Car for Sale & Rent, Addis Ababa, Ethiopia

Car for Sale & Rent, Addis Ababa, Ethiopia Sick and tired of Ethiopian politics?

“ትሸታላችሁ” በሚል ጥቁር መንገደኞችን ከበረራ ላይ ያስወረዱ ሰራተኞች ከስራ ተባረሩ፡፡***********ከፎኒክስ አሪዞና ወደ ኒዮርክ ለመጓዝ ወንበራቸው ላይ የነበሩ ጥቁር አሜሪካዊያን በበረ...
24/06/2024

“ትሸታላችሁ” በሚል ጥቁር መንገደኞችን ከበረራ ላይ ያስወረዱ ሰራተኞች ከስራ ተባረሩ፡፡
***********
ከፎኒክስ አሪዞና ወደ ኒዮርክ ለመጓዝ ወንበራቸው ላይ የነበሩ ጥቁር አሜሪካዊያን በበረራ አስተናጋጅ አማካኝነት ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ይነገራቸዋል፡፡

ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በተፈጠረው በዚህ ክስተት የበረራ አስተናጋጁ ጥቁር አሜሪካዊያንን መርጦ ለምን እንዳስወረዳቸው ሲጠየቅም ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ መጥፎ ሽታ ያለው መንገደኛ በመኖሩ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል ተብሏል፡፡

በተለያዩ ወንበሮች ላይ የተቀመጡት እና የማይተዋወቁት እነዚህ 5 ጥቁር አሜሪካዊያን መጥፎ የሰውነት ሽታ አለ በሚል ከየተቀመጥንበት ተመርጠን እንድንወርድ መደረጋችን ግልጽ ዘረኝነት ነው ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በረራው ቢዘገይም በዚሁ አውሮፕላን አብረው እንዲጓዙ ከተደረጉ አምስት ጥቁር አሜሪካዊያን መካከል ሶስቱ ክስ መስርተውም ነበር፡፡

ለደረሰብን የዘረኝነት ጥቃት አየር መንገዱ ካሳ ሊከፍለን ይገባል ሲሉ ክስ የመሰረቱት እነዚህ ሶስት አሜሪካዊያን በተፈጠረው ክስተት ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡

ክስ የቀረበበት የአሜሪካን አየር መንገድ በወቅቱ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩትን ሁሉ ከስራ ማባረሩን አስታውቋል፡፡

ጉዳዩ በፍጹም ተቀባይነት የለውም ያለው አየር መንገዱ መንገደኞችን ማበላለጥ ፍጹም ከሙያ ስነ ምግባር በመሆኑ እርምጃ እንደወሰደባቸው ገልጿል፡፡

በፈረንጆቹ 2017 ላይ አንድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጥቁር አሜሪካዊያን ዘረኝነት እና መድሎዎችን ለመራቅ በአሜሪካን አየር መንገዶች እንዳይበሩ ሲል አስጠንቅቆ የነበረ ሲሆን አየር መንገዶች ማስተካከያ አድርገናል ማለታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያውን አንስቷል፡፡
#ምንጭ አል አይን

በቀራንዮ ከተማ ‘በመንግስት ሃይሎች’ ተፈፀመ የተባለን አሰቃቂ ግድያን ተከትሎ ነዋሪዎቹ በፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን ገለፁ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በቀራንዮ ከተማ ከሳምንት በፊት ሰኔ...
20/06/2024

በቀራንዮ ከተማ ‘በመንግስት ሃይሎች’ ተፈፀመ የተባለን አሰቃቂ ግድያን ተከትሎ ነዋሪዎቹ በፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን ገለፁ

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በቀራንዮ ከተማ ከሳምንት በፊት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን ተከትሎ ነዋሪዎቹ በፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቁ፤ ግድያው የተፈጸመው በቤተክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ የመቃብር ጉድጓድ በመቆፈር ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ግድያው የተፈፀመው ቀደም ብሎ የፋኖ ታጣቂዎች በመንግስት ኮንቮይ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።

በወቅቱ ጥቃቱ በተፈጸመበት ቦታ በመድረስ አስከሬኖቹን ካነሱት ሰዎች አንዱ ነኝ ያሉን የአይን እማኙ “በተገደሉት ሰዎች አስከሬን እና በፈሰሰው ደም ተሸፍነው የተረፉ ሶስት ሰዎች መገኘታቸውን” አስታውቀዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ከምስራቅ ጎጃሟ ቀራንዮ በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እሁድ ሰኔ 9 በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህና ወረዳ ጂጋ ከተማ በፈጸሙት ጥቃት መምህራን እና የባንክ ቤት ሠራተኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች “መረሸናቸውን” ሁለት የዐይን እማኞች እና ከተማዋን ወክለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቡት አቶ አበባው ደሳለውን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

https://addisstandard.com/Amharic/%e1%89%80%e1%8a%93%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%89%a3%e1%88%b5%e1%89%86%e1%8c%a0%e1%88%a8%e1%8b%89-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%88%83%e1%8b%ad%e1%88%8e%e1%89%bd/?amp=1

Via Addis Standard

አስርቱ ትዕዛዛት ወደ መመሪያ‼️የአሜሪካዋ ሉይዚያና ግዛት በሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች መማሪያ ክፍሎች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ አስርቱ ትእዛዛትን የሚያሳይ ፖስተር እንዲ...
20/06/2024

