Ethio best

Ethio best We strive for peace

በአማራ ክልል ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል ተባለ-----------------------------------
02/07/2025

በአማራ ክልል ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል ተባለ
-----------------------------------

02/07/2025

አድስ አበባ በጣም ተለውጣለች።ውብ እና ፅዱ ሆናለች ይህንን መካድ አይቻልም።ምናልባትም ከአፍሪካ ምርጥ ከተሞች አንዷ ትሆናለች ብዬ አስባለሁ።

በትግራይ ክልል በሁለቱ የህወሓት አንጃዎች መካከል የነገሰው ውጥረት____________በትግራይ ክልል የእርስ በእርስ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል እና ክልሉ የትርምስ አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ሳልሳ...
02/07/2025

በትግራይ ክልል በሁለቱ የህወሓት አንጃዎች መካከል የነገሰው ውጥረት
____________
በትግራይ ክልል የእርስ በእርስ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል እና ክልሉ የትርምስ አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ሳልሳይ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ሳወት) ገልጿል።ሁለቱ የህወሓት አንጃወች በሚያወጧቸው መግለጫወች አንዳቸው ሌላውን ይወቅሳሉ።በደብረፂዎን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ ከኤርትራ ጋር ግንኙነት እያደረገ እና ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህ የክልሉ አለመረጋጋት ዳፋው ለመላው ኢትዮጲያ ነው።

ሠላም ለ ኢትዮጲያ!
ሠላም ለሀገራችን!

ሩሲያ በ15 የሚደርሱ የአውሮፓ ሚዲያዎች ላይ እገዳ ጣለችች______የአውሮፓ ህብረት ከዚህ ቀደም በአመቱ መጀመሪያ ላይ በሩሲያ ሚዲያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ሩሲያም 15 በሚጠጉ የአ...
02/07/2025

ሩሲያ በ15 የሚደርሱ የአውሮፓ ሚዲያዎች ላይ እገዳ ጣለችች
______
የአውሮፓ ህብረት ከዚህ ቀደም በአመቱ መጀመሪያ ላይ በሩሲያ ሚዲያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ሩሲያም 15 በሚጠጉ የአውሮፓ ሚዲያዎች ላይ የእግድ ውሳኔ አስተላልፋለች።የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንዳሉት በሩሲያ ፌደሬሽን ግዛት ውስጥ የሀሰት ዜና የሚያሰራጩ የአባል ሀገራቱ ሚዲያ ድረ-ገፆች ላይ ገደብ ለመጣል ወስነናል ብለዋል።የትኞቹ ሚዲያዎች እንደሆኑ ግን አልተገለፀም።

ወላይታ ድቻ ዋንጫው ተመለሰለት_______________________የኢትዮጲያ ዋንጫ አሸናፊ ሲዳማ ቡና ውጤት ተሠረዘ።ሲዳማ ቡና ታግደው የነበሩ ተጨዋቾችን አሰልፎ ዋንጫውን ቢያነሳም የኢትዮጲ...
01/07/2025

ወላይታ ድቻ ዋንጫው ተመለሰለት
_______________________
የኢትዮጲያ ዋንጫ አሸናፊ ሲዳማ ቡና ውጤት ተሠረዘ።ሲዳማ ቡና ታግደው የነበሩ ተጨዋቾችን አሰልፎ ዋንጫውን ቢያነሳም የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋንጫዎን ለ ወላይታ ድቻ እንዲመለስ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው ዲቻ የዋንጫው ባለቤት የሆነው።

01/07/2025
በትግራዩ ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሴቶች ላይ ዘግናኝ ወሲባዊ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚገልፅ ጥናታዊ ሪፖርት ይፋ አደረገ።እንደዘገባው በትግራይ ጦርነት ወቅት በትግራይ ከሚገኙ ሴቶች ...
01/07/2025

በትግራዩ ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሴቶች ላይ ዘግናኝ ወሲባዊ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚገልፅ ጥናታዊ ሪፖርት ይፋ አደረገ።እንደዘገባው በትግራይ ጦርነት ወቅት በትግራይ ከሚገኙ ሴቶች 10%ቱ የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ነበሩ ብሏል ከነዚህም ውስጥ 70%ቱ በቡድን የመደፈር የደረሰባቸው እንደሆኑ በጥናቱ ገልጿል።

