

Office: +251114707335
Email: [email protected]
Walta FM
Office: +251111552200
Email: [email protected]
Web and Social Media
Office: +251114704139
Walta SMS: 8970
Website: www.waltainfo.com
Facebook Amharic: https://bit.ly/3Ma7QTW
Facebook English: https://www.facebook.com/WMCC-English-108890734710426/
Facebook Arabic: https://bit.ly/3vmjIZR
Twitter Amharic: https://twitter.com/walta_info
Twitter Arabic: https://twitter.com/walta_arabic
YouTube: https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Telegram: https://t.me/WALTATVEth

በቺካጎ ማራቶን ሃዊ ፈይሳ አሸነፈችአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ47ኛው የቺካጎ ማራቶን አትሌት ሀዊ ፈይሳ አሸንፋለች፡፡አትሌት ሀዊ ርቀቱን 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ56 ...
12/10/2025

በቺካጎ ማራቶን ሃዊ ፈይሳ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ47ኛው የቺካጎ ማራቶን አትሌት ሀዊ ፈይሳ አሸንፋለች፡፡

አትሌት ሀዊ ርቀቱን 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መገርቱ አለሙ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ "ሕዳሴ ዋንጫ" ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 2 ...
12/10/2025

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ "ሕዳሴ ዋንጫ" ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።

የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አሸናፊ ጌታቸው እና አዲሱ አቱላ አስቆጥረዋል።

መቻልን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቻርለስ ሙሴጌ ከመረብ አሳርፏል።

መቻል፣ኢትዮዽያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በቅደም ተከተል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ መርሐ ግብሩን አጠናቅቀዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ያደረጉት ውይይት በምስል፡-
12/10/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ያደረጉት ውይይት በምስል፡-

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ትርጉም …አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡ቀኑ “ሰንደ...
12/10/2025

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ትርጉም …

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡

ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው፡፡

በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት እና በሰንደቅ ዓላው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ምንድን ነው?

1. አረንጓዴው ቀለም፡- የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው፡፡

2. ቢጫው ቀለም፡- የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው፡፡

3. ቀዩ ቀለም ፡- ለነፃነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡

እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. ክብ የሆነው፡- ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል፡፡

2. ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች፡- የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሐይማኖቶችን እኩልነት ያመለክታሉ፡፡

3. ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ፡- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ የመሠረቱትን አንድነት ያመላክታል፡፡

4. ቢጫ ጨረሩ ደግሞ ፡- በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሔር፣ ብሔረሰቦች የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል፡፡

በአቤል ነዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

የአዳብና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነውአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዳብና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በወዳጅነት ፓርክ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተ...
12/10/2025

የአዳብና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዳብና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በወዳጅነት ፓርክ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡

አዳብና በጉራጌ ማሕበረሰብ ዘንድ ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት አምስት ቀን ድረስ ወጣቶች በተለያዩ ባሕላዊ ትውፊቶች የሚያከብሩት በዓል ነው።

የማሕበረሰቡ ባህላዊ መገለጫ ከሆኑት ባህልና እሴቶች መካከል አንዱ የሆነው አዳብና የመተጫጫ፣ የነፃነት እንዲሁም የተጠፋፉ ወዳጆች የሚገናኙበት በዓል መሆኑም ተመላክቷል።

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ባሕልን በማስተዋወቅ የቱሪስት ስበት እንዲሆን መሰል ፌስቲቫሎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተጠቅሷል፡፡

በመላኩ ገድፍ

በሶማሌ ክልል የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል በቅርቡ የተመረቁና የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን አስመ...
12/10/2025

በሶማሌ ክልል የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል በቅርቡ የተመረቁና የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የዲጂታል ሚዲያ ዳይሬክተር አቶ ቢሻር ሞሐመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የድጋፍ ሰልፉ በዛሬው ዕለት በክልሉ በሚገኙ 95ቱም ወረዳዎች እና ስድስቱ ከተማ አስተዳደሮች ነው የተካሄደው።

የድጋፍ ሰልፉ መንግሥት በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ በመጀመሩና ከዚህ በፊት የነበረባቸውን ጥያቄዎች እየመለሰ በመሆኑ እንደሆነ አንስተዋል።

በዚህም አሁን ላይ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ በመሆኑ ደስተኛ እንደሆኑና ለመንግሥት ያላቸውን አጋርነት ለማረጋገጥ ያለመ ሰልፍ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

በአፋር ክልል ባራሕሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደረሰአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀ...
12/10/2025

በአፋር ክልል ባራሕሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

የሰሜናዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ አስሓብ የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረዋል።

በሁለቱ ወረዳዎች መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ለተጎጂዎች ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

የባራሕሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሊ ሁሴን በበኩላቸው÷ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በአደጋው እድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ህይወት ማለፉን ገልጸው÷ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም አስረድተዋል።

በመሬት መንቀጥቀጡ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ መቅረታቸውን ጠቁመዋል።

ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

በአሊ ሹምባሕሪ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ተጠባቂው የፍጻሜ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቻል...አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ "ሕዳሴ ዋንጫ "ዛሬ ፍጻሜውን ሲያገኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመ...
12/10/2025

ተጠባቂው የፍጻሜ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቻል...