አስርቱ ትዕዛዛት ወደ መመሪያ‼️
የአሜሪካዋ ሉይዚያና ግዛት በሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች መማሪያ ክፍሎች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ አስርቱ ትእዛዛትን የሚያሳይ ፖስተር እንዲለጠፍ አዘዘች።
ቴክሳስ፣ ኦክላሆማ እና ዩታን ጨምሮ ሌሎች በሪፐብሊካን የሚመሩ ግዛቶች ተመሳሳይ ህጎች በቅርቡ እንደቀረቡ ከቢቢሲ ዘገባ አዩዘሀበሻ ተመልክቷል።
፲(10) አስርቱ ትዕዛዛት ( ሕግጋት ) ዝርዝራቸው👇
፩ / ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ
፪/ የእግዚአብሔር የአምላክሕን ስም በከንቱ አትጥራ
፫/ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ
፬/ አባትና እናትሕን አክብር
፭/ አትግደል
፮/ አታመንዝር
፯/አትስረቅ
፰/ በሐሰት አትመስክር
፱/ አትመኝ
፲/ ባልንጀራሕን እንደ እራስሕ አድርገህ ውደድ
አዩዘሀበሻ
==

በጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ጋር በተያያዘ የሦስት ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ሕይወት አለፈ‼️በጎረቤት አገር ጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የከባድ መ...
20/06/2024

በጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ጋር በተያያዘ የሦስት ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ሕይወት አለፈ‼️
በጎረቤት አገር ጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የከባድ መኪና አሽርካሪዎች እና የመኪና ጥገና ባለሙያ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕይወት እንዳለፈ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር አስታወቀ።
ተሽከርካሪዎች የሚያጓጉዙት ጭነት ሳይደርስ ወደ ጅቡቲ ተጉዘው ለቀናት እንዲጠብቁ እየተደረገ መሆኑ ለሙቀት እና ለሌሎች ችግሮች እንዲጋለጡ እያደረጋቸው እንደሆነ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ምርቶች ዋነኛ በር ወደ ሆነችው ጂቡቲ የሚመላለሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና መቀመጫውን በአገሪቱ ያደረገ የጥገና ባለሙያ ሕይወታቸው ያለፈው፤ በሰኔ ወር መጀመሪያ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እንደሆነ የማኅበሩ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዳመነ ተሾመ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት የማኅበሩ አመራሮች ሕይወታቸው ካለፈው ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በላይነህ ክንዴ የግል ትራንስፖርት አሽከርካሪ እንደሆነ እና ቀሪዎቹ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ በመንግሥታዊ የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
ሕይወቱ ያለፈው የጥገና ባለሙያ የመንግሥታዊው የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆነው ኢትዮጰያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሠራተኛ እና ሌላኛው አሽከርካሪ ደግሞ የአማራ ክልል የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ጥቁር አባይ ትራንስፖርት አሽከርካሪ እንደሆነ አመራሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጰያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ እንዲሁም በላይነህ ክንዴ የግል ትራንስፖርት የአሽከርካሪዎቹን ህልፈት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
በጂቡቲ ያለው ወቅታዊው የሙቀት ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑን የሚናገሩት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን፤ በአሁኑ ወቅት ያለው የአየር ሁኔታ አሽከርካሪዎች “ሊቋቋሙት የማይችሉት” እንደሆነ አስረድተዋል።
#ቢቢሲ
=======================

ከ500 በላይ የሀጅ ተጓዦች መሞታቸው ተነገረ‼️👉 ከሞቱት አብዛኞቹ ግብፃዊያን ናቸው ተብሏል።በሳውዲ አረቢያ በዘንድሮው የሃጅ ጉዞ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በከባድ ሙቀት መሞታቸውን ባ...
20/06/2024

ከ500 በላይ የሀጅ ተጓዦች መሞታቸው ተነገረ‼️
👉 ከሞቱት አብዛኞቹ ግብፃዊያን ናቸው ተብሏል።
በሳውዲ አረቢያ በዘንድሮው የሃጅ ጉዞ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በከባድ ሙቀት መሞታቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ከተለያየ ሀገራት ሐጅ ሥርዓት ለመፈጸም በሥፍራው የሚገኙት ምእመናን በሳውዲ አረቢያ ያለው ወቅታዊ ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑት ሙቀቱን መቋቋም ተስኗቸው ህይወታቸው እንዳለፈ ተነግራል። ከሟቹ መካከል ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑት ግብጻውያን መሆናቸውን ከኤፍፒ የተገኘው መረጃው ያመለክታል ።
አዩዘሀበሻ
=======================

The first automobile was produced in Germany by Carl Benz in 1886. 137 years later see what they have made out of it! Ap...
16/06/2024

The first automobile was produced in Germany by Carl Benz in 1886. 137 years later see what they have made out of it!

Apart from Mercedes, so many other names have emerged in car production.This transformation is not only seen in automobile industry but in all aspects of life in Germany and Europe. E.g in education, medicine, commerce, politics, sports and so on.

First picture in this post is Mercedes 137 years ago and the same Mercedes today.

Second picture, is our palm wine tapping more than 2000 years ago and the same palm wine tapping today.

Address

Bole Medhanealem Area
Addis Ababa

Telephone

+251912095575

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Car for Sale & Rent, Addis Ababa, Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share