South Ethiopia Regional Evangelical Churches Fellowship Office Arbaminch

South Ethiopia Regional Evangelical Churches Fellowship Office Arbaminch South Ethiopia Regional E/ C/F/Office Arbaminch የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000468138496
ብርሃን ባንክ: 1502150129555

🎉 የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት 50ኛ ዓመት የመሪዎች ዓመታዊ ስልጠናና የክብረ በዓል መርሐ ግብር በድል ተጠናቀቀ!ከደቡብ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህ...
18/07/2026

🎉 የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት 50ኛ ዓመት የመሪዎች ዓመታዊ ስልጠናና የክብረ በዓል መርሐ ግብር በድል ተጠናቀቀ!

ከደቡብ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት 12 ዞኖችን በመወከል በዚህ ታላቅ መርሐ ግብር ተገኝተን አክብረናል። ከቀደሙት ትውልዶች ተምረን፣ የወንጌልን አደራ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በአዲስ ብርታት ተነሳስተናል።

🙏 ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን!

#50ኛዓመት #ወንጌል #አንድነት #ደቡብኢትዮጵያ

13/07/2026

“ለኢትዮጵያ መንፈሳዊ እድገትና ለማኅበረሰብ ተስፋ የቆመ የአንድነት ተቋም” መጋቢ ዶ/ር ወንድማገኝ አስፋው

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ህብረቱ ባለፉት አምስት አስርት ዓመታት ወንጌልን በታማኝነት በማገልገል፣ አብያተ ክርስቲያናትን በአንድነት በማስተሳሰር እና ለሀገርና ለማኅበረሰብ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት የታላቅ ታሪክ ባለቤት ሆኗል።

ይህ ህብረት በቀደሙት አባቶች እምነት፣ ፅናትና መስዋዕትነት ላይ የተገነባ በመሆኑ፣ የብዙዎችን ሕይወት በወንጌል የለወጠ፣ ትውልዶችን ያነፀ፣ ታማኝ አገልጋዮችን ያፈራ እና በሀገራችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ልማት ውስጥ የማይተካ ሚና ተጫውቷል።

ከመንፈሳዊ ተልዕኮው ባሻገር፣ በሰብአዊ እርዳታ፣ በአደጋ ጊዜ ድጋፍ፣ በሴቶችና ወጣቶች አቅም ግንባታ፣ በሕፃናት አገልግሎት፣ በጤናና በማኅበራዊ ንቃተ ህሊና ሥራዎች በመሳተፍ ለማኅበረሰቡ ተስፋ፣ ሰላምና በረከት የሆነ የእምነት ተቋም ሆኖ ቆይቷል።

50 ዓመታት ያስመዘገበው ታሪክ ያለፈውን የሚያስታውስ ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ለቤተ ክርስቲያን፣ ለሀገር እና ለመጪው ትውልድ የበለጠ ተስፋና አገልግሎት የሚገነባበት ጠንካራ መሠረት ነው።

“የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ባለፉት 50 ዓመታት የወንጌልን እውነት በጽናት ጠብቆ፣ የቤተክርስቲያንን አንድነት አጠናክሮ፣ ማኅበረሰቡን በተግባራዊ ፍቅር በማገልገል ለኢትዮጵያ የማይረሳ አሻራ ያሳረፈ የእምነት፣ የተስፋ እና የአንድነት ምሰሶ ነው።

እግዚአብሔር የጀመረውን መልካም ሥራ ወደ ፍጻሜ ያድርሰው፤ ህብረቱም ለቤተ ክርስቲያን፣ ለሀገራችን እና ለዓለም ሕዝቦች የበረከት ምንጭ ሆኖ ይቀጥል።”

መጋቢ ዶ/ር ወንድማገኝ አስፋው
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ጸሐፊ

የህብረቱን ማሕበራዊ ሚዲያዎች በመቀላቀል አዳዲስ መረጃዎች ይከታተሉ።
You tube;- https://www.youtube.com/-et
tiktok;- https://www.tiktok.com/
Telegram;- https://t.me/ECFEmaterial
Follow እና Share ስለምታደርጉ እናመሰግናለን

06/07/2026
ደረሰ ደረሰ ደረሰ 🔥🔥🔥የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል እና የመሪዎች ኮንፍራንስ ቀን ደረሰ።ከመስከረም 4 ቀን 1968 ዓ.ም የጀመረ...
06/07/2026

