
23/06/2025
የካራቴ ስፖርት በአማራ ክልል የበላይነት ተጠናቀቀ።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም (Ethio press) በ6ኛው የመላው ኢትዮጰያ ጨዋታዎች የአማራ ክልል በጅማ ከተማ በካራቴ ስፓርት ደምቋል።
ሁለት አሰልጣኝ እና 16 ወንድና 10 ሴት የስፖርቱ ተፋላሚዎችን ይዞ ክልሉ ጅማ ከትሟል።
በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል መካከል የአጠቃላይ አሸናፊ ለመኾን የነበረው ፍጥጫ በመጨረሻም በአማራ ክልል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ዛሬ አሸናፊውን የሚለዩ በሁለቱም ጾታ የቡድን ውድድሮች ተደርገዋል። በወንድ የቡድን ፋይት ውድድር ተጠበቂ የነበረ ነው። ሁለቱም ክልሎች አራት አራት የወርቅ እና ተጨማሪ ሜዳልያዎችን ይዘው ለፍጻሜው በቅተዋል።
ይሄንን የፍጻሜ ውድድር አማራ ክልል በብርቱ ልጆቹ በማሸነፍ የበላይ ኾኗል። በሴቶቹ የቡድን ፋይት የነሐስ ሜዳልያ አግኝተዋል። ውጤቱን ተከትሎም የካራቴ ስፖርት ውድድርን የአማራ ክልል አሸንፏል።
አማራ በ5 ወርቅ 4 ብር እና 5 ነሐስ ቀዳሚ ኾኗል። ኦሮሚያ 4 ወርቅ፣ 4 ብር እና 3 ነሐስ ሁለተኛ ሲኾን ድሬደዋ 2 ወርቅ፣ 2 ብር እና 8 ነሐስ በመሰብሰብ ሦስተኛ ኾነው አጠናቅቀዋል። አዲስ አበባ፣ ቤንሻንጉል፣ አፋር፣ ሲዳማ እና ጋምቤላ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃ በማግኘት አጠናቅቀዋል።