Sisay beatu

Sisay beatu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sisay beatu, Digital creator, sisaybesatu 30, Addis Ababa.

07/05/2026
13/04/2026

በሴፉ ፋንታሁን ሾው በነበረኝ ቆይታ የትውልድ መንደሬ መኪና እንዲያስገባ ማስጠረጌን ተከትሎ ቀጣይ ጠጠር የማስደፋት እቅድ እንዳለኝ ሳወራ የሰማች በለንደን ሐገር የምትኖር
እመቤት ንመታ የምትባል እህቴ ጠጠሩ ሲደፋ የምችለውን ድጋፍ አደርጋለው ብላ ቃል ገብታልኝ ነበረ። ይኸው በቃሏ መሰረት ዝግጅቷን ጨርሳለች ሙሉ የፕሮግራሙ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ፖስተሩን ይመልከቱ!! ለንደን የምትኖሩ የኔም የሷም ወዳጆች በእለቱ እንድትገኙ ስል በአክብሮት ጥሪዬን አቀርባለው!!!

09/04/2026
08/04/2026
28/03/2026

ከጉንችሪየ ለኢትዮጵያ የተበረከተው አዲስ አዳጊ ኮከብ

| እኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ደጅ ከረገጥኩበት እለት ጀምሮ ፣ እያስደመመኝ ነው።አስቀድሞ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ከደረሰ በኋላ ለኪነ ጥበብ ያለው ልዩ መሰጠትና ጉጉት ስላየሁ፣ ወደ ቢሮዬ ጠርቼው አናግሬው ነበር። የሰጠነው የተማሪዎች ካውንስል የህዝብ ግንኙነት ነበር።

ግቢው ራሱን ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ብዙ ነገሮች እንዳሉት በዚህም በዞኑ ውስጥ ያለውን አቅም በደንብ ለመጠቀም እንደሚረዳው፣ ዞኑም ይሁን ዩኒቨርሲቲው ከእርሱ የሚፈልጉት ብዙ ነገር እንዳለ ነግሬው ተስማምተን ተለያየን።

ቆይቶ ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለውድድር ማስታወቂያ ሲወጣ ስላላስቻለው መጥቶ ተወዳደረ። ተሳክቶለትም አለፈ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲአትር ት/ቤት ተቀላቀለ። በድጋሚ ወልቂጤ እንዲቀር ባሳምነውም በአገር ደረጃ ከፍ ያለ ነገር ሰርቼ ህዝባችንን ማስጠራት ይሻላል ነበር ያለኝ።

መልካም እድል ተመኝቼለት ተሰናበትን። አይደርስ የለ ፍረሽ ሆኜ ስድስት ኪሎ ስገባ እነ ፍርፍር ተራን ያስፎሸኝ እሱ ነው። ናኦድ አሁን የዩኒቨርሲቲዝ ከባድ የቲአትር ሰው የመድረክ መሪ እና አጋፋሪ ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደሞ ትልቁን የአገር ዋርካ በመድረክ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ድጌ ኮራሁበት። እናንተም ማንኛውም አይነት የጉራጊኛና የአማርኛ የመድረክ ስራ ሲኖራችሁ ደውላችሁ አሰሩት።በእርግጥም ትወዱታላችሁ። ተራእንረ ኧሰሞ!

ስልኩ: +251994691902

© Remedan Nürgeta

“ሄሮድስ ለልደቱ ቀን ለዘፈነችዋ ሴት የመንግሥቴን እኩሌታም ቢሆን እሠጥሻለሁ አላት:: ጌታ ሆይ እኔ ለአንተ ልደት ዘምሬያለሁ? ምን ትሠጠኝ ይሆን?" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ "ሦስት ነገሮች ያ...
07/01/2026

“ሄሮድስ ለልደቱ ቀን ለዘፈነችዋ ሴት የመንግሥቴን እኩሌታም ቢሆን እሠጥሻለሁ አላት:: ጌታ ሆይ እኔ ለአንተ ልደት ዘምሬያለሁ? ምን ትሠጠኝ ይሆን?" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ሦስት ነገሮች ያስደንቁኛል:: አባቱ የማይቀድመው ልጅ
፤ እናቱን የፈጠረ ሕፃን ፤ ፈጣሪዋን የወለደች እናት"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

"አፍሪካ ለአፍሪካውያን የመቃብር ስፍራ ብቻ ነች‼️" ፑቲን"አንድ የአፍሪካ ሰው ሀብታም ሲሆን የባንክ ሂሣቦቹን ወደ ስዊዘርላንድ ይልካል ፤ ለህክምና ወደ ፈረንሳይ ይጓዛል፤ ወደ ጀርመን ሄዶ...
06/01/2026

"አፍሪካ ለአፍሪካውያን የመቃብር ስፍራ ብቻ ነች‼️" ፑቲን

"አንድ የአፍሪካ ሰው ሀብታም ሲሆን የባንክ ሂሣቦቹን ወደ ስዊዘርላንድ ይልካል ፤ ለህክምና ወደ ፈረንሳይ ይጓዛል፤ ወደ ጀርመን ሄዶ ኢንቨስት ያደርጋል ፤ ምርቶችን ከዱባይ ይገዛል፤ የቻይና ቁሳቁስ ይጠቀማል ፤ እሱ በሮም ወይም በመካ ይጸልያል፤ ልጆቹ በአውሮፓ ይማራሉ ፤ ወደ ካናዳ፣ አሜሪካና አውሮፓ ሄደው ይጎበኛሉ::

ሲሞት በተወለደበት የአፍሪካ መንደር ውስጥ ይቀበራል:: አፍሪካ ለአፍሪካውያን የመቃብር ቦታ ብቻ ናት:: አንድ የመቃብር ስፍራ እንዴት ሊለማና ሊያድግ ይችላል? ”
ምንጭ- አዲስ አድማስ

Address

Sisaybesatu 30
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sisay beatu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share