Borara media

Borara media neworld product and services I introduce the history of Ethiopia

ይህ ልጅ ህጻን ልጅ ደፍሮ ተሰውሮአል የሚኖርበትን አካባቢና የሚገኝበትን ስልክ የሚያወቅ  በፈጣሪ ተባበሩኝ ለፖሊስ ሙሉ ክስ ለመቅረብ እንዲመቸኝ ነው እባካችሁ ለፖሊስ ጠቁሚ አትበሉኝ መጀመሪ...
27/08/2026

ይህ ልጅ ህጻን ልጅ ደፍሮ ተሰውሮአል የሚኖርበትን አካባቢና የሚገኝበትን ስልክ የሚያወቅ በፈጣሪ ተባበሩኝ ለፖሊስ ሙሉ ክስ ለመቅረብ እንዲመቸኝ ነው
እባካችሁ ለፖሊስ ጠቁሚ አትበሉኝ መጀመሪያ እናንተ ድምፅ ሁኑልኝ
እሱ ስገኝ እንዴት እንደደፈራት እነግራቸዋለሁ
አመሰግናለሁ!

27/08/2026

I got over 1,050 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mame Mamela, Abdella Husen Guddeta, ሰይድ ኢብራሂም አሊ, Nati Ma...
25/08/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mame Mamela, Abdella Husen Guddeta, ሰይድ ኢብራሂም አሊ, Nati Man, የፈላስፎች መንደር, AbrHaley Webi, Abbaan Haqaa Rabbuma

Big shout out to my newest top fans! 💎 የፈላስፎች መንደርDrop a comment to welcome them to our community,  fans
22/08/2026

Big shout out to my newest top fans! 💎 የፈላስፎች መንደር

Drop a comment to welcome them to our community, fans

እነ ካሳዬ ቀነኒሳ 11 ሰዎች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዲያቸውን እንዲከለከሉ ታዘዘ።በአምቦ ከተማ "120" በተባለ በተደራጀ ቡድን ሰላማዊ ዜጎችን በማሰቃየት ...
19/08/2026

እነ ካሳዬ ቀነኒሳ 11 ሰዎች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዲያቸውን እንዲከለከሉ ታዘዘ።

በአምቦ ከተማ "120" በተባለ በተደራጀ ቡድን ሰላማዊ ዜጎችን በማሰቃየት ፣ በመደብደብ ፣ንብረት የመዝረፍ ወንጀል ተጠርጥረው በዐቃቢህግ መደበኛ ክስ የቀረበባቸው እነ ካሳዬ ቀነኒሳን ጨምሮ 11 ተከሳሾች በተከሰሱበት ተደራራቢ የወንጀል ክስ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ ተሰጠ።

ትዕዛዙን የሰጠው የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።

ችሎቱ የፍትህ ሂደቱን ለማፋጠን እንዲያስችል ታሳቢ በማድረግ በተረኛ ችሎት የዐቃቢህግ ማስረጃን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሸዋ ዞን ዐቃቢህግ ጽ/ቤት ከፖሊስ ጋር በመሆን ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ማጣሪያ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ አጠናቆ ከ15 ቀን በፊት በእነ ካሳዬ ቀነኒሳ 13 ተከሳሾች ላይ መደበኛ ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

እነዚህ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው ተከሳሾች

* 1ኛ ካሳዬ ቃነኒሳ ጉልቲ፣
* 2ኛ ታከለ ዳሮ ብሩ፣
* 3ኛ አብዲሳ ጉደታ ባይሳ፣
* 4ኛ ሃብታሙ አላማየሁ ጉታ፣
* 5ኛ አራርሳ ኑጉሴ ጉደታ፣
* 6ኛ ማንጌ ተፈሪ ቡልቱ፣
* 9ኛ ተከሳሽ ገመቹ ጂራታ መንገሻ፣
* 10ኛ ዲናሎ ወይም ጂፋር ቃበታ ደላንሳ፣
* 11ኛ ሮቤራ ወይም ፈራኦል ፍቃዱ እንዳቡ፣
* 12ኛ ቶኩማ ወይም ተመስገን ሞሲሳ ብልቡላ እና
* 13ኛ ተከሳሽ አበራ ኢቲቻ በንቲ ናቸው።