ደረሰ ደረሰ ደረሰ 🔥🔥🔥

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል እና የመሪዎች ኮንፍራንስ ቀን ደረሰ።

ከመስከረም 4 ቀን 1968 ዓ.ም የጀመረው የሕብረቱ ጉዞ ከሐምሌ 7 - 10, 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አራዳ ፓርክ 50ኛ ዓመቱን ልናከብር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውናል።

በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አደረሰን

የህብረቱን ማሕበራዊ ሚዲያዎች በመቀላቀል በእለቱ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን ይከታተሉ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩና የመጋቢያን ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነውየኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት (ECFE) የተመሠረተ...
16/06/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩና የመጋቢያን ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት (ECFE) የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ ክብረ በዓል እና የ2018 ዓ.ም የመጋቢያን ኮንፈረንስ ከሐምሌ 6 እስከ 9 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ኅብረቱ የዝግጅቱን ዝርዝር መረጃ በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል።

በመግለጫው መሠረት፣ 50ኛው ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል የኅብረቱን የ50 ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ፣ ያለፉ ዘመናት አስተዋጽኦዎች እና የወደፊት የአገልግሎት አቅጣጫዎችን ለማስታወስና ለማክበር የሚያገለግል መሆኑ ተገልጿል።

በ9 ቤተ እምነቶች የተመሠረተው ኅብረቱ በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የወንጌል አማኝ ቤተ እምነቶችን በአባልነት አቅፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ እያገለገለ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የ2018 ዓ.ም የመጋቢያን ኮንፈረንስ መጋቢያንን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት፣ በአገልግሎት ልምድ ልውውጥ፣ በመሪነት እና በመንፈሳዊ ዕድገት ለማጠናከር የተዘጋጀ መርሃ ግብር መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ደረጀ ታፈሰ በመግለጫቸው፣ “ይህ የወርቅ ኢዩቤልዩ ክብረ በዓል ባለፉት 50 ዓመታት በጋራ የረዳንንና የመራንን እግዚአብሔር የምናመሰግንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዝግጅቱ ወቅት ለኅብረቱ እድገትና መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ቀደምት አባቶች፣ መሪዎች እና አገልጋዮች ልዩ ዕውቅናና ክብር እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ እንግዶች፣ መጋቢያን፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።

ይህ ታሪካዊ የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ ክብረ በዓል እና የመጋቢያን ኮንፈረንስ የኅብረቱን ያለፉ ዓመታት ስኬት በማስታወስ ለቀጣይ ትውልድ የአገልግሎት ራዕይና አቅጣጫ የሚያሳይ ወሳኝ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።

Evangelical Churches Fellowship of Ethiopia (ECFE)
50 Years of Unity, Service and Gospel Witness

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በፕሮፌሰር ክሬግ ኪነር የተለገሱ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበረከተግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብ...
03/06/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በፕሮፌሰር ክሬግ ኪነር የተለገሱ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበረከተ

ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በታዋቂው የነገረ መለኮት ምሁር ፕሮፌሰር ክሬግ ኪነር የተለገሱ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በይፋ አስረከበ።

በርክክቡ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ፓስተር ደረጀ ታፈሰ እንደገለጹት፣ እነዚህ መጻሕፍት በፕሮፌሰር ክሬግ ኪነር የተጻፉ ሲሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ያላቸውን መልካም ምኞት በሚገልጽ ጽሑፍና በግል ፊርማቸው የተሸለሙ ናቸው።

ፓስተር ደረጀ በንግግራቸው፣ እነዚህ መጻሕፍት በአገር ውስጥ በቀላሉ ለግዥ የማይገኙ በመሆናቸው፣ በአንድ ማዕከላዊ ስፍራ ተሰብስበው ቢቀመጡ ለብዙ አጥኚዎች፣ ተማሪዎችና አንባቢያን ትልቅ ጥቅም እንደሚያስገኙ ገልጸዋል። አክለውም፣ እውቀት ያለው ትውልድ ለአገር እድገት ወሳኝ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ጠቅሰው፣ ኅብረቱ በዚህ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል።

እንዲሁም መጻሕፍቱን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የስጦታው መሳካት እንዲቻል ላደረጉት ጥረት ዶክተር ፈቃደ አመኑን ከልብ አመስግነዋል።

