Saja times ሣጃ -ታይምስ

Saja times ሣጃ -ታይምስ ለማህበረሰባችን ፈጣን ፣ተጨባጭ መረጃ ፤ ባህል እና የአከባቢ ፀጋን ለአለም ማስተዋወቅ

27/09/2025

Ayyaanni bara haaraa saba Yem , kan bara 2018 fulbaana 21 fii 22 godina yem magaalaa saajaa irratti kabajama
kottaa nu waliin ayyaaneffadhaa

26/09/2025
''ሄቦ''የየም ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል መስከረም 21-22 በደማቅ ሁነታ ይከበራል በዓሉን ለማድመቅ የየም ዞን አዲሱ ባህል ቡድን እና ጎኔር ኪነ-ጥበብ ቡድን ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ...
26/09/2025

''ሄቦ''የየም ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል መስከረም 21-22 በደማቅ ሁነታ ይከበራል በዓሉን ለማድመቅ የየም ዞን አዲሱ ባህል ቡድን እና ጎኔር ኪነ-ጥበብ ቡድን ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ነው ።
''ጎር ዎታውቶ''

ሳጅን ዳንኤል ሊጋባ ህልፈት እጅግ ልብ ሰባሪ ነው።  ነፍስህ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ከደጋጎች ጎን ያድርግ !!
26/09/2025

ሳጅን ዳንኤል ሊጋባ ህልፈት እጅግ ልብ ሰባሪ ነው።
ነፍስህ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ከደጋጎች ጎን ያድርግ !!

መስከረም 15 ‹‹ኢፍቱ›› የንጻት ወይንም የነጻነት ቀን!!በየም ብሔረሰብ መስከረም 15 ቀን "ኢፍቱ" ይባላል፡፡ይህ ዕለት በብሔሰቡ ዘንድ የነጻነት ቀን ተብሎ ይወሰዳል። የግልና የአካባቢ ፅ...
25/09/2025

መስከረም 15 ‹‹ኢፍቱ›› የንጻት ወይንም የነጻነት ቀን!!

በየም ብሔረሰብ መስከረም 15 ቀን "ኢፍቱ" ይባላል፡፡ይህ ዕለት በብሔሰቡ ዘንድ የነጻነት ቀን ተብሎ ይወሰዳል። የግልና የአካባቢ ፅዳት ዘመቻ የሚደረግበት ቀን ነው።

በዚህ ዕለት አሮገው ልብስ ይታጠባል።አሮገው አጥር በአዲስ አጥር ይተካል ወይም ይታደሳል። ደጅ ይጠረጋል፤ ቤቱ በኖራ ቀለም ይቀባል፡፡ ወጣቶች በነፃነት በመኖሪያ ቤት ግድግዳ ላይ የመልካም ምኞት ጽሁፎችን ይፅፋሉ፤አበባ ይስላሉ....ሴቶች እርስ በርስ ፀጉራቸውን ይሰራሉ።

በሌላ በኩል የሆድ ህመም እንዳይኖር እና ለሄቦ በዓል የተሰናዳውን ምግብ በደንብ ለመመገብ ፍላጎት እንዲጫምር የሚያደርግ የምግብ ዓይነት የሚበላበት ቀንም ነው፡፡ ይህ ምግብ ጎመንና ኖዕሜያ የተባለ የእጽዋት ቅጠል ተከትፎ በተፈረፈረ ቆጮ እና ቡላ የሚዘጋጅ (ዳኣ) በመባል የሚታወቅ ምግብ ነው።
መልካም በዓል

24/09/2025

መስከረም 14
"ካም ኬሳ››
የዕርቅ ስርዓት!

ይህ ስርዓት ከሄቦ ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ በየዓመቱ የሚፈጸመው መስከረም 14 ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ‹‹ካምኬሳ››ዕለት ይባላል። ይህ ቀን በቤተሰብም ሆነ በዘመድ አዝማድ መካከል የተፈጠረ ቅራኔና የሰነበተ ቂም ካለ በእርቅ ስርዓት አስፈጻሚ ‹‹ማግ››(ሽማግሌዎች) አማካኝነት የእርቀ ሠላም ስርዓት የሚፈፀምበት ቀን ነው።

በዚህ ቀን የሚደረግበት ምክንያት ቂም ይዞ ወደ አዲሱ አመት መሻገር ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለሚታመን ነው። በዚህም ምክንያት ቅራኔ ያለባቸው ግለሰቦች በዕለቱ በሽማግሌዎች ፊት ቀርበው ይቅር ተባብለው ይታረቃሉ።

ይቅርታ ለማድረጋቸው ምልክት ይሆን ዘንድ ሁለቱም ወገን የመስዕዋት ‹‹ማር›› ያቀርባሉ። የስርዓቱ አስፈጻሚ ‹‹ማግ››ማሩን በእሳት ለብ ባለ የእንሰት ቅጠል ይዘው እንዲቀምሱ ይደረጋል። በመጨረሻም ‹‹ቦርዴ››(የብሔረሰቡ ባህላዊ መጠጥ) በአንድ ዋንጫ በጋራ እንዲጠጡ(ሹማ) ያደርጋል። ይህ የሚሆነው ከአሁን በኃላ ታርቀናል፤በፍቅር በጋራ በአንድነት እንኖራለን ማለታቸውን ለማመላከት ነው፡፡

ምንጭ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ!