ሌሎቹ ማለትም 7ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ወይም (ነጻነት) ወንድሙ እና ፣ 8ኛ ተከሳሽ ነሞና ጉታ አራርሳ በሚመለከት በሌሉበት ነው ክስ የቀረበባቸው።

ተከሳሾቹ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) (ለ) አንቀጽ 35 እና አንቀጽ 671 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ መተላለፋቸው ተጠቅሶ ተደራራቢ የወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

በክስ ዝርዝሩ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾች 120 በሚል ስያሜ በቡድን በመደራጀት ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ በአንቦ ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በተለያዩ ጊዜያት በስልክ በመከታተል በመያዝ፣አካላዊ ድብደባ በመፈጸም በተለያዩ ግሮሰሪዎች ውስጥ ግለሰቦች በማሰቃየት፣ በማስፈራራትና በመደብደብ እያስፈራሩ በተለያዩ መጠኖች ገንዘብ በመቀበል የውንብድና ወንጀል በመፈጸም ንብረት በማውደም በተንቀሳቃሽ ምስል ይቀርጹ እንደነበረም በክሱ ላይ በዝርዝር ሰፍሯል።

በሌላኛው ክስ ደግሞ በ1ኛ ተከሳሽ ካሳዬ ቃነኒሳ ጉልቲ በተባለው ግለሰብ ላይ በቀረበ ክስ እንደተመላከተው ተከሳሹ የከተማ መሬት ሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 35 (1) (ለ) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ ከ2015 ዓ/ም በቁጥጥር ስር እስከ ዋለበት ጊዜ ድረስ በአንቦ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በአጠቃላይ 10 ሺህ ካሬ ሜትር የሚጠጋ ይዞታን በህገወጥ መንገድ በመያዝና ህገ ወጥ ግንባታ ማከናወን የሚል ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

በሌላኛው ክስ ደግሞ ይኸው 1ኛ ተከሳሽ ከተለያዩ ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማከናወኛ በሚል ከተጎጂዎች ገንዘብ ከወሰደ በኋላ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ይዞ በመሄድ “ይህ መሬት የእኔ ነው፣ ከተማዋ እየተቆጣጠርኩና እየገነባሁ ነው " በማለት ንብረታቸውን የወሰደ፣ጉዳት ያደረሰ መሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ በዐቃቢህግ በቀረበ 26 የክስ ዝርዝር ላይ የተከሳሾች ተሳትፎ ተጠቅሶ የቀረበ ሲሆን የሰው፣የሰነድ፣የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃን ከክሱ ጋር ተያይዞ ለችሎቱ አቅርቧል።

ተከሳሾቹ በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ቀርበው ክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸውና በንባብ እንዲረዱት ከተደረገ በኋላ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው ነበር

ዋስትና መፈቀድ አለበት ወይስ መፈቀድ የለበትም በሚለው የመከራከሪያ ነጥብ ላይ በዐቃቢህግ እና በተከሳሾች ጠበቃ በኩል ክርክር ተደርጓል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ያቀረቡት ዋስትና ጥያቄን ከቀረበባቸው ተደራራ ቢክስና ክብደት አንጻር ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የፍትህ ሂደቱን ለማፋጠን እንዲያስችል ታሳቢ በማድረግ በተረኛ ችሎት በተከሳሾች ላይ የዐቃቢህግ ማስረጃን ለመስማት ለነሃሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

የህግ የበላይነትን እናክብር፣እናስከብር

በየአካባቢያችን ወንጀሎችን በጋራ እንከላከል

ሰላም ለሀገራችን ይሁን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Addis Ababa Police




🌴🌴🌴

18/08/2026
ይሄኛውስ መቼ ነው የሚቀጣው?
18/08/2026

ይሄኛውስ መቼ ነው የሚቀጣው?

