Fazakiri ፋዛክር F

Fazakiri ፋዛክር F የሀ/ከ/እስልምና ጉዳዮች ቱላ እና አካባብ መስጅዶች የወጣቶች እና የሴቶች ምክር እና ዳዓዎ
Fazakirimedia

30/08/2026

የባሌ ሱልጣኔት፣የኑር ሑሴንና ሼኽ ሱፊ ዑመር ታሪክ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

በአሕመዲን ጀበል፣ከባሌ ሮቤ ከተማ።
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

ትናንትና ዛሬ በባሌ የነበርን ጉብኝት አስመልክቶ ስለባሌ ያልተነገሩ ታሪኮችን ከዚህ በፊት በ2ቱ የታሪክ መጽሐፍቶቼ ላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ምንጮችን በመጠቀም እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። መልካም ንባብ!

​«ባሌ» የሚለው መጠሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሑፍ የተመዘገበው በዛጉዌ ዘመነ መንግሥት ነበር። ቀደምት ከነበሩት የኢትዮጵያ እስላማዊ ሱልጣኔቶች መካከልም ባሌ አንዷና ዋነኛዋ ነበረች።

​እንደ አቡል ፊዳእ (1273–1331) እና ኢብኑ ፈድሉላህ አል-ዑመሪ (1348 የሞተው) ያሉ ዝነኛ ዐረብ የታሪክና መልክአ-ምድር ጸሐፍት በኢትዮጵያ ምድር ሰባት ሙስሊም መንግሥታት እንደነበሩ መዝግበዋል። (Ulrich Braukämper, 2003, Islamic History and Culture in Southern Ethiopia, p. 131)

​የባሌ ሱልጣኔት በሰሜን ከደዋሮ (የዛሬው አርሲ አካባቢ) እና ከሻርካ (ገደብ) ጋር ስትዋሰን፣ በምዕራብ ከሐዲያ፣ በምሥራቅ ደግሞ ከአዳል ሱልጣኔት ጋር ድንበር ነበራት።

​ግብጻዊው የታሪክ ምሁር ተቂይ አድ-ዲን አሕመድ አል-መቅሪዚ እንደ አአውሮፓ አቆጣጠር ሐጅ ለማድረግ በ836 ዓመተ ሂጅራ ሐጅ ወደ መካ ያቀኑትን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በማናገር በ1435 «አል-ኢልማም ቢ-አኽባር መን ቢ-አርድ አል-ሀበሻህ ሚን ሙሉክ አል-ኢስላም» (በሀበሻ ሀገር የነገሡ ሙስሊም ነገሥታት አጭር ታሪክ) በተሰኘው መጽሐፉ፣ በሀበሻ ምድር ከነበሩት ሰባት እስላማዊ ሱልጣኔቶች አንዷ ባሌ መሆኗን በዝርዝር አስፍሯል። (Al-Maqrizi: The Book of the True Knowledge of the Moslem Kings in Abyssinia, G. W. B. Huntingford Trans., p.7)

​የባሌ ሱልጣኔት የዛሬዎቹን ጎባ፣ ሲናና፣ ዲንሹ፣ አጋርፋ፣ ጋሴራ እና ጎሮን ያካተተ ሰፊ ግዛት የነበራት ሲሆን፣ ዋና ከተማዋም ከሮቤ በስተሰሜን ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቃ የምትገኘው «ዙላህ» እንደነበረች ይነገራል። (Terje Østebø, Localizing Salafism in Bale, Ethiopia, 2008, pp. 69–70)

​የኢብኑ ተይሚያህ ተማሪ የነበረው አል-ዑመሪ «መሳሊክ አል-አብሳር» በተሰኘው ታዋቂ ድርሳኑ እንደገለጸው፣ የባሌ ሱልጣኔት የሃያ ቀናት የእግር ጉዞ የሚያስኬድ የጎን ስፋትና የስድስት ቀናት የርዝመት ርቀት ነበራት። የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ይህንን ሲተነትኑት ግዛቱ ወደ 400 በ 120 ኪሎ ሜትር ወይም 48 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ያስረዳሉ። (Richard Pankhurst, 1997, The Ethiopian Borderlands, p. 71)