በበኩላቸው ዶክተር ፈቃደ አመኑ፣ መጻሕፍቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑ የነገረ መለኮት ምሁር የተጻፉ በመሆናቸው፣ ለተለያዩ የእምነት አመለካከቶች ያላቸው ምሁራንና ተመራማሪዎች የጥናት ሥራቸውን ለማገዝ ጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። አብርሆት ቤተ መጻሕፍት ለሁሉም ክፍትና ተደራሽ መሆኑ ስጦታው እዚያ እንዲቀመጥ ምክንያት እንደሆነም አብራርተዋል።

ዶክተር ፈቃደ አመኑ አክለውም፣ ይህ የመጻሕፍት ስጦታ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንዳልሆነ፣ ወደፊትም ተጨማሪ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ለማበርከት ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ታሪኩ፣ ለተደረገው ውድ የመጻሕፍት ስጦታ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ በቤተ መጻሕፍቱ ስም ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት እና ለፕሮፌሰር ክሬግ ኪነር የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

ይህ የመጻሕፍት ስጦታ በኢትዮጵያ የእውቀት ልማትን፣ የምርምር ባህልን እና የንባብ ተደራሽነትን ለማጠናከር የሚያግዝ ጠቃሚ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

🚨 የታላቅ መንፈሳዊ ጥሪ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እድል! 🚨📖 “እኛም አንድ እንደሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ”— ዮሐንስ 17፡21የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕ...
02/06/2026

🚨 የታላቅ መንፈሳዊ ጥሪ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እድል! 🚨

📖 “እኛም አንድ እንደሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ”
— ዮሐንስ 17፡21

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ጽ/ቤት (SER-ECF) በክልሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋፋት፣ ወንጌልን ለማዳረስ፣ መሪዎችን ለማብቃት፣ ሰላምን ለማጠናከር እና ማህበረሰብን ለመለወጥ በትጋት እየሰራ ይገኛል።

👉 ይህን ታላቅ ራዕይ በጋራ ለማሳካት ጊዜዎን፣ እውቀትዎን እና ሙያዎን ለእግዚአብሔር ሥራ ለማዋል የምትፈልጉ ክርስቲያኖች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ ተማሪዎች እና የአገልግሎት መሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት እንዲቀላቀሉን እንጋብዛለን።

💼 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፎች

🌍 ወንጌልና ተልዕኮ

👥 የማህበረሰብ ልማትና እንክብካቤ

🧒 የሕፃናትና ወጣቶች አገልግሎት

📚 የአመራር ስልጠናና አቅም ግንባታ

📸 ሚዲያ፣ ኮሙዩኒኬሽንና ዲጂታል አገልግሎት

🗂️ ጥናት፣ ምርምርና መረጃ አሰባሰብ

🕊️ የሰላም ግንባታና እርቅ

📋 የኮንፈረንስና ዝግጅቶች ማስተባበር

💻 የቢሮ አስተዳደርና ድጋፍ

🤝 አጋርነትና የሀብት ማሰባሰብ

💙 ለምን ይቀላቀሉ?

✅ በክልሉ የሚፈጠር መንፈሳዊና ማህበራዊ ለውጥ አካል ይሆናሉ

✅ የአመራርና የአገልግሎት ልምድ ያገኛሉ

✅ ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር ይገናኛሉ

✅ ይፋዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምስክር ወረቀት ያገኛሉ

🚀 አሁኑኑ ይመዝገቡ!

🔗 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScpf4q2tXRL2u9MXw7FPhfb6FAfruxx-4x80WodxycG0daPIw/viewform

📍 አርባ ምንጭ፣ ኢትዮጵያ

📧 [email protected]

📞 +251 91 157 5204
📞 +251 91 661 8105

📖 “ለጌታ እንደሚገዛ ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።”
— ቆላስይስ 3፡23

Win Souls for God Evangelical Ministries
ወጣት ለክርስቶስ Youth for Christ
Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ
Christian Generation

