Rediet bekele

Rediet bekele እንኳን ደና መጣችሁ በኔ ቤት ስለተለያዩ ነገሮች እያነሳን እንጨዋወታለን😍

☝️ታላቅ ቅናሽ👉ደንበኞቻችን Human hair ላይ  ለ        አንድ ወር የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድርገናል ይደውሉ ይዘዙን።✡ 12 grade Original human hair 👉 price pe...
28/03/2024

☝️ታላቅ ቅናሽ
👉ደንበኞቻችን Human hair ላይ ለ
አንድ ወር የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድርገናል ይደውሉ ይዘዙን።

✡ 12 grade Original human hair

👉 price per 200 gram👇

➡️ 18 inch 12500 birr
➡️ 20 inch 13500 birr
➡️ 22 inch 14500 birr
➡️ 24 inch 15500 birr
➡️ 26 inch 16500 birr
➡️ 28 inch 17500 birr
➡️ 30 inch 18500 birr
➡️ 32 inch 19500 birr

ይደውሉ ይዘዙን
📱 0944365018

እዚ ግሩፕ ውስጥ እየገባችሁ አዳዲስ እቃዎች ምረጡ
28/03/2024

እዚ ግሩፕ ውስጥ እየገባችሁ አዳዲስ እቃዎች ምረጡ

Human hair በተመጣጣኝ ዋጋ አለኝ😊
27/03/2024

Human hair በተመጣጣኝ ዋጋ አለኝ😊

eyelash extension glue በብዛት የሚፈልግ አለ በጥሩ ዋጋ ኢንቦአክስ ፃፉልኝ😊
27/03/2024

eyelash extension glue በብዛት የሚፈልግ አለ በጥሩ ዋጋ ኢንቦአክስ ፃፉልኝ😊

ቆንጆ ቦርሳዎች በተመጣጣኝ ዋጋ አሉኝ ግዙ🥰🙏
27/03/2024

ቆንጆ ቦርሳዎች በተመጣጣኝ ዋጋ አሉኝ ግዙ🥰🙏

ቆንጆ የሴት ጫማዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በብዛትም በነጠላም የሚፈልግ አለኝ እየገዛችሁ🥰🙏
27/03/2024

ቆንጆ የሴት ጫማዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በብዛትም በነጠላም የሚፈልግ አለኝ እየገዛችሁ🥰🙏

የወንድ መነፅሮች0944315959
23/10/2023

የወንድ መነፅሮች
0944315959

የሴት ቆንጆ ሰአቶች አሉ በቴሌግራም https://t.me/onlineshoppingeth ገብታችሁ ሌሎችም እቃዎችን እዩ በስልክ ቁጥር 0944315959 ደውሉ ዴሊቨሪም አለ
20/10/2023

የሴት ቆንጆ ሰአቶች አሉ በቴሌግራም https://t.me/onlineshoppingeth ገብታችሁ ሌሎችም እቃዎችን እዩ
በስልክ ቁጥር 0944315959 ደውሉ ዴሊቨሪም አለ

😌ብርዱ
17/07/2023

😌ብርዱ

  ከዚው ከፌስቡክ የተገኘ ሁሉም ሰው ሊማርበት የሚችል ጥሩ ታሪክ        ህይወት ትምህርቴን ለመጨረስ እድል ስላልሰጠችኝ ስራ የጀመርኩት ገና የ16 ዓመት ልጅ ሆኜ ነበር::     የመጀመ...
01/07/2023