ፍልስጤማዊያን ዛሬም ስቃያቸው በርትቷል____________________________በጋዛ ሰርጥ እስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከጀመሩ ወዲህ ንፁሀን ፍልስጤማዊያን ዋጋ እየከፈሉ ብዙዎች ህይወታቸ...
01/07/2025

ፍልስጤማዊያን ዛሬም ስቃያቸው በርትቷል
____________________________
በጋዛ ሰርጥ እስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከጀመሩ ወዲህ ንፁሀን ፍልስጤማዊያን ዋጋ እየከፈሉ ብዙዎች ህይወታቸው አልፎ በቁጥር ለመግለፅ የሚከብድ ህፃናት: ሴቶች እና አዛውንቶች አካላቸውን አጥተው ቀናት እየቆጠሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል።

የአሁኑ ጋዛ የተጋረጠባት አደጋ ግን ከምን ግዜውም የከፋ ይመስላል።ረሀብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም እየፈጇቸው ነው። አለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ወደ ጋዛ አቅንተው ለፍልስጤማዊያን ምግብ ማድረስ አልቻሉም።ሁሉም በሮች ዝግ ሁነዋል።ዜጎች ሞት አፋፍ ላይ ቆመዋል።የመንግስታቱ ድርጅት መግለጫ ቢያወጣም ሰሚ አላገኘም።

አልሂላል ማንችስተር ሲቲን አሸንፎ ሩብ ፍፃሜ ደረሰ?----------------------------------የሳዑዲው ክለብ አልሂላል በ120 ደቂቃ ፍልሚያ በውብ እግርኳስ ትዕይንት የእንግሊዙን...
01/07/2025

አልሂላል ማንችስተር ሲቲን አሸንፎ ሩብ ፍፃሜ ደረሰ?
----------------------------------
የሳዑዲው ክለብ አልሂላል በ120 ደቂቃ ፍልሚያ በውብ እግርኳስ ትዕይንት የእንግሊዙን ማንችስተር ሲቲን 4 ለ 3 በማሸነፍ ነው ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለው።ይህም የሳዑዲ አረቢያ ሊግ ማደጉን ያሳያል።የሲሞን ኢንዛጊው ቡድን አልሂላል በሩብ ፍፃሜው ከብራዚሉ ፍሉሚነንስ ይገናኛል።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መባባስ! የኔቶ ዝግጅት_____________________________ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት  ከጀመረች ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን ጥቃት  በኬቭ ላይ አድርሳለች።ከ114 ...
01/07/2025

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መባባስ! የኔቶ ዝግጅት
_____________________________
ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት ከጀመረች ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን ጥቃት በኬቭ ላይ አድርሳለች።ከ114 በላይ ሚሳኤሎች እና 1270 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተጠቅማ ዩክሬንን ደብድባለች።ይህን ተከትሎ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (NETO) ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።ወታደራዊ በጀቱ በእጥፍ እንዲጨምር አባል ሀገራቱ ወስነዋል።ኔቶ በእጅ አዙር ዩክሬንን ከማገዝ ወጥቶ በይፋ ጦርነቱን የሚቀላቀልበት ጊዜ ሩቅ አይመስልም።

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የኔቶ አባል ሀገራት የመከላከያ በጀት እንዲጨምር መስማማት የጥምረቱን መውደቅ ያፋጥነዋል ሲሉ አጣጥለውታል።

30/06/2025

በአድስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ገርጂ ካዲስኮ አካባቢ የኤሌክትሪክ መስመር ሲያስተካክል የነበረ ወጣት በኤሌክትሪክ ተይዞ ህይወቱ አለፈ።የ27 አመቱ ወጣት በኮርኒስ ወስጥ ያለፈ የኤሌክትሪክ ገመድ ሲዘረጋ ኤሌክትሪኩ እንደያዘው የአድስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ኮሚሽን አስታውቋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio best posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share