ዘርማ ጉራጌ

ዘርማ ጉራጌ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዘርማ ጉራጌ, Addis Ababa.

25/02/2025

ወልቂጤ ላይ ያሉት ትንኮሳዎች የመንግስት አካላት ትፈቱታለቹ ወይስ እኛ ዘርማዎች እንፍታው ባጭር ግዜ ልታሳውቁን ይገባል ከዚ በላይ አንታገስም በቃ

የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼድቅ ለምእመናን በሙሉ ለ2017 ዓ.ም አብይ ፆም   የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው...
23/02/2025

የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼድቅ ለምእመናን በሙሉ ለ2017 ዓ.ም አብይ ፆም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላለፉ።

የካቲት 16/2017 ዓ.ም(ወልቂጤ )

በፆሙ ወራት ምእመናን ከእህልና ውሃ ብቻ ሳይሆን ከክፋት ሁሉ በመጠበቅ ራሳቸውን ለፈጣሪ ማቅረብ እንዳለባቸው አባታዊ መልእክታቸውን ገልፀዋል።

ብፁህ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የ2017 የአብይ ፆምን አስመልክስተው ለምእመናን ባስተላለፉት መልእክት የአብይ ፆም ራሱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የፆመውና ዲያብሎስን ድል ያደረገበት ወቅት በመሆኑ ምእመናን ይህንኑ በማሰብ መንፈሳዊ በረከትን ለማግኘት ወራቱን በፆምና በፀሎት ማሳለፍ እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በፆሙ ወቅት ምእመናን ከእህልና ውሃ በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ይቅር በመባባል፣በመረዳዳትና በመተሳሰብና ሌሎች መንፈሳዊ ተግባራትን በማከናወን ከአምላካቸው ጋር ያላቸውን ቅርበት ማሳደግ እንዳለባቸው ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ተናግረዋል።

ከክፉ ተግባራት መራቅና መልካም ስራዎችን ማከናወን የሠዎች የሁልጊዜ ግዴታዎች ቢሆኑም በተለይ በፆም ወራት መሠል መልካም እሴቶችን የበለጠ መጎልበት ትልቁ የፆም አላማ መሆኑን ተናግረዋል ብፅዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ።

ይህንን በመገንዘብ ህዝብ ክርስቲያኑ በልዩ ትኩረት ፆሙን ሊያሳልፈው ይገባል ብለዋል።

ፆም ከመንፈሳዊ አስተዋፅኦ ባሻገር የህብረተሰቡን ማህበራዊ ግንኙነት ለማሻሻል ትልቅ ጥቅም ያለው በመሆኑ በተለይ ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ካላችበት አስቻገሪ ሁኔታ ተላቃ ሰላምና ፍቅር እንዲነግስ ከልብ መፆም ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

የታረዙትን በማልበስ ፣የተጠሙትን በማጠጣት፣የተራቡትን በማብላትና በሌሎችም አስቻጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመደገፍ ማሳለፍ የፆም ወራት ልዩ መገለጫዎች ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላም ሆነ ምእመናን በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ፆምና ከልብ የመነጨ ልመና ያስፈልጋል ያሉት ብፁህ አቡነ መልከ ጼድቅ በዚህም የነነዌ ሰዎች በመፆማቸውና በይቅርታ በመመለሳቸው ከጥፋት መዳናቸውን አውስተዋል።

ይህንኑ አብነት በማድረግ ፈጣሪያችን ይቅር እንዲለን ከልብ በመፆምና በመፀለይ ለፈጣሪ መቅረብ ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ ፦ ዘርማ ሚዲያ

ሰለሞን ባረጋ የሲቪያ ማራቶንን በአንደኝነት አጠናቀቀ።ሰለሞን ባረጋ ማራቶን የመጀመሪያ ውድድሩ ከሆን  2:05:19 በመግባት አሸናፊ ሆኗል።✅️2025 SEVILLA  MARATHON ⭐️SELEM...
23/02/2025

ሰለሞን ባረጋ የሲቪያ ማራቶንን በአንደኝነት አጠናቀቀ።

ሰለሞን ባረጋ ማራቶን የመጀመሪያ ውድድሩ ከሆን 2:05:19 በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