ከዚው ከፌስቡክ የተገኘ ሁሉም ሰው ሊማርበት የሚችል ጥሩ ታሪክ
ህይወት ትምህርቴን ለመጨረስ እድል ስላልሰጠችኝ ስራ የጀመርኩት ገና የ16 ዓመት ልጅ ሆኜ ነበር::
የመጀመሪያ ስራ የተቀጠርኩት በካፌ መስተንግዶ ነበር ምንም አይነት የስራ ልምድ አልነበረኝም ነገረ ግን ፈጣንና የነገሩኝን ቶሎ ቀጨም የሚደርግ የልጅ ጭንቅላት ነበረኝና ስራው ጋር የተዋሃድኩት ብዙ ሳልቸገር ነበር የሚገኘው ቲፕ እየጣመኝ ለአንድ ዓመታት ከካፌ ካፌ እየቀያየርኩ ሰራሁ የተቀጠርኩበት ካፌ ፊትለፊት የመኪና አስመጭ ቢሮ ነበር ሁሌም ሻይ ቡና የምወስድላቸው እኔ ነኝ ትዕዛዛቸው ደቂቃ ሳይቆይ ከተፍ ስለሚልላቸው ይወዱኝ ነበር በኋላ ቅልጥፍናና ልጅነቴን ሲያዪ በፅዳትና ተላላኪነት እንቅጠርሽ አሉኝ ያለማመንታት መስተንግዶዬን ትቼ እነሱ ጋር ተቀጠርኩ በወቅቱ መስሪያ ቤት ተቀጥሮ መስራት ለእኔ ትልቅ ነገር ይመስለኝ ነበር። ቢሮቸውን አፀዳለሁ ወረቀት ከቢሮ ቢሮ እወስዳለሁ ኮፒ አደርጋለሁ.....ብቻ የማልታዘዘው ነገር አልነበረም አራት ወር እንደሰራሁ ግን ሰለቸኝ በተለይ በየቀኑ ቲፕ ለምጄ የወር ደመወዝ መጠበቅ ከባድ ሲሆንብኝ ተውኩትና ከቤተሰብ ጋር የስሚንቶ ወረቀት እየተረከብን አፅድተን ከሩብ ኪሎ እስከ አምስት ኪሎ እንዲይዝ አድርገን እየቆራረጥን እየለጠፍን መርካቶ ላሉ ወረቀት አከፋፋዮች ፣ ለችርቻሮ ሱቆችና ለሱፐር ማርኬቶች ማስረከብ ጀመርን ስራው ገቢ ቢኖረውም እጅግ አድካሚ ነበር በተለይ ወረቀቱን ከየስሚንቶ ፋብሪካው ከየ ብሉኬትና ቱቦ መስሪያ ቦታ እየዞር መሰብሰብና ሲሚንቶውን ማፅዳቱ በጣም አስቸጋሪ ነበር በዛ ላይ ተረካቢውቹ የሚወስዱት በዱቤ ስለነበር ከነሱ ጋር ብር አምጡ ንዝንዙ ተስፋ ያስቆርጥ ነበር (ሰው ደስ የሚለው የለፋበትን በሰዓቱ ሲያገኝ ነው)

በዛስራ ትንሽ እንደቆየን የወረቀቱን ስራ ለቤተሰብ ትቼ በራችን ላይ በሸራ ቆቆር እየተረከብኩ ከሻይ ጋር መሸጥ ጀመርኩ ነገር ግን ተጠቃሚወቹ የሰፈር ልጆች ስለነበሩ ዛሬ የለንም ሲሉኝ ችግር የለውም ውሰዱ እያልኩ ብዙ ሳልሰራ ከሰርኩ😂

