Lula Gezu

Lula Gezu Welcome to Lula Gezu facebook fan page ** This is a creative/public content page, Not official.

ባለን መርካት!"ባለው ነገር ያልረካ፣ ሊኖረው በሚፈልገው ነገር አይረካም" (Wisdom Quotes)ትክክለኛ አባባል ነው! አሁን ባለን ነገር ረክተንና ደስተኞች ሆነን ካልተነሳን፣ እንዲኖረን ...
10/03/2026

ባለን መርካት!

"ባለው ነገር ያልረካ፣ ሊኖረው በሚፈልገው ነገር አይረካም" (Wisdom Quotes)

ትክክለኛ አባባል ነው! አሁን ባለን ነገር ረክተንና ደስተኞች ሆነን ካልተነሳን፣ እንዲኖረን የምንፈልገው ነገር እጃችን ቢገባም መርካትና ደስተኛ መሆን አንችልም፡፡

ሁሉም ነገር የሚጀምረው በቅድሚያ አሁን ባለን ነገር ከመርካት ነው፡፡ “እርካታ” ማለት አሁን በእጃችን ላይ ባለን ነገር ደስተኛ ለመሆን መወሰን ማለት ነው፡፡

ይህ አሁን በእጃችን ባለን ነገር በመርካትና ፈጣሪን በማመስገን የመጀመር ልምምድ፣ ያለንን እና የሌለንን ነገር እየቆጠርን የስሜት መዋዠቅ ውስጥ ከመግባት ይጠብቀናል፡፡

ባለን እንርካ፣ የሌለንን ለማሟላት ግን እንስራ!

ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ነች!አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ያደርጋታል፡፡ የአይሮፕላን በረራ አደገኛው፣ ለመከስከስ ተጋላጭ የሆነውና እጅግ ትልቅ ጥንቃቄ የሚስፈልገው ጊ...
10/03/2026

ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ነች!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ያደርጋታል፡፡ የአይሮፕላን በረራ አደገኛው፣ ለመከስከስ ተጋላጭ የሆነውና እጅግ ትልቅ ጥንቃቄ የሚስፈልገው ጊዜ ሁለት ነው፡፡

1) የመነሻው (የመጀመሪያ) ጊዜ፣

2) የማረፊያው (የመጨረሻው) ጊዜ፡፡

ማንኛውንም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ስትጀምሩ በጥንቃቄ አስባችሁበት ጀምሩ፡፡ በችኮላ፣ በመላ-ምትና በግድ የለሽነት የተጀመረ ነገር ለመከስከስ አደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ ትክክለኛ ነገር እየጀመርን እንኳን በጥንቃቄ ካላደረግነው ከአደጋው አናመልጥም፡፡

ማንኛውም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ወደማብቂያው እንደደረሰ ሲገባንና “ማሳረፍ” ስንፈልግም ታላቅ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ በስሜታዊነትና በችኮላ ነገሮችን ከማቋረጥ መጠንቀቅንና ስናቋርጠው ደግሞ በጥበብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ አሳርፉት እንጂ አትከስክሱት!

የተባረከ ምሽት ተመኘን🙏

 #ስኬት!✅በጃፓን ውስጥ በምትገኝ ትንሽ የገጠር መንደር ውስጥ ከደሃ ቤተሰብ ነው የተወለደው።ቤተቦቹ እሱን የማስተማር አቅም ስላልነበራቸው ገና በ9 አመቱ ትምህርቱን አቋርጦ ቤተሰቡን ለመደገ...
10/03/2026

#ስኬት!

✅በጃፓን ውስጥ በምትገኝ ትንሽ የገጠር መንደር ውስጥ ከደሃ ቤተሰብ ነው የተወለደው።ቤተቦቹ እሱን የማስተማር አቅም ስላልነበራቸው ገና በ9 አመቱ ትምህርቱን አቋርጦ ቤተሰቡን ለመደገፍ በአንድ ትንሽ ሱቅ ውስጥ በፅዳት ሰራተኝነት ተቀጠሮ መስራት ጀመረ።

✅ከትንሽ ጊዜ በኃላም በ አንድ የኤሌክትሪክ እቃዎችን በሚያመርት ድርጅት ውስጥ በቋሚነት ተቀጠረ።የአንፓልና ሶኬት ስራ ትኩረቱን ይስቡት ነበርና በየቀኑ ራሱን ያስተማርና ይመራመር ነበር።ሶኬትን ከቀድሞው አሻሽሎ መስራት ቢችልም በአሰሪው ድርጅት ተቀባይነት አላግኘም።'የማይረባ ስራ ነው።'ሲሉም አጣጣሉት። እሱ ግን በስራው እርግጠኛ ነበርና የራሴን ድርጅት መመስረት አለብኝ ሲል አሰበ።

✅ሃሳቡን ለጓደኞቹ አጫወታቸው 'አንተ ትምህርት አልተማርክም፣ልምዱም የለህም፣ገንዘብም የለህም።ውጤታማ ለማትሆንበት ስራ ብለህ ቋሚ የሆነውን ስራህን ባትተው ነው የሚሻልህ ይህን የእብድ ሃሳብህን ተው።'ሲሉ ተሳለቁበት።

✅የተማረ ባይሆንም፣ገንዘብ ባይኖረውም በራሱ ይተማመን ነበርና በ22 አመቱ የህይዎቱ ትልቁን ውሳኔ ወሰነ።በቋሚነት ከሚሰራበት ድርጅት ለቆ በትንሿ ቤቱ ውስጥ የእራሱን ድርጅት መሰረተ።ከሚስቱ ጋር በመሆንም አሻሽሎ የሰራውን ሶኬት በማምረት ቤት ለቤት እየዞሩ ለመሸጥ ሞከሩ ነገር ግን ቀላል አልሆነለትም።አንድም የሚግዛውም አላግኘም።ወራቶች አለፉ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ የሚገዛው ሊገኝ አልቻለም። የእለት ምግብ እጥተው የቤት እቃዎቻቸውን ሁሉ እስከመሸጥ ደረሰ።ህልሙን ፅልመት ሊውርሳት በተቃረበበት ወቅት አንድ ድርጅት 1000 ሶኬቶችን እንዲሰራ ትዕዛዝ ሰጡት።

✅ ከዛሬ 100 አመት በፊት በ1000 ትዕዛዞች የተጀመረው ድርጅት ዛሬ ላይ ከ250,000 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ያሉት ትልቅ ድርጅት ለመሆን በቅቷል። በ አመት 65 ቢሊዮን ዶላር ከሽያጩ ገቢ የሚያገኝ ድርጅትም ሁኗል።

✅ይህን ስኬት ያለምንም ትምህርትና ገንዘብ ማሳካት የቻለው ታላቅ ሰው 'konosuke Matsush*ta 'ይባላል።በትንሽ ቤት ውስጥ የተመሰረተው አሁን በመላው አለም ታዋቂና ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት የ 'panasonic company ' ባለቤት ነው።

✅ስኬት በትምህርት ደረጃ ወይም በገንዘብ መጠን ውስጥ ጥገኛ አይደለችም።ስኬት በራስ መተማመንን ትፈልጋለች።

✅ ' just believe in yourself,when no one else's does'

© Inspire Ethiopia

#ማስታወሻ :- ፅሁፉ እና ምስሉ ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም። ነገር ግን ለመግለጫነት እና ሳቢ ለማድረግ ብቻ የመጣ ምስል ነው።

Address

Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lula Gezu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share