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ "ሕዳሴ ዋንጫ "ዛሬ ፍጻሜውን ሲያገኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቻል ለዋንጫው ይፋለማሉ፡፡

መቻል በግማሽ ፍጻሜው ኢትዮ ኤሌክትሪክን በኮለን ኮፊ ብቸኛ ግብ በማሸነፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወሳል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በበኩሉ÷ በግማሽ ፍጻሜው ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በመርታት ለፍጻሜ መድረሱ አይዘነጋም፡፡

ሁለቱ የፍጻሜ ተፋላሚዎች በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ተገናኝተው መቻል 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ተጠባቂው የፍጻሜ ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት 30 ላይ በአዲስ አባባ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋልአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ...
12/10/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከቡርኪናፋሶ ጋር ዛሬ ምሽት ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን በምደቡ ካደረጋቸው 9 ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ፤ በአራቱ ተሸንፎ እንዲሁም በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።

በዚህም ብሔራዊ ቡድኑ 9 ነጥብ በመሰብሰብ በምድቡ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ተጋጣሚው የቡርኪናፋሶ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ፥ በ18 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ 10ኛ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ መደረግ ይጀምራል።

አስቀድማ ወደ 2026 ዓለም ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠችው ግብፅ፥ ምድቡን በ23 ነጥብ ስትመራው ቡርኪናፋሶ በ18፣ ሴራሊዮን በ12፣ ጊኒ ቢሳው በ10፣ ኢትዮዽያ በ9 እንዲሁም ጅቡቲ በ1 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የኢሬቻ በዓል አከባበር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በምስል:-
12/10/2025

የኢሬቻ በዓል አከባበር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በምስል:-

የኢሬቻ በዓል በቡራዩ በመልካ አቴቴ፣ በገላን በመልካ ጨፌ ቱማ፣ በሰበታ በመልካ ሰበታ እና በሰንዳፋ በኬ በመልካ ጎራ ተከብሯል።
12/10/2025

የኢሬቻ በዓል በቡራዩ በመልካ አቴቴ፣ በገላን በመልካ ጨፌ ቱማ፣ በሰበታ በመልካ ሰበታ እና በሰንዳፋ በኬ በመልካ ጎራ ተከብሯል።

ጀግንነት ክላሽ ከማንገብ ይልቅ ሀገር በማልማት መገለጥ አለበት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጀግንነታችን መገለጥ ያለበት ክላሽ በማንገ...
11/10/2025

ጀግንነት ክላሽ ከማንገብ ይልቅ ሀገር በማልማት መገለጥ አለበት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጀግንነታችን መገለጥ ያለበት ክላሽ በማንገብ ሳይሆን ሀገር በማልማትና የህዝብን ኑሮ በማሻሻል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፌዴራል እና ክልል አመራሮች ጋር በገጠር ኮሪደር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ጀግንነት የሚለው እሳቤ በተሳሳተ አውድ እየተተረጎመ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ጀግንነት ክላሽ አንግቦ መዞር ሳይሆን የደሀ እናትን ቤት በመስራት የሚገለጥ ነው ብለዋል፡፡

ጀግንነትን በተሳሳተ መንገድ ተገንዝበው ላልተገባ ዓላማ ጊዜ እና ጉልበታቸውን የሚያጠፉ ወንድሞቻችን የደሃ ወገኖቻችንን ህይወት ለመቀየር ሊሰሩ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጀግንነት ሀገርን በመለወጥና የህዝቡን ኑሮ በማሻሻል መገለጥ እንዳለበት ጠቅሰው፥ ይህን ማድረግ ከቻልን ከልመና መውጣት እንችላለን ነው ያሉት፡፡

በቅርቡ ከልመና ነጻ ለመውጣት ህዝብ በማወያየት ስራ ጀምረናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አብዛኞቹ ክልሎች እነዚህን ስራዎች በይፋ ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ መኖሪያቸው በመመለስ ሰርተን ህይወታቸውን በመለወጥ ኢትዮጵያን ባጠረ ጊዜ ከልመና ማውጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

ሰዎችን አፈናቅሎ ማፈን እንደ ፖለቲካ እየታየ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከዚህ አስተሳሰብ ወጥተን በሀገር ደረጃ የሚጨበጥ ለውጥ በማምጣት ልጆቻችን ከችግርና ጦርነት ተላቀው በሰላም እንዲኖሩ ማድረግ እንችላለን ነው ያሉት፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WMCC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to WMCC:

Share

Our Story

About Walta Information and Public Relations Center S.C. is a private media outlet and Public Relations Center established in 1994. Its major objective is playing significant roles in minimizing the gap of information flow in Ethiopia. Company Overview Walta Information and Public Relations Center S.C. is a private media outlet and Public Relations Center established in 1994. Its major objective is playing significant roles in minimizing the gap of information flow in the country. Accordingly, it has been gathering, organizing, analyzing and disseminating credible, accurate and balanced news and news genres. Besides, it has been providing public relations services since its reorganization, some three years back. The institution has also been contributing an immense role in peace building, democratization and sustainable economic development.