Prosperity For All

Prosperity For All News

የጀግና ልጅ የሚያስታውስ ለትላንት ዛሬ የሚያመሰግን ትውልድ ተፈጥሯል፣ ታሪክ አይረሳም!የኢትዮጵያ ኩራትና የጀግንነት ተምሳሌት የሆኑት የኮሎኔል አብዲሳ አጋ ልጅ አቶ ኤልያስ፣ አባታቸው ደምና...
06/01/2026

የጀግና ልጅ የሚያስታውስ ለትላንት ዛሬ የሚያመሰግን ትውልድ ተፈጥሯል፣ ታሪክ አይረሳም!

የኢትዮጵያ ኩራትና የጀግንነት ተምሳሌት የሆኑት የኮሎኔል አብዲሳ አጋ ልጅ አቶ ኤልያስ፣ አባታቸው ደምና አጥንታቸውን በገበሩላት ሀገር ውስጥ የመኖሪያ ቤት አጥተው መቸገራቸው የታሪክ ጠባሳ ሆኖ ቆይቷል።

ሆኖም ግን፣ ይህንን የቆየ የፍትህ እጦት ተረድተው ለጀግናው ልጅ የመኖሪያ ቤት ከሙሉ የቤት እቃዎች ጋር እንዲሰጣቸው ያደረጉት የከንቲባዋ ተግባር እጅግ የሚደነቅና "ለባለውለታዎቻችን ክብር እንሰጣለን" የሚል ታላቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው።

ይህ እርምጃ የከንቲባዋን አስተዋይ አመራር ከማሳየቱም በላይ፣ ለኦሮሞ ህዝብና ለሀገር ባለውለታዎች ያላቸውን ጥልቅ ተቆርቋሪነትና አክብሮት በተግባር ያረጋገጠ ነው።

ጀግኖቻችንን በህይወት እያሉ ማክበርና ቤተሰቦቻቸውን መንከባከብ የሀገር አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር በመሆኑ፣ ለተደረገው መልካም ስራ ምስጋናችን የላቀ ነው።

06/01/2026

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

“ዘንድሮ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የምናከብረው የተነገረው የተስፋ ቃል መድረሱን፣ የለውጥ ብርሃን መፈንጠቅ መጀመሩን፣ የመሻገር ዘመን መቅረቡን እያመንን ነው። ጉዟችን በውጣ ውረድ የተሞላ ነበር፤ ተስፋ አስቆራጭ መከራዎችን አስተናግደናል። ከእንግዲህ ፈተናው ጨርሶ አይጎበኘንም ባንልም፣ ተስፋችን የሚወለድበት የዋዜማው ዕለት ላይ ደርሰናል። የፍዳው ዘመን ላይመለስ ተሸኝቶ፣ የማንሠራራት ዘመን እንደመጣ በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን።”
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ደ/ር ዐቢይ አህመድ

በዓሉን ስናከብር የፍቅር መገለጫ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ በማድረግ የተቸገሩትን በማሰብ እና በመርዳት ፍቅርን በመግለጥ ይሁን።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት ይሁንላችሁ።

በድጋሚ መልካም የልደት በዓል ይሁንልን!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Baga ayyaana guyyaa dhaloota gooftaa Iyyasuusiin nagaan isin gahe!

"Ayyaana guyyaa dhaloota Gooftaa Iyyasuus baranaa kan kabajnu jechi waadaa dubbatame gahuu, ifti jijjiiramaa mul'achuu eegaluun barri cehuumsaa dhihaachuu amanaati. Imalli keenya bu'aa bahiin kan guutame ture, qormaatilee abdii kutachiisan keessummeessineerra. Kana booda goonkumayyuu qormaatni nu hin daawwatu jechuu dhiisunus abdiin keenya kan itti dhalatu guyyaa jala bultii irra geenyeerra. Barri qoruumsa akka hin deebinetti gaggeeffamee, barri olka'iinsaa akka dhufe onnee guutuun dubbachuu ni dandeenya."
Kabajamoo Ministira Muummee Dr.Abiy Ahimad.

Ayyanicha wayita kabajnu ibsituu jaalalaa kan ta'e Gooftaa Iyyasuus fakkeenya godhachuun kanneen rakkatan yaadachuun fi gargaaruun jaalala ibsuun haa ta’u.

Ayyaanichi kan nagaa, kan jaalalaafi waloomaa isiniif haa tahu.
Irra deebiin ayyana dhalootaa nagaa nuuf haa tahu!

Itoophiyaan tattaaffii ijoollee isheetiin sodaatamtee fi kabajamtee bara baraan haa jiraattu!

Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu!

06/01/2026

ፖለቲካን ከወንበር ጋር
አቢቹ ❤️🇪🇹👌!
🙏🇪🇹 🙏ሼር🙏🙏
🙏'









❤️
✍️
█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏
╭━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭━━╮
╰╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃╯╯╯
┈┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕┃⠀┃
┈┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕┃⠀┃
┈┃⠀╰█▓▒░M░E░▒▓

ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የመኖሪያ ቤት ተሰጠው! በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎ...
06/01/2026

ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የመኖሪያ ቤት ተሰጠው!
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች አስተላልፈዋል።

የቤት ስጦታ ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታዎች መካከል ታዋቂው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ይገኝበታል!