በመሀል ሰፈራችን ያለ የውጭ ድርጅት የፅዳት ስራ ማስታወቂያ አወጣና ተቀጠርኩ ስራው ቢሮና መፀዳጃ ቤቶችን ማፅዳት የምሳ ሰዓት ላይ ለሰራተኞቹ ሻይ ቡና ማፍላት በልተው ሲጨርሱ የምግብ አዳራሹን ማፀዳዳት ነበር ስራው አይከብድም ደመወዙም ጥሩ ነበር በዛ ላይ በራሳቸው ወጭ አስተምረው እዛው ይቀጥራሉ ስለተባለ ደስ ብሎኝ ነበር ነገር ግን ከእኔ በፊት ስትሰራ የቆየች ሴትዮ ከፋችብኝ እሷ ቁጭ ብላ የምታዘው እኔን ሆነ እሷ ማፅዳት ያለባትን ቢሮና ታፀዳኛለች እምቢ እንዳልል ትልቅ ሴትዮ ናት በዛ ላይ ቆይታለች ለቀጣሪውቼ አቃጥራ ብታስባርረኝስ ብዬ አንገቴን ደፍቼ መስራቴን ቀጠልኩ ሴትዮዎ ግን እየባሰባት መጣ ኤጭ ገና ለገና ያስተምሩኛል ብዬማ አልጨቆንም አልኩና ስራውን ትቼ ወደ ለመድኩት መስተንግዶዬ ተመለስኩ።
ያኔ ግን ከካፌ ከፍ አድርጌ ሬስቶራንት ተቀጠርኩ። ደረጃውን የጠበቀ ትልልቅ ሰዎች የሚገቡበት ሬስቶራንት ነበር በዛ ላይ ባለቤቶቹ ለሰራተኛ የነበራቸው ቅርበት እንደቤተሰብ ስለነበር ሁሉም ሰራተኛ ስራውን የሚሰራው በደስታ ነበር እኔም ቤተኛ ለመሆን ጊዜ አልፈጀብኝም በትንሽ ወራቶች የቤቱ ተወዳጅ አስተናጋጅ ሆንኩኝ ብዙ ከስተመር አፈራሁ በተለይ የካፕሎች ዘንድ ተመራጭ ነበርኩኝ ስራዬን የምሰራው በፍቅር ነበር የማገኘው ቲፕ የልጅ ሀብታም አድርጎኝ ነበር(ምን ዋጋ አለው ቁጠባ የሚባል አላውቅም) ስራውን በጣም ከመውደዴ ብዛት ሁሌም ወደፊት የራሴ ሬስቶራንት እንደምከፍት አልም ነበር ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ደስ ብሎኝ ሰራሁ። በዛን ወቅት ስለአረብ ሀገር በጣም ተጋኖ ይወራ ስለነበር እኔም ለመሄድ ልቤ ተነሳ በተለይ ሬስቶራንት የመክፈት እቅዴ ለማሳካት የግድ መሄድ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ ትንሽ ገንዘብም ጠርቀም አድርጌ ስለነበር የምወደውን ስራ ትቼ ዱባይ ተሰደድኩ
ያው የስደትን ነገር ብዙ ስለተወራለት ልለፈው ..... ከአምስት አመት የስደት ቆይታ በኋላ በሰላም ሀገሬ ገባሁ ትንሽ እረፍት አድርጌ እንደ ሀሳቤ ቅልብጭ ያለች ባህላዊ ምግብ ቤት ከፈትኩ (አቤት ያኔ የተሰማኝ ደስታ) እረዳት ቢኖሩኝም ምግቡን የማበስለው እራሴ ነበርኩ ቤታችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝነኛና ተወዳጅ ሆነች ብዙ ከስተመርም አፈራን በርግጥ በልተው የለንም የሚሉ ዱቤ ተጠቅመው የሚጠፋ ሰዎችም ነበሩ
እኔም የለኝም ሲሉኝ አያስችለኝም😓(በነገራችን ላይ ነጋዴ ለማትረፍ ቆፈጣና የሚስጨንቀው ትርፍና ኪሳራውን ብቻ መሆን አለበት!እንደ እኔ ልፍስፍስ ሰው የመክሰር አጋጣሚው የሰፋ ነው)