ይህ የባሌ ሱልጧኔት የቆዳ ሥፋት የዛሬን ኳታርና እስራኤል ግዛት ድምር ሰፊ ነው። ​በተጨማሪም ሱልጣኔቱ 18 ሺህ እግረኛና በርካታ ፈረሰኞችን ያካተተ ጠንካራ ሠራዊት ነበራት። (Braukämper, pp. 76–77)

​ሼኽ ኑር ሑሴን ባሌ
💢💢💢💢💢💢

​በቀደምትነት እስልምናን በባሌ በማስተማር ረገድ ሼኽ ሰዒድና ሼኽ ኢብራሂም የሚባሉ ዓሊሞች ቢጠቀሱም፣ ከ1200ዎቹ (ከ13ኛው ክፍለ ዘመን) ጀምሮ ግን እምነቱ ሥር እንዲሰድ ትልቁን ሚና የተጫወቱት ሼኽ ሑሴን ባሌ ነበሩ።
​በኋላ ላይ የሶፍ ዑመር ዋሻ በስማቸው ከተሰየመው ከደቀመዝሙራቸው ከሼኽ ሱፊ ዑመር አሕመድ ጋር በመሆን ባሌን የእውቀትና የዳዕዋ ማዕከል አደረጓት። (Braukämper, p. 83)

​ሼኽ ሑሴን ትምህርታቸውን የጀመሩት በአናጂና ነበር። ወዲያውም ከተለያዩ የባሌ አካባቢዎች ሰዎች ወደ እርሳቸው መጉረፍ ጀመሩ። ተመራማሪው ቴሪ ኦስቴቦ የአካባቢውን ትውፊት ዋቢ አድርገው እንደጻፉት፣ ተማሪዎች ከአናጂና ለስድስት ወራት ተቀምጠው ከተማሩ በኋላ ወደየቀያቸው ተመልሰው መስጊድና መድረሳ በመክፈት ያስተምሩ ነበር። (Østebø, pp. 65–66)

​የሼኽ ሑሴን የማስተማር ስልት ንድፈ-ሀሳብን ከተግባር ጋር ያዋሃደ ነበር። ተማሪዎቻቸው ለስድስት ወራት በኪታብ ደረጃ እውቀት ከቀሰሙ በኋላ ወደ ተግባራዊ ዳዕዋ ይሰማራሉ፤ በመስክ ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶችና ጥያቄዎች ይዘው ወደ መምህራቸው ይመለሳሉ። በእነዚያ ተጨባጭ ልምዶችና ሪፖርቶች ላይ ተመስርተው ለተጨማሪ ስድስት ወራት ጥልቅ ትምህርት ይቀስማሉ።
​ይህ የተቀናጀ ስልት ከፍተኛ ለውጥ በማምጣቱ እስልምና በባሌ ሕዝብ ዘንድ በፍጥነት ተቀባይነት አገኘ። ማኅበረሰቡም «የእውቀትና የእምነት ብርሃን አበሩልን» ሲል አክብሮታቸውን ገልጾ «ኑር ሑሴን» (የሑሴን ብርሃን) የሚለውን ስያሜ ሰጣቸው።

​የሼኽ ኑር ሑሴን ማንነት
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

​ከ1200 በፊት የሼኽ ኑር ሑሴን አያት የሆኑት ሼኽ ዐብደላህ ዐረቦችና ሶማሌዎች አብረው ከሚኖሩባት ከመርካ ከተማ በመነሳት በሶማሌ የባህር ዳርቻ ዳዕዋ ማድረግ ጀመሩ። ልጃቸው ሼኽ ኢብራሂም ዐብደላህም የአባታቸውን ፈለግ ተከትለው በማስተማር ወደ ሰሜን ምሥራቅ ባሌ ዘለቁ። (Braukämper, p. 135)

