Æbman bæb

Æbman bæb Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Æbman bæb, Digital creator, Hawasa, Addis Ababa.

ኣልሳካ ሲልህ መንጌድህን እንጅ; ኣላማህን ኣትቀይር; ዛፍ ቅፕሉን እንጅ ስሩን ኣይቀይርም ። see translations "
When you are not successful change your direction ;not your goal ;atree changes it's roots, but it's leaves...✍️✍️✍️✍️https://www.youtube.com/-tube356

💚💛❤️ እውነትን የሚናገር ዘፋኝ ግፍን ከሚደግፍ ሰባኪ ይበልጣል ይሻላል።ዘፈን ኃጢአት ነው ” የሚል ሰው ፣ ከዘፈን የከፋውን  የሰው ልጅ መከራ ፥ ግፍ እና በደል ” ዝም ብሎ የሚመለከት ወ...
26/04/2026

💚💛❤️ እውነትን የሚናገር ዘፋኝ ግፍን ከሚደግፍ ሰባኪ ይበልጣል ይሻላል።

ዘፈን ኃጢአት ነው ” የሚል ሰው ፣ ከዘፈን የከፋውን የሰው ልጅ መከራ ፥ ግፍ እና በደል ” ዝም ብሎ የሚመለከት ወይም ደግሞ የሚደግፍ ከሆነ፣ እሱ ለሆዱ ያደረ ምንደኛ እንጂ በፍጹም እውነተኛ የክርስቶስ አገልጋይ ሊሆን አይደለም ።

አንተ የሕይወት ቃል የሆነውን ወንጌል ይዘህ ምን ሰራህበት ? አጣመህ ጥላቻንና ዘረኝነትን እየሰበክበት ፥ ግፈኞችንና አንባገነኖችን እየደገፍክበት ፣ ቢዝነስ እየሰራህበትና እየነገድክበት አይደል እንዴ ?

የምትንቀው ኃጢአተኛ ነው ፥ ዓለማዊ ነው ፥ የምትለው ይሄ ሰው ግን በዘፈኑ ታሪክን አወሳበት ፥ ፍቅር አንድነትን ሰበከበት ፥ ግፍና በደልን ተቃወመበት ፥ ተረኞችና አንባገነኖችን ታገለበት ፥ ለታፈነ ሕዝብ ድምፅ ሆነበት እንጂ ሌላ ምን ሲሰራበት ተመለከትክ ?

አንተ ክርስቶስን ይዣለሁ ብለህ በወንጌል ያልተቃወምከውን ጭራሽ ጠበቃ የሆንክለትን ግፍና በደል እሱ እውነትን ይዞ በዘፈን ተጋፈጠው ።

አንተ የክርስቶስን አደራ በልተህ ለምድራዊ ገዢዎች እያሸረገድክ ሺ አመት ንገሱ ስትል ፤ ይሄ ሰው ግን ለቆመለት አላማ በመታመኑ የታሰረ ፥ የተንገላታ ፥ ጥቅሙን መብቱን የተነጠቀና ብዙ ዋጋ የከፈለ ሰው አይደለምን ?

አንተ ጳጳስ ሐዋርያ ነብይ መምህር ... ተብለህ ምን ዋጋ ከፈልክ ? ከምትንቀው ኃጢአተኛ ዓለማዊ ከምትለው ከአንድ ዘፋኛ ያነሰ ጽድቅና ምግባር ይዘህ ትመጻደቃለህ ? ግብዝ ፈሪሳዊ !!

ባዶ ስብከት ከሚሰብክ "ሐዋርያ " ይልቅ፣ ለድሆች ድምፅ የሚሆንና ዋጋ የሚከፍል "ዘፋኝ " ለህዝቡ ቅርብ ነው።

አንተ በሙያህ በስብከትህ ፥ በመዝሙርህ ፥ በአገልግሎትህ ያላሳመንከውን ያልነካኸውን ያልደረስክለትን ሕዝብ ፤ እሱ በሙያው ( በዘፈኑ ) ማረከው አሳመነው ልቡን ነካው አስለቀሰው ።

አሁን ላይ ሕዝቡ ከእረኛው ይልቅ ዘፋኙን ለምን ተስፋ አደረገ ? ከአንተ ስብከት ይልቅ ለምን በዘፈን መጽናናትን መረጠ ? ከመዝሙር ይልቅ እንዴት ዘፈን ከፍቶ እየሰማ አለቀሰ ? ወንጌል ስለ ፍቅር ብቻ አይሰብክም ፥ ስለ ፍትህ ይሰብካል ፥ ለሰው ፊት አያደላም ፥ ከተገፉት ከተጨቆኑት ጎን ይቆማል ፥ ለደኃው ይፈርዳል ።

አንተ ግን መርጦ አልቃሽ ነህ ፤ ደሀው ላይ ዘፋኙ ላይ ትበረታለህ እንጂ መስዋዕትነት የሚጠይቀው ዋጋ የሚያስከፍለው የሂሮድስ ግፍና በደል ላይ ግን ዲዳ ነህ ።

ይሄ ሰው ዘፈን አወጣ በተባለ ቁጥር " ዘፈን ኃጢአት ነው " የሚል አጀንዳ ይዘው እዚህ ሰው ላይ የሚዘምቱ ሰዎች እውነት ዘፈንን ጠልተውና ዘፈንን ተጸይፈው ነው ?

እረ በፍጹም ! እነዚህ ሰዎች የዘፈን ኃጢአትነት ገዷቸው እንዳይመስልህ ፤ የሚደግፉትና የጥቅም ተጋሪዎች የሆኑበት ስርዓተ መንግስት አገዛዝ ስለተነካባቸው አንድም ታማኝነታቸውን ለማሳየት አንድም በፍርሃት ነው የሚጮሁት ።

ከጀርባቸው የዘርና የሃይማኖት ጥላቻን የተሸሙ ፥ የፖለቲካ አጀንዳን ያነገቡ ሰዎች ናቸው ።

ዘፈንማ ከዓለማዊ እስቴጅ ላይ ተባራ ጓዟን ጠቅልላ እነሱ ቸርች ከከተመች እኮ ቆየች ። አይደለም እነሱ አምላካቸው ራሱ መቼ ያለ ዘፈን ይንቀሳቀሳል ?

ግፍን የሚደግፉ ፥ በደልን እያዩ ዝም የሚሉ ፥ የአንባገነኖችን ጫማ የሚልሱ ራሳቸውን ለጥቅም የሸጡ ሰዎች በምን ሞራላቸው ነው በዜማ ስለ ሀገር ስለ ፍቅር ስለ አንድነት ወዘተ የሚያዜመውን የነጻነት ታጋይ የሚያወግዙት ?

መጋቢ ሀዲስ እሸቱ

#እውነት #ኢትዮጵያ

Address

Hawasa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Æbman bæb posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share