
21/09/2025
መልካም ዜና: ምርጥ የአእምሮ ቁርስ
ውድ የሕይወት ስጦታ
የዛሬ ቀንህ ውድ ስጦታ ነው፣ አመስግነው! 🙏
ጠዋት ስልካችሁን 🤳 ከማንሳታችሁ በፊት ለአፍታ ቆም በሉና ጥልቅ ትንፋሽ ወደ ውስጥ ውሰዱ፣ በቀስታም አውጡት። በአፍንጫችሁ ትንፋሽ ስላለና 🌬️ ዛሬ በሕይወት መኖራችሁን፣ በሰላም ማደራችሁን አስቡ።
በየቀኑ በአለማችን ከ300,000 በላይ ሰዎች፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ደግሞ ከ2,000 በላይ ሰዎች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፣ እኛ ግን ሌላ አዲስ ቀን ተሰጥቶናል። ☀️ ይህንን ቀን እንደ ውድ ስጦታ ተመልከቱት።
ከዛሬ ጀምሮ የጠዋት ልምዳችሁን ቀይሩ። በየቀኑ ጠዋት ለተሰጣችሁት ሕይወት፣ ለጤናችሁ፣ ለቤተሰባችሁ እንዲሁም ላላችሁት ፍቅር በልባችሁ ውስጥ ምስጋና አቅርቡ። ይህን ስታደርጉ በውስጣችሁ አዲስ የብርሃንና የደስታ ጉልበት ሲፈጠር ይሰማችኋል። እያንዳንዷን ቅጽበት በማስተዋልና በአመስጋኝነት ተጠቀሙበት።
"አመስጋኝ ሰው ሁልጊዜ የሚያመሰግንበትን ነገር ይጨመርለታል፤ የሚያማርር ሰው ደግሞ የሚያማርርበትን ነገር ይጨምርለታል"
ይህ ጥቅስ የሕይወታችንን አመለካከት አስፈላጊነት ያሳየናል። የምናተኩርበት ነገር የውስጣችንን ዓለም እንደሚቀርጸው ይነግረናል። ምስጋናን እንደ ልምድ ስንይዝ፣ ሁልጊዜም የምንደሰትበት ምክንያት እናገኛለን። በሌላ በኩል፣ ማማረርን ስንለምድ፣ ሁልጊዜም የምናዝንበት ወይም የምናማርርበት ነገር ላይ ተጨማሪ ሀሳቦችን እና ሁኔታዎችን እየፈጠርን የጭንቀታችንን መጠን እንጨምራዋለን። የሕይወታችን ጥራት የሚወሰነው በውስጣችን ባለው ምርጫና አመለካከት ላይ ነው።
የለቱ የመወያያ ጥያቄ፡-
ነገ ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ መጀመሪያ የምታመሰግኑት ነገር ምንድነው? ኮሜንት ላይ አካፍሉን።
ብርሃናችሁ ይብራ! ❣️
የበለጠ ውጤታማ እና የተሳካ ህይወትን ለመፍጠር የሚረዳዎትን የ21 ቀን የፓራዳይም ሺፍት ስልጠናችንን ይቀላቀሉ። ለበለጠ መረጃ እና ለመመዝገብ በስልክ ቁጥር +251 938 25 25 25 ይደውሉ።