ምሁርነት በሰርተፍኬት ብዛት ሳይሆን በልብ ርህራሄና በተግባራዊ ለውጥ የሚመዘን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጎ አድራጎት ተግባሮቻቸው በተጨባጭ መስክረዋል። እርሳቸው ስለ ምሁርነት በሰጡት ማብ...
05/01/2026

ምሁርነት በሰርተፍኬት ብዛት ሳይሆን በልብ ርህራሄና በተግባራዊ ለውጥ የሚመዘን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጎ አድራጎት ተግባሮቻቸው በተጨባጭ መስክረዋል። እርሳቸው ስለ ምሁርነት በሰጡት ማብራሪያ "ምሁር ማለት የጨለመውን የሚያበራና መፍትሄ የሚያመነጭ ነው" እንዳሉት ሁሉ ለአቅመ ደካሞች ቤት በመገንባት፣ የተማሪዎችን ምገባ በማስፋፋትና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት በመቀየር ያሳዩት ቁርጠኝነት እውቀትን ከሰብዓዊነት ጋር ያጣመረ የምሁርነት ልዕልና መገለጫ ነው።

ይህ በንድፈ-ሃሳብ ያልታጠረ ይልቁንም የወገንን እንባ የሚጠርግና በችግር ውስጥ ላሉት ብርሃን የሚፈነጥቅ ተግባራቸው ምሁርነት ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ወጥቶ በማህበረሰቡ ልብ ውስጥ መኖር እንዳለበት የሚያሳይ ህያው ተምሳሌት ነው።

05/01/2026
03/01/2026

ፋይዳ ምን ይፈይዳል?

የዲጂታል መታወቂያ አሁን ባለንበት ዓለም የኢኮኖሚና የማህበራዊ ትስስርን እየቀየረ ያለ የቴክኖሎጂ አብዮት ነዉ፡፡

በኢትዮጵያም "ፋይዳ" መታወቂያ የዚህ ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ አንዱ አካል እየሆነ ሲሆን እንደ ስንጋፖር፣ ህንድ እና ኢስቶኒያ ያሉ ሀገራት የዲጂታል መታወቂያን በመጠቀም አብዛኛዎቹን የመንግስት አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል በመቀየር የዜጎቻቸውን ሁለንተናዊ አገልግሎት በማዘመን ተጠቃሽ ሀገራት ናቸዉ ፡፡

የጥናት ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ የዲጂታል መታወቂያን ስራ ላይ ማዋል ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ፋይዳ ዜጎች ማንነታቸው ታውቆ ሁሉንም ማህበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት እንዲያገኙ ከማድረጉም ባሻገር የባዮሜትሪክ መረጃዎችን በመጠቀም ማንነትን መጭበርበርንና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማዘጋጀት የማይቻል በማድረግ የሀገርን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ ያጠናክራል።

ፋይዳ በመንግስትና በዜጎች መካከል የሚገቡ ደላላዎችን በማስቀረት፣ አገልግሎቶች ለታለመላቸው እውነተኛ ዜጎች ብቻ እንዲደርሱ በማድረግ ሙስናንና የሀብት ብክነትን የመከላከል ትልቅ አቅም ያለው ዲጂታል ሥራ ነዉ።"

የአገልግሎቶ አሰጣጥን የምያሳልጥ ይህ ስርዓት፣ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትገነባ መሰረት ይጥላል።

የፋይዳ መታወቂያ ወረቀትንና የተንዛዛ ቢሮክራሲን በማስቀረት የቴክኖሎጂ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ዘርፎችን በማቀናጀት ኢትዮጵያ በ2030 ካለመችበት እንድትደርስ የሚያስችላት ትልቅ ብልጽግና ግብ ነዉ፡፡

እያንዳንዱ ዜጋ በዚህ የታሪክ ጉዞ ውስጥ የፋይዳ መታወቂያ በመያዝ፣ ለሀገሪቱ የዲጂታል ሽግግር ስኬትና ለዘመናዊ አሰራር መስፈን መሰረታዊ ሚና መጫወት ይገባል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

03/01/2026
02/01/2026
ከመሰደድ ወደ ሀገር ግንባታና ሀቀኛ ምሁራዊነትየዛሬ 33 ዓመት 42 ምሁራን  ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ  በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ብቻ ተባረዋል፡፡ ዛሬስ ? ዛሬማ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ...
02/01/2026

ከመሰደድ ወደ ሀገር ግንባታና ሀቀኛ ምሁራዊነት

የዛሬ 33 ዓመት 42 ምሁራን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ብቻ ተባረዋል፡፡
ዛሬስ ? ዛሬማ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ምሁራን በክብር አገር ለመገንባት በጋራ ከመሪያቸው ጋር እያወጉ ነው፡፡

02/01/2026

"ሀሳብ የለውጥ ኃይል ነው ምሁራን ደግሞ የለውጥ ወኪሎች ናቸው።"-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሁራን በማህበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ለውጥ ሀገርን ወደ ብልጽግና እንደሚያሸጋግር በመጥቀስ ምሁራን የለውጥ ወኪልና የሀሳብ ኃይል መሆን እንደሚገባቸው አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው። በመድረኩ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው ምሁራን ሊላበሷቸው የሚገቡ እሴቶችን ሲገልፁ "ምሁራን የሀሳብ አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ፣ አንባቢ፣ እንዲሁም ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ መሆን ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል። በተጨማሪም "የመደመር" መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ በመግለጽ፣ ተቋማቱ በሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ አይተኬ መሆኑን መንግስታቸው በጽኑ እንደሚያምንጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማርና የምርምር ተግባራቸውን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ወደ ፈጠራና ተግባር መለወጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብልጽግና በተደመረ አቅም ለማፋጠን የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፅንኦት ተናግረዋል ፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Address

Adwa
Metu

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity For All posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prosperity For All:

Share