በ2025 በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸው የአፍሪካ ከተሞች በአፍሪካ የከተማ እድገት እና መስፋፋት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በኢኮኖሚ ፍላጎት የተነሳ መኖሪያቸውን በከተማ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ...
24/09/2025

በ2025 በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸው የአፍሪካ ከተሞች

በአፍሪካ የከተማ እድገት እና መስፋፋት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በኢኮኖሚ ፍላጎት የተነሳ መኖሪያቸውን በከተማ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይገኛል።

በተለይም በዋና ከተማዎች የሚገኝ መጠኑ ከፍ ያለ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ሰዎች ወደ ከተሞች እንዲሳቡ ማድረግ ስለመቻሉ የወርልድ ፖፑሌሽን መረጃ ይጠቁማል።

በዚህ የተነሳም ከሁለት ሚሊየን በላይ ነዋሪ ያላቸው የአፍሪካ ከተሞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ይገኛል።

ባለፉት አስርት አመታት እየታየ ያለው እድገት በፈረንጆቹ 1975 ከነበረው ቁጥር ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ነው።

በጊዜው በጣት የሚቆጠሩ የአፍሪካ ከተሞች 6 ሚሊዮን ነዋሪ በመያዝ ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት ግን 23 ሚሊዮን ነዋሪን በመያዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ የሆኑ ከተሞች በአህጉሯ መፈጠር ችለዋል።

ግዙፍ ከተሞች በስራ እድል ፈጠራ ፣ በመሰረተ ልማት ፣ በመኖሪያ ቤት እና በሌሎችም ከኢኮኖሚ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ያላቸው አቅም ከአጎራባች ትናንሽ ከተሞች እና ከገጠር አካባቢዎች ዜጎችን በመሳብ የነዋሪያቸው ቁጥር አድጓል።

ካይሮ፣ ኪንሻሳ እና ሌጎስ 17 ሚሊየን እና ከዛ በላይ ነዋሪን በመያዝ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ከሚጠሩት ከተሞች መካከል ናቸው።

የአፍሪካ ከተሞች እድገት እና የነዋሪዎች ቁጥር መጨመር ለስነ-ህዝባዊ አሰፋፈር እና ለኢኮኖሚ እድገት ሚናው የላቀ መሆኑ ይነገራል።

በዚሁ ልክ ይህ የህዝብ ቁጥር በትክክለኛው የከተማ ፖሊሲ ካልተመራ በመሰረተልማት ፣ በትራንስፖርት ፣ በመኖሪያ ቤት እና ሀይል አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው መረጃው ጠቁሟል።

ይህን የህዝብ ቁጥር ወደ ኢኮኖሚያዊ አቅም ለመቀየር ከተሞች በስራ እድል ፈጠራ እና በመሰረተ ልማት ላይ የሚከተሉት አካሄድ ወሳኝ መሆኑም ተነስቷል።

በ2025 በርካታ ነዋሪዎችን በመያዝ ከ23 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት የግብጽ መዲና ካይሮ ቀዳሚ ስትሆን፤ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎዋ ኪንሻሳ 17 ሚሊየን ነዋሪን በመያዝ ትከተላለች።

ሌጎስ ፣ ሉዋንዳ እና ዳሬሰላም ከሶስት እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ሲይዙ፤ አዲስ አበባ ከ5 ሚሊዮን 956 ሺህ በላይ ህዝብ መኖሪያ በመሆን 9ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

24/09/2025

ካሜ ከሳ
መስከረም 14 ቀን የእርቅ ቀን "ካሜ ከሳ" ባሳለፍነው ዓመት ውስጥ የተቀያየመ እና የተጣላ ሰው ቂም ይዞ ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር ስለሌበት የብሔረሰቡ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች ባሉበት ማር ቀርቦ እርስ በራሳቸው ይቅርታ አድርገው በዓሉን በሰላም በፍቅር ለማሳለፍ የእርቅ"ካሜ ከሳ"ሥነ-ሥርዓት ተካሂዶ ይውላል::
መልካም በዓል

በመስከረም ወር የሚከብሩ የብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት መካከል
23/09/2025

በመስከረም ወር የሚከብሩ የብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት መካከል

23/09/2025

አሚኒ ሄቦን ዎኖ ዙተቤኒም
የኟር ካልስዋ ዙተቤኒም

Great work
23/04/2024

Great work

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Saja times ሣጃ -ታይምስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share