
04/08/2025
ከ368ቱ ተጫዋቾች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ቀርቷል !
በ2004 የፖርቹጋል አውሮፓ ዋንጫ ከተጫወቱት 368 ተጫዋቾች ከአንዱ በስተቀር ሁሉም 367 እግር ኳስ አቁመዋል፡፡
16 ሀገራት በተካፈሉበት 12 ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አሁንም በመጫዎት ላይ ሚገኘው ብቸኛው ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ነው፡፡
በጊዜው19 ዓመቱ የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአሁን ሰዓት ለሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር እየተጫወተ ይገኛል፡፡
ከ21 ዓመት በፊት በተደረገው የአውሮፓ ዋንጫ በፍጻሜው ግሪክ አስተናጋጇ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመርያም ለመጨረሻም ጊዜ የአህጉሩን ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል፡፡
⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media