​«ኑር ሑሴን ባሌ» በመባል የሚታወቁት ታላቁ ዓሊም ሙሉ ስማቸው ሼኽ ሑሴን ኢብራሂም ዐብደላህ ይባላል። ከ800 ዓመታት በፊት በባሌ ምድር ያስተማሩት ሼኽ ሑሴን፣ በሕዝብ ዘንድ ያገኙት ተቀባይነትና ተጽዕኖ እጅግ የጎላ ነበር።
​ሼኽ ሑሴን አሕመድ፣ ሙሐመድ፣ ተማም፣ ሱለይማንና ዐብደላህ የተባሉ አምስት ወንዶችና አንዲት ሴት ልጅ ነበሯቸው።

ጥንታዊው የበላ መስጊድ
📶📶📶📶📶📶📶

በባሌ ምድር እጅግ አንጋፋ ከሆኑት ቅርሶች መካከል አንዱ በባሌ ከአናጂና በስተደቡብ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው «የበላ መስጊድ» ነው። ምንም እንኳ ዛሬ ፍርስራሹ ብቻ ቢታይም፣ በአካባቢው የትውፊት መረጃዎች መሠረት መስጊዱ የተገነባው ገና በ11ኛው ክፍለ ዘመን (በ1067 ዓ.ም አካባቢ) እንደነበር ይነገራል።

መስጊዱ በስፋቱ 40 በ40 ሜትር ሲሆን፣ ጣራውን ደግፈው የያዙ 14 ግዙፍ ምሰሶዎች (አምዶች) ነበሩት። በዚያ ዘመን እንዲህ ዓይነት ሰፊ ይዞታ ያለው መስጊድ መገንባቱ፣ በወቅቱ አካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ማኅበረሰብና የደራ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የነበረበት ማዕከል እንደነበር በግልጽ ያሳያል።

የሼኽ ሱፊ ዑመርና የዋሻው ታሪክ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የሶፍ ዑመር ዋሻ አስደናቂ የተፈጥሮ መስህብ ብቻ አይደለም፤ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በባሌ ምድር ለእስልምና መስፋፋት ትልቅ ድርሻ የነበረው የታሪክ ማዕከል እንጂ።

የሼኽ ኑር ሑሴን ባልደረባና የቅርብ ተማሪ የነበሩት ሼኽ ሱፊ ዑመር አሕመድ ዋሻውን ለብቻ ወደ ፈጣሪ የሚቃረቡበት (ኢዕቲካፍ የሚያደርጉበት)፣ ለተማሪዎቻቸው እውቀት የሚያስጨብጡበት እና ለዳዕዋ የሚያዘጋጁበት ስፍራ አድርገውት ነበር። በወቅቱ በርካታ ደቀመዛሙርት በዋሻው ውስጥ እየተማሩና እየሰገዱ በመውጣታቸው፣ ቦታው የእውቀትና የመንፈሳዊ ብርሃን መፍለቂያ ሆነ።

ለዚህም ነው ይሄ ታላቅ የተፈጥሮ ዋሻ ዛሬም ድረስ በሳቸው ስም «የሶፍ ዑመር ዋሻ» እየተባለ የሚጠራው።

የባሌ የጥጥ ሀብትና የንግድ መስመር
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የባሌ ሱልጣኔት ከታወቀችባቸው ዋነኛ የተፈጥሮ ጸጋዎች አንዱ ጥራት ያለው የጥጥ ምርቷ ነበር። የ14ኛው ክፍለ ዘመን የታሪክ ጸሐፊ ኢብኑ ፈድሉላህ አል-ዑመሪ እንደመዘገበው፣ በባሌ የሚመረተው ጥጥ ለዕለት ተዕለት ልብስ ስራ ብቻ ሳይሆን ለሰፊ የገበያ ልውውጥ ይውል ነበር።

ባሌ ከቀይ ባህርና ከህንድ ውቅያኖስ ጋር በሚያገናኘው በታዋቂው የዘይላዕ የንግድ መስመር ላይ በማረፏ፣ የጥጥ ምርቷን ጨምሮ እንደ ዝባድና የቀንድ ከብት ያሉ ውድ ሀብቶቿን ወደ ውጭ ገበያ በስፋት በማቅረብ ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅም መገንባት ችላ ነበር።