🔴 በአሜሪካ የ5 ዓመት ሕፃን ላይ የግብረ ሥጋ ድፍረት ፈጽሞ ህይወቷን ያጠፋው ወንጀለኛ በገዳይ መድኃኒት መርፌ ተገደለ።

በአሜሪካ አላባማ ግዛት፣ ካማሪ ሆላንድ የተባለች የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ላይ የግብረ ሥጋ ድፍረት ፈጽሞ ሕጿኗን በመግደሉ የተፈረደበት ጄረሚ ትሬማይን ዊሊያምስ የተባለ የ42 ዓመት ጎልማሳ ባለፈው በሞት ተቀጥቷል።

ካማሪ በ2021 ከጆርጂያ ኮሎምበስ ከተማ ከቤቷ ከጠፋች በኋላ ምርመራው ወደ አላባማ ፊኒክስ ሲቲ ተስፋፋ። ፖሊስ ዊሊያምስ በሚኖርበት ቤት ፍተሻ ሲያካሂድ የሕፃኗ እቃዎች ተገኝተዋል፤ በመጨረሻም አስክሬኗ ከሕንፃው ምድር ቤት ተገኝቷል።

በምርመራው መሠረት ሕፃኗ ከመገደሏ በፊት ታስራ የግብረ ሥጋ ድፍረት ተፈጽሞባት ነበር፤ በመጨረሻም በመታነቅ ሕይወቷን አጥታለች። በዊሊያምስ ስልክ ላይም ጥቃቱን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መገኘታቸው በፍርድ ሂደቱ ተገልጿል።

ዊሊያምስ እ.ኤ.አ በ2024 የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሲሆን ጥፋተኛ መሆኑን አምኖ የይግባኝ ሂደቶችን ለመተው በመምረጡ የተፋጠነ የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል። በዚህም ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ዕለት በገዳይ መድኃኒት መርፌ ተገድሏል።

የአላባማ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንደገለጸው፣ ዊሊያምስ ከዚህ በፊትም በሌሎች ሕፃናት ላይ ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን መናዘዙ ተገልጿል።

የዊሊያምስ ግድያ በተፈጸመበት በዚያው ሀሙስ ቀን በኦክላሆማ እና ቴነሲ ግዛቶችም ሁለት ሌሎች የሞት ፍርዶች ተፈጽመዋል።

በኦክላሆማ 70 ዓመቱ ካርሎስ ኩዌስታ-ሮድሪጌዝ እ.ኤ.አ 2003 ባለቤቱን ኦሊምፒያ ፊሸር በመግደሉ ሞት ተፈርዶበር ተገድሏል። የሞት ፍርዱ ከመፈጸሙ በፊት ከ20 ዓመታት በላይ ዘብጥያ ተወርውሯል።

በቴነሲ ደግሞ 66 ዓመቱ አንቶኒ ዳረል ሂንስ እ.ኤ.አ በ1985 ካትሪን ጄን ጄንኪንሰን የተባለች የ54 ዓመት የሞቴል ሠራተኛ በመግደሉ ተገድሏል። የሞት ቅጣቱ የተፈጸመው ወንጀሉ ከተፈጸመ ከ40 ዓመታት በኋላ ነው። ግለሰቡ ላለፉት 40 ዓመታት በእስር ቆይቷል።

በአሜሪካ ኦክላሆማ፣ ቴነሲ እና አላባማ በአንድ ቀን ሶስት የሞት ቅጣቶችን ተፈጽመዋል። ይህ በአሜሪካ ከረጅም ዓመታት በኋላ በአንድ ቀን ሶስት ግዛቶች የሞት ቅጣት ሲፈጽሙ የታየ ክስተት ሆኗል።

ለመጨረሻ ጊዜ ሶስት የአሜሪካ ግዛቶች በአንድ ቀን የሞት ቅጣት የፈጸሙት እ.ኤ.አ ጥር 7 ቀን 2010 ነበር። የ2026ቱ ክስተት ከ16 ዓመታት በኋላ የተደገመ ነው።

ሶስቱ የሞት ቅጣቶች በግዛቶቹ በተናጠል የተወሰኑ እንጂ በአንድ ላይ እንዲፈጸሙ ተቀናጅተው አልነበረም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

18/08/2026

ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!
አንተ ሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ
እባክህን
ማረኝ
አድነኝ
ባርከኝ
ስምህ ለዘላለም ብሩክ ይሁን
አመሰግናለሁ። አሜን!

18/08/2026

ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!
አንተ ሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ
እባክህን
ማረኝ
አድነኝ
ባርከኝ
ስምህ ለዘላለም ብሩክ ይሁን
አመሰግናለሁ። አሜን!!!

Address

Ethiopia
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Borara media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share