✅️2025 SEVILLA MARATHON ⭐️SELEMON BAREGA🇪🇹 DEBUT

15/02/2025
ልማት ልማት እያላቹ ትሰበስባላቹ  ከዛ ዙሪያቹ  በዛ ገንዘብ  ግፈኞች ትገዛላቹ የት ሄደ ያለ ሁሉ ይደበደባል መከራ ስቃይ አሳይታቹ   ከዛ ከተማ እንዲወጣ ታደርጋላቹ  እድሜ ልኩ አይልማ
04/02/2025

ልማት ልማት እያላቹ ትሰበስባላቹ ከዛ ዙሪያቹ በዛ ገንዘብ ግፈኞች ትገዛላቹ የት ሄደ ያለ ሁሉ ይደበደባል መከራ ስቃይ አሳይታቹ ከዛ ከተማ እንዲወጣ ታደርጋላቹ እድሜ ልኩ አይልማ

ሁኔታዋች ግን ምን እየሆኑ ነው
03/02/2025

ሁኔታዋች ግን ምን እየሆኑ ነው

27/01/2025

በአንድ እራስ ሁለት ምላስ ዳመ በለጠ #ጉራጌ #ጉራ #ጉራጌ

ይሄ መንገድ ተጨማሪ 80ቢሊዮን ወጪ ጠይቆ ነው ወይስ   መንገድ ስቶ ነው   የቆየው ይሄ  ሁሉ አመት
23/01/2025

ይሄ መንገድ ተጨማሪ 80ቢሊዮን ወጪ ጠይቆ ነው ወይስ መንገድ ስቶ ነው የቆየው ይሄ ሁሉ አመት

የእርዳታ ጥሪከሰሞኑ በዘገብነው ዘገባ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ፉቻሬ-44 ቀበሌ ልዩ ስሙ ኧባቃር በተባለ መንደር በተነሳ ድንገተኛ እሳት ቃጠሎ 11 ቤቶች ከነሙሉ ቤት ንብረታቸው መቃጠላቸውን ...
23/01/2025

የእርዳታ ጥሪ
ከሰሞኑ በዘገብነው ዘገባ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ፉቻሬ-44 ቀበሌ ልዩ ስሙ ኧባቃር በተባለ መንደር በተነሳ ድንገተኛ እሳት ቃጠሎ 11 ቤቶች ከነሙሉ ቤት ንብረታቸው መቃጠላቸውን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

ይህንን ተከትሎም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጎጂ አካላቱን መልሶ ለማቋቋም በወረዳው በኩል ህጋዊ እውቅና ያለው የገቢ ማሰባሰቢያ አካውንት እንዲከፈት ሲጠየቅ ነበር፡፡

የወረዳው መንግስትም ይህንን የህዝብ ጥያቄ ከግምት በማስገባት በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትና ታማኝነት ባላቸው ሶስት ግለሰቦች ስም የገቢ ማሰባሰቢያ አካውንት ከፍቷል፡፡

በዚሁ መሰረትም አካውንቱ የተከፈተው፦
1ኛ-መልስ አበሻ
2ኛ-ሀጅ ነስሩ ሳቢርና
3ኛ-አ/ቋድር አብድላ ስም ሲሆን አካውንት ቁጥሩም 1000673072465 (ንግድ ባንክ)መሆኑን እየገለፅን ከዚህ አካውንት ውጪ የሚደረግ የትኛውም እንቅስቃሴ ህገ-ወጥ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪ ያላችሁ የአካባቢው ተወላጆችና ባለሀብቶች፣ የዞናችንና በአጠቃላይ የሀገራችን ህዝቦች ለነዚህ ተጎጂ አካላት የአቅማችንን በማድረግ አለሁላችሁ እንድንላቸው ጥሪያችንን እናደርጋለን፡፡
የጌታ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፡፡

አትሻዶ ኮንሰርት በቲክቶክ  ቅዳሜ ጥር17/05/2017 ማንም እዳይቀር  ቤተሰቦች አደራ አደራ
21/01/2025

አትሻዶ ኮንሰርት በቲክቶክ ቅዳሜ ጥር17/05/2017 ማንም እዳይቀር ቤተሰቦች አደራ አደራ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251952471819

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዘርማ ጉራጌ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share