ሰባቱ ወንድማማች ሐጂዎች
✅✅✅✅✅✅✅✅

ከሼኽ ኑር ሑሴን ዘመን በኋላ በባሌ ምድር የዋቄፈና እምምነት በገነነበት ጊዜ በ18ኛ መጨረሻና በ19ኛ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ኢስላማዊ እውቀትና ዳዕዋ ዳግም እንዲያንሰራራ ትልቁን አሻራ ያሳረፉት «ሰባቱ ሐጂዎች» በመባል የሚታወቁት የዓሊሙ የሼኽ ዳዉድ ልጆች ነበሩ።

እነዚህ ሰባት ወንድማማቾች ኢልምን ከቀሰሙ በኋላ ሐጅ በመድረግ ከዚያ ሲመለሱ ወደ ተለያዩ የባሌ አካባቢዎች በመሰማራት፣ መድረሳዎችን በመክፈትና ማኅበረሰቡን በማስተማር የትውልድ ቅብብሎሹ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል።

እነርሱም ሐጂ ሺሃቡዲን፤ ሐጂ ሳዲቅ፣ ሐጂ ኢብራሂም፣ ሐጂ ዐሊ ባህር፣ ሐጂ አሚር፣ ሐጂ ሻሌ እና ሐጂ አሚን ናቸው።(Localizing Salafisim Religious Change among Oromo Muslims in Bale, Ethiopia, P.68 )

የኑር ሑሴን መካነ-መቃብር የዚያራ አጀማመር
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የባሌው የሼኽ ኑር ሑሴን መንደር ከነበረበት የቂርኣትና የእውቀት ማዕከልነት ወጥቶ ዛሬ ወደሚታወቀው የቀብር ዚያራና የበረከት ፍለጋ ስፍራነት የተቀየረው በ18ኛው መገባደጃ እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነው።

በ18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ (1783–1794 እ.ኤ.አ.) የሐረሩ አሚር ዐብዱ አል-ሻኩር በመካነ-መቃብሩ ግቢ ውስጥ በአብዱልቃድር ጄይላኒ ስም መስጊድ በማስገንባት በሐረርና በባሌ መካከል ጠንካራ ሃይማኖታዊ ግንኙነት ፈጠሩ።

ሆኖም በ1800 መጀመሪያ ላይ የአርሲው ሼህ አባስና የባሌው ሼኽ ሙሐመድ ቲሊማ ቲልሞ በህልም ሼኽ ሁሴን ባሌን በህልም "አየን" በማለት ወደ ሥፍራው ዚያራ አደረጉ።ሰዎችም የሼህ ሁሴንን ቀብር እንዲዘይር አበታቱ። ሆኖም በሂደት የስፍራው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ አቅጣጫውን እየቀየረ መጣ።

ይህ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ቅርጽ የያዘው የዚያራ ልማድ በዋናነት የሦስት ነገሮች ቅይጥ ውጤት ነበር፦

አንደኛ፣ በ13ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት የሼኽ ኑር ሑሴን ተማሪዎች በየስድስት ወሩ እውቀት ለመቅሰምና ሪፖርት ለማቅረብ ወደ አናጂና ያደርጉት የነበረው መመላለስ ከዘመናት በኋላ ወደ መቃብር ጉብኝት ተቀየረ።

ሁለተኛ፣ ማኅበረሰቡ ቀደም ሲል ወደ አባ ሙዳ ያደርገው የነበረው የኦሮሞ ባህላዊ የጉዞ ሥርዓት ከቀብር ዚያራው ጋር ተዳበለ።

ሦስተኛ፣ ከመቃብሩ በረከት ፍለጋ (ተበሩክ)፣ ስዕለት መሳልና መማጸን የመሳሰሉ ከእስልምናው የተውሒድ አስተምህሮ ያፈነገጡ ባዕድ ልማዶች በስፋት እየተቀላቀሉበት ሄዱ። ይህም ቀደም ሲል ለሼኽ ኑር ሑሴን ዱዓእ ከማድረግ ይልቅ እርሳቸውን ለመማጸን ወደ መዘየር ተለወጠ።