አመት ከሦስት ወር እንደሰራን ሌላ ቅርንጫፍ ለመክፈት እያሰብኩ ያ ኮሮና የሚሉት ክፉ በሽታ መጣ😓😓
ስራው ሞተ ሳይሰራ የቤት ኪራይ መክፈል ደሞ በጣም ከባድ ነበር ለትንሽ ጊዜ ባለኝ ካፒታል ያለ ገበያ ለ6ወር ቤቱን ላለመዝጋትና ሰራተኞቹን ላለማባረር ቤት ኪራይና ደመወዛቸውን እየከፈልኩ ተንገዳገድኩ ግና ገና ጀማሪ ስለነበርኩ መቋቋም አቃተኝ ከሰርኩ ማስቀመጥ የምችለውን እቃ አስቀምጨ የሚሸጠውን በማይረባ ዋጋ ሽጬ ምግብ ቤቴን ዘጋሁና ቤቴ ተቀመጥኩ (እጅግ ተስፋ የቆረጥኩበት ወቅት)
የማያልፍ የለም ኮሮና አለፈ ተመልሼ ምግብ ቤቴን ለመጀመር ቤት ኪራዮ የማይቀመስ ሆነ ሞራሌ ሞተ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ተስፋ ቆረጥኩ ረጅም ጊዜ በድብርት ከቤት ሳልወጣ አሳለፍኩ።
የሆነ ቀን መውደቅ መነሳት መክሰር ማትረፍ ባንች አልተጀመረም ይህ የሚሆነው በህይወት ስላለሽ ነው አንች ያጣሽው ገንዘብ ነው በዛ ክፉ መቅሰፍት ስንቱ ህይወቱን አጥቶል እኮ ቆይ አንችስ ሞተሽ ቢሆን ይሄንን ቀን ለማየት ትታደይ ነበር?? እራሴን ጠየኩ በራሴ አፈርኩ ፈጣሪዬን ይቅር በለኝ ብዬ ፀለይኩ ቁጭ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ተማከርኩ ምግብ ቤት መክፈት ቢያቅተኝ በሙያዬ ቤቴ እየሰራሁ በፊት በየስራ ቦታቸው ለምናደርስላቸው ደንበኞች በስልክ የዲሊቨሪ አገልግሎት መስጠት እንደምችል ራሴን አሳምኝ በአዲስ መንፈስ ለስራ ተነሳሁ የቢዝነስ ካርድ አሰርቼ ለደንበኞቼ ሰጠሁና ስራውን አሀዱ አልኩ ከሱ በተጨማሪ እንጀራ እየጋገርኩ ለሱቅ ማስረከብ ጀመርኩ አሁንም ትንሽ ጊዜ ተፍጨረጨርኩ ነገር ግን የምግብ ስራ ትርፉ ከብዛት ስለሆነ የዲሊቨሪው ስራ አዋጭ አልሆነም እንጀራው የሚረከቡት ባለሱቆች ደሞ ሌላ ነገር እየቀላቀሉ የሚሸጡ ጋጋሪዎች በሚስረክቡበት ዋጋ አስረክቢን ማለት ጀመሩ እነሱ በሚሉት ዋጋ ባስረክብ የምጋግረው ጤፍ እንጀራ ነበርና አያዋጣም እንዲያዋጣኝ ከፈለኩ ደሞ ህሊናዬን ልሸጥ ነው
(ያው ንግድ ካልዋሹ ካልሰረቁ ካልከፉ አያዋጣም ኣ😂)
ከዚህ ሁሉ ቢቀርስ ብዬ ተውኩትና እንደለመድኩ ወደ ስደቴ መጣሁ ......

እነሆ ዛሬ በስደት ነኝ ተመስገን በጉልበቴ ሰርቼ በማደሬ ቤተሰቤን በማስተዳደሬ ለተቸገረ ያቅሜን ለማድረግ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ

በህይወቴ ብዙ ቻሌንጆች አልፈዋልዋል ተስፋ የጣልኩበት መና ሆኗል ያቃል፤ኪሳራን አስተናግጃለሁ፤ ተስፋ ቆርጨ ድባቴ ውስጥ ገብቼ አውቃለሁ፤ ዝቅ ብሎ ከመስራት ቀጥሮ እሰከማሰራት አይቼዋለሁ አንድ ነገር ግን ሁሌም ለ ሳም እነግራታለሁ........ !!!!!

እና ምን ልላችሁ ነው በስራችን ብዙ ተስፋ የሚስቆርጡ ነገሮች ይገጥሙን ይሆናል የማይገባን ቦታ የማይመጥነን ስራ እየሰራን ይሆናል ግን ዛሬ እኛ ይሄን የምንታገለው በጤናና በህይወት ስላለን ነው..........ነገ ደሞ የተሻለ ይሆናል!!!!!

😊😍
06/06/2023

😊😍

Address

Addis Ababa
ADDISABABA

Telephone

+251944305018

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rediet bekele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category