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት  የሥራ አመራር ቦርድ ወቅታዊ መግለጫክቡራን የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት መሪዎች ፣ አባል ቤተእምነቶች...
25/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የሥራ አመራር ቦርድ ወቅታዊ መግለጫ
ክቡራን የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት መሪዎች ፣ አባል ቤተእምነቶች ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ዛሬ የምናቀርበው መልእክት የተለመደ አይደለም፤ ነገር ግን እውነትን ለመናገር የሚጠይቅ ጊዜ አሁን በመሆኑ ።
”እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።” (ዮሐንስ 8:32)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የሥራ አመራር ቦርድ፣ በክልሉ ውስጥ የወንጌል አንድነትን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ አስተምህሮን እና መንፈሳዊ ታማኝነትን ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ይታወቃል ።
በሌላ በኩል መንግስት የወንጌል አማኞች ራሳቸውን እንዲያስተዳደሩ ባወጣው በአዋጅ ቁጥር 1208/2012 የካውንስሉ አባል እና መስራች በመሆን በካውንስሉ እየተሳተፍን እንገኛለን፡፡
በቅርቡ ግን፣ በክልሉ ውስጥ ከአንዳንድ የካውንስል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሪዎች ጋር በተያያዘ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች፣ ከመንፈሳዊ መመሪያዎች፣ ከሕጋዊ አሰራሮች እና ካውንስሉ ከተመሰረተበት መሠረታዊ ዓላማ ጋር የማይጣጣሙ መሆናቸው የክልሉ ህብረት ሥራ አመራር ቦርድ ደርሰበታል።
የታዩ ዋና ዋና ግድፈቶች
1. የአደባባይ ኮንፍራንሶችን የማስፋፋት እንቅስቃሴዎች
2. የቤተክርስቲያናት እና የመንፈሳዊ ህብረቶችን ተልዕኮና ሚናን የሚተኩ ድርጊቶች መፈጸም
3. የህብረቱን እሴት እና ቁሳዊ ጥቅም የሚነኩ ድርጊቶችን መፈፀም
4. በአባል ቤተ እምነቶች እና ህብረቶች ላይ የሚደረጉ ጫናዎች እና ጣልቃ ገብነቶች
5. ፍትሃዊነት የጎደላቸው የካዉንስሉ የምርጫ ሂደቶች
እነዚህ ሁኔታዎች ካውንስሉ ከተመሰረተበት ዓላማ ያፈነገጡ አሰራሮች መሆናቸውን ደርሶበታል፡፡ በተጨማሪም የክርስቲያናዊ አንድነትን የሚያደናቅፉ፣ የእምነት ግልጸኝነትን የማይወክሉ እና የተቋማትን እምነት የሚሸረሽሩ መሆናቸውን ያሳያል።

በመሆኑም የሥራ አመራር ቦርዱ የሚከተሉትን ውሳኔዎች እና ጥሪዎች ያቀርባል፦
1. በካዉንስሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚደረጉ የአደባባይ ኮንፍራንሶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ
2. የቤተክርስቲያናት እና የመንፈሳዊ ህብረቶችን ተልዕኮ ሚናን የሚተኩ ድርጊቶች ከመፈጸም እንዲቆጠቡ
3. የወ/አ/ህብረት ንብረቶችን ወደ ካዉንሉ ለማዛዋወር የሚደረጉ እንቅስቀሴዎች ካዉንስሉ ከተመሠረተበት አዋጅ ጋር የሚጸረር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆሙ
4. በአባል ቤተክርስቲያናት ላይ የሚደረጉ ጫናዎችና የተሳሳተ መረጃ ስርጭት እንዲታረም
5. ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና አካታች የምርጫ ሂደት በክልሉ ሥር ባሉ ዞኖች እና የወረዳ ህብረቶች እንዲካሄድ
ሁሉም አካላት የካውንስሉን መመሪያዎች፣ የተቋሙን ደንብ እና የሥነ-ምግባር መመሪያዎችን በጥንቃቄ እንዲከተሉ ጥሪ እናቀርባለን
የሥራ አመራር ቦርዱ ሁሉም አካላት በሰላም፣ በውይይት እና በሕጋዊ መንገድ ያሉ ችግሮችን እንዲፈቱ ይጠይቃል።
የወንጌል አንድነትና የክርስቲያናዊ እሴቶች ጥበቃ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ይገነዘበል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የሥራ አመራር ቦርድ

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ክልላችንን ይባርክ!

ሚያዚያ 27 / 2018 ዓ.ም
አርባምንጭ

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

አሊያንስ ኮሌጅ  ለጥያቄው መልስ መስጠቱን  አሳወቀ።
22/05/2026

አሊያንስ ኮሌጅ ለጥያቄው መልስ መስጠቱን አሳወቀ።

Address

Arbaminch
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Regional Evangelical Churches Fellowship Office Arbaminch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share