(Terje Østebø, Localizing Salafism: Religious Change among Oromo Muslims in Bale, Ethiopia, 2008, p. 144)

በሂደትም በአፄዎቹ ድጋፍና ማበረታቻ የአናጂናው ዚያራ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ እንደ አማራጭ «ሐጅ» እንዲቆጠርና ሰዎች ወደ መካህ ተጉዘው ሐጅ ከማድረግ ይልቅ የባሌውን የሼኽ ኑር ሑሴን ዚያራ እንደ ትልቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ እንዲወስዱት በርካታ ግፊቶች ተደርገዋል።

አጼ ኃይለ ሥላሴ የባሌ ኑር ሁሴንን ስፍራ በመጎብኘት፣ድጋፍ በማድረግና በዚያ ያሉትን ከግብር ነጻ በማድረግ አበረታተዋል።

በተጨማሪም የአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት "ሐጅ ከማል ሐጂ" ለተሰኘው ግለሰብ ድጋፍ በማድረግ ወደ መካና መዲና ጉዞ አድርጎ "የመካና መዲና ጉዞ ምስጢር" የተሰኘ መጽሐፍ እንዲጽፍ አድርጓል።በዚህ መጽሐፍ ላይ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ኑር ሁሴን ባሌ እያለለት ሐጅ መምጣት እንደሌለበት እንደገለጹ አድርጎ ጽፏል።ይህንን
እንዲህ ይገልጸዋል፡-

‹‹አረ ለመሆኑ /ታላቁ/ ነቢዩ ሙሐመድ ያሉትን /የተናገሩትን/ አንብበሃልን? በአገራችን ስንት ቅዱስ ሥፍራዎች እንዳሉስ ታውቃለህን? የአገራችንን እኮ ብናሳምረው የውጭ ዓለም እየመጣ /እየጎረፈ/ ሊጎበኘው ይችላል። ስለዚህ ሁለት ጥቅም ተገኘ ማለት አይደለምን? የአሩሲው ሰይድ ኑር ሁሴንን ታሪክና ዝና አወቅኸው? /ነቢዩ መሐመድ/ ኑር ሁሴንን የጎበኘ እኔን ጎበኘ ማለት ነው፤ እርሱን አልፎ የመጣ እኔንም እንዳለፈ ያህል ነው ብለዋል። እየተባለ ስለሚነገረው ተምረሃልን? ዳሩ እንደዚህ ያለውንና ራስን በራስ መቻልን መች ያስተምሯችኋል። የሃይማኖት ትምህርታችሁን በእናት አገራችሁ ብታጠናቅቁ፣ ይህን የመሰለው ባህላዊ ቁም ነገሮች መች /ያመልጣችሁ/ ይዘነጋችሁስ ነበር።››

(ሐጂ ከማል ሐጂ፣ የመካና የመዲና ጉዞ ምስጢር፣ ብርሃንና ሰላም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት የታተመ፣ ገጽ 28)
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
ፎቶግራፉን በባሌ በመገኘት ያነሳው ካሜራ ማን አሕመድ ነጋ ነው።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

የአሕመዲን ጀበል የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ! ሊንኩ ከሥር በአስተያየት መስጫው ስር ተጠቅሷል።👇
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

30/08/2026
22/08/2026
31/07/2026
29/07/2026

ሼይኽ መከተ ሙሄ በዛሬው እለት ወደ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነታቸው ከ20 ዓመታት በኋላ ዛሬ በመመለሳቸው የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ።
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

ሼህ መከተ ሙሄ ከ20ዓመታት በፊት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን በፕሬዝዳንት የመሩና በጊዜው በፍርድ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን መብት ላለማስነካት ብዙ ታግለዋል።በዚሁ ምክንያት ብዙ ዛቻ፣ማስፈራሪያና እንግልት የደረሰባቸው ሲሆን በድምጻችን ይሰማ ሂደትን የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ በማንሳታቸው በኢህአዴግ መንግስት በሐሰት በሽብር ተከሳው ቃሊቲና ቂሊንጦ ታስረው ዋጋ የከፈሉ ናቸው።

✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

የዛሬ ሃያ ዓመት ከፕሬዝዳንታቸው ስለተባረሩበት ሁኔታ በመስከረም 1998 የሠለፊያ ጋዜጣ እንዲህ ዘግቦት ነበር፣

«በነሐሴ 1997 የጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩትን ሐጅ መከተ ሙሔን አቶ ከማል በድሪ፣ አቶ አባይ ፀሐዬ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሻለቃህ ወርቅነህ ገበየሁ እና የደህንነት ባለስልጣናት በመጥራት በአዋጅ የተቋቋማ የሸሪዓ ፍ/ቤት በእስልምና ጉዳዮች (ኤንጂኦ) ስር እንዲገባ ፈርም ተባሉ፡፡ ሐጅ መከተ ሙሔ “የሙስሊሙን ህልውና አልሸጥም!” አሉ፡፡ “ያዘዝንህን አትቀበልምን?” ሲሉ ዛቻ የተሞላ ጥያቄ አቀረቡላቸው፡፡

ሐጅ መከተም “አዎ! የሙስሊሙን ህልውናና መብት ከምሸጥ ለማኝ ብሆን ይሻለኛል!” የሚል ምላሽ በመስጠታቸው አስብበት የሚል ማስፈራሪያ ሰጥተው ተለያዩ፡፡ በመስከረም 4/1998 በቢሯቸው ሳሉ ለሐጅ መከተ አንድ የደህንነት አባል መጥቶ “ትፈርማለህ አትፈርምም” ሲል ጠየቀ፡፡ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በስልክ “አልፈርምም ብሏል” ሲል ተናገረ፡፡

“ቢሮውን አሽግበትና አስወጣው!” የሚል ትዕዛዝ የተቀበለው ደህንነት ሐጅ መከተን አስወጥቶ ቢሮውን አሸገ፡፡መስከረም 5/1998 በአቶ ከማል በድሪ በተጻፈ ደብዳቤ መታገዳቸው ደረሳቸው፡፡ »(ሠለፊያ ጋዜጣ)

💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ እመኛለሁ።
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

Sheikh Makata Muhhee waggaa 20 booda gara aangoo Pirezidaantummaa Mana Murtii Waliigala Shari'aa Federaalaatti waan deebi’aniif, gammachuu guddaan natti dhaga'ame ibsuun barbaada.
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

Sheikh Makata Muhhee waggaa 20 dura Pirezidaantii Mana Murtii Shari'aa Federaalaa ta'uun kan tajaajilan si'a ta'u, mirga seeraan mana murtichaaf kenname eegsisuuf dhiibbaa fi giddudhuulummaa hedduu irra ga'e dura dhabatanii falmaniiru. Sababa kanaanis doorsisni, roorroon fi dararaa heddun irra ga'eera. Akkasumas soccho'iinsa "Dimtsachin Yisema" keessatti gaaffii uummata Muslimaa waan kaasaniif, mootummaa ADWUI'n yakka terorizimii sobaatiin hammatamanii manneen sirreessaa Qaallittii fi Qiillinxoo keessatti hidhamuun gatii ulfaataa kaffalaniiru.
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

Akkamitti waggaa dhibba dura (waggaa 20 dura) Pirezidaantummaa irraa akka ari'ataman Gaazexaan 'Salafiyyaa' Fuulbaana bara 1998 fiilbaana irratti akka gabaasetti:
«Hagayya bara 1997 Pirezidaantii Mana Murtii Shari'aa Waliigala Federaalaa kan turan Haajjii Makata Muhhee, Obbo Kamaal Badrii, Obbo Abbaay Tsahaayyee, Komishinara Poolisii Federaalaa Saalaqaa Warqineh Gabayyahuu fi qondaaltonni odeeffannoo fi eegumsa biyyaa (NISA) walitti waamuun, 'Mani Murtii Shari'aa seeraan dhaabbate kun dhiimma Islaamummaa (Kora Muslimoota/NGO) jalatti akka deebi’u mallatteessi' jedhaniin. Haajjii Makata nis, “Ani dhimma fi eenyummaa Muslimaa hin gurguru!” jedhanii didan. Isaanis doorsisaan “Wanta ajajamte hin fudhattuu?” jechuun gaaffii dhiyeessaniif.

Haajjii Makata ree, “Eeyyee! Eenyummaa fi mirga Muslimaa gurguruu irra kadhattuu ta'uu kootu naaf wayya!” jedhanii deebisaniif. Isaanis “Itti yaadi” jechuun doorsisanii addaan bahan. Fuulbaana 4 bara 1998 utuu waajjira isaanii keessa jiraniis, miseensi odeeffannoo fi eegumsa biyyaa tokko gara waajjira Haajjii Makata dhufees, “Ni mallatteessita moo hin mallatteessitu?” jedhee gaafate. Isaanis ree didani. Isinis bilbilaan “Hin mallatteessu jedheera” jechuun gabaase.

“Waajjira sana saamsii akka inni keessaa ba'u taasisi!” ajaja jedhu kan fudhate miseensi odeeffannoo fi eegumsa biyyaa sanaas Haajjii Makata waajjirachaa keessaa baasee balbala saamse. Fuulbaana 5 bara 1998 xalayaa Obbo Kamaal Badriin barreeffameen hojii irraa dhorkamuun isaanii isaan dhaqqabe.» (Gaazexaa Salafiyyaa)
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
Barri hojii garii fi milkaa'inaa akka isiniif ta'u hawwiin qabu ibsa.
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

ሼይኽ መከተ ሙሄ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ተሾሙ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሃምሌ 22 ቀን 2018 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በዚህም መሰረት በራሳቸዉ ፈቃድ መልቀቂያ ባቀረቡ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ምትክ በኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ተመልምለው የቀረቡ እጩዎችን በተመለከተ ጉባኤው ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት እንዲሁም ሼህ አብዱልመናን መሃመድ አህመድን የፌ/ጠ/ሸ/ፍ/ቤት ም/ፕሬዚደንት ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥቷል፡፡

አዲሶቹ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች ህዝበ ሙስሊሙ ከተቋሙ ሊያገኝ የሚገባውን ቀልጣፋ እና ተቋሙን የሚመጥን አገልግሎት እንዲሰጥ ታላቅ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል::

ለሼይኽ መከተ እና ለሼይኽ አብዱልመናን መልካም የሰራ ዘመን ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ

በዛው ኤለት ቀን 19/11/2018 ልዓ።በዛርው ኤሌት በቡርቃ ራሃማ ማስጅድ ውስጥ የወጣቶች እና የሴቶች ዳዓዎ እና ምክክር በሰላም ተካህዷለ።የሀዋሳ ከተማ እስልምናን ጉዳዮች ቱላ እና አካባብ...
26/07/2026

በዛው ኤለት ቀን 19/11/2018 ልዓ።
በዛርው ኤሌት በቡርቃ ራሃማ ማስጅድ ውስጥ የወጣቶች እና የሴቶች ዳዓዎ እና ምክክር በሰላም ተካህዷለ።

የሀዋሳ ከተማ እስልምናን ጉዳዮች ቱላ እና አካባብ መስጅዶች የወጣቶች እና የሴቶች ዳዓዎ እና ምክክር በመስጠት ላይ ትምህርት እየተሰጠ ያለው ሳምንታዊ ስልጠና ቀጥሏል በስልጠናው እንዲሳተፉ
የሙስልም ወጣቶች ዳዕዋ እና ምክክር በቡርቃ ማስጅድ ማስጅድ ራሃማውስጥ ተካህዷለ።

በመስጅድ አካባብና ውስጥ የወጣቶች ፂዳት በወር 1ግዜ እድሰጡ
ተሰምቷል
የቁርዓን ፕሮግራም በየቀኑ እንድኖር ስተለፈለገ ቁርዓንም እንድቀሩ ብዙ ወጣቶች ትኩረት አድርጉ ተሰምቷል

t.me/fazakiri

Fazakiri ፋዛክር

Address

Awassa
Addis Ababa
ADDES ABABA

Telephone

+955321809

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fazakiri ፋዛክር F posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share