ቆንጆ Ethiopia

ቆንጆ Ethiopia 💚💛❤በቆንጆ Ethiopia ላይ ለሀገሪቷ ከፍታና ብልፅግና የማዕዘን ድንጋይ የሆኑ ሀሳቦች ይነሳሉ !!! ቆንጆ ኢትዮጵያን እናያለን !!

መረጃ አዘል ጥያቄየኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቋል። በቅርብ ቀናትም በይፋ ይመረቃል። እርስዎ በግልዎ በግድቡ ጥንስስና ግንባታ ወቅት ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ብለው የሚያስቧቸውን አካላትና...
01/09/2025

መረጃ አዘል ጥያቄ

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቋል። በቅርብ ቀናትም በይፋ ይመረቃል። እርስዎ በግልዎ በግድቡ ጥንስስና ግንባታ ወቅት ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ብለው የሚያስቧቸውን አካላትና ግለሰቦች በቅደም ተከተል ዕውቅና ቢሰጡ?
***
ማስታወሻ:- ጨዋነት የጎደላቸው አስተያየቶች አይስተናገዱም።

የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከቀድሞው ስራ አስኪያጅ ኢንጂንር ስመኘውን በቀለ በሃላ በመረከብ ፕሮክቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት በመምራት ለዛሬው ክብርና ስኬት ...
01/09/2025

የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከቀድሞው ስራ አስኪያጅ ኢንጂንር ስመኘውን በቀለ በሃላ በመረከብ ፕሮክቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት በመምራት ለዛሬው ክብርና ስኬት ያበቁ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ክብርና ምስጋና አለዎትና እንኳን ደስ አለዎት ደስ አለን !

01/09/2025

Big shout out to my newest top fans! Muluken Ayalew, ሙሉ ቶልቻ ሁንዴ, Temesgen Areko

"አሰብ ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ነው!  የትኛውንም ዋጋ ከፍለን እናስመልሰዋለን። "  ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ "አሰብ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ግዛት ነው የኢትዮጵያም ህልውና ነው ፤በኢትዮጵያ...
01/09/2025

"አሰብ ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ነው! የትኛውንም ዋጋ ከፍለን እናስመልሰዋለን። "

ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ

"አሰብ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ግዛት ነው የኢትዮጵያም ህልውና ነው ፤በኢትዮጵያ ጉዳይ የመወሰን መብት ባልነበረው የሽግግር ቡድን አሳልፎ የተሰጠ ራስ ገዝ የባህር በራችን ነው፤ በዚህም ብዙ ሃገራት በናንተ ድክመት ነው እስካሁን ያልተመለሰው እንጂ እስካሁን መቆየት ያልነበረበት ነው ይሉናል ፤ አሁን ላይ የቀይ ባህር ጉዳይ የህልውናችን ጉዳይ ሆኗል ለህልውናችን ስንልም የትኛውን ዋጋ ከፍለን አሰብን እናስመልሰዋለን ። "

ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ የአሰብን ኢትዮጵያዊነት በግልፅ እንቅጩን ከገለፁበት ንግግር

ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet

ህዳሴ ግድቡ ቶሎ እንዲጀመር: ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስጀመሪያ 1.5ቢሊዬን ብር ($88 Million) የሰጡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ!!!
01/09/2025

ህዳሴ ግድቡ ቶሎ እንዲጀመር: ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስጀመሪያ 1.5ቢሊዬን ብር ($88 Million) የሰጡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ!!!

“በ7 ዓመቴ ለሕዳሴ ግድብ ማሠሪያ የማረባውን ዶሮ ሰጥቻለሁ” - የዛሬዋ የ17 ዓመት ወጣት ***********************"ሀገር ስትጣራ አለሁ ለማለት ትልቅ ትንሽ አይልም፤ ሁላችሁም ...
30/08/2025

“በ7 ዓመቴ ለሕዳሴ ግድብ ማሠሪያ የማረባውን ዶሮ ሰጥቻለሁ” - የዛሬዋ የ17 ዓመት ወጣት
***********************

"ሀገር ስትጣራ አለሁ ለማለት ትልቅ ትንሽ አይልም፤ ሁላችሁም ሀገራችሁን ውደዱ፤ በቻላችሁት ልክ ሀገራችሁን ጥቀሙ"፦ የያኔዋ የ7 ዓመት አዳጊ - ሰሚራ ኢብራሂም

ሰኔ 15 ቀን 2007 ደበብ ወሎ ከላላ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ሀገር መልዕክት ልካላቸው ተስብስበዋል።

ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀሉም የአቅሙን እያዋጣ ነው። የዚህ ታሪክ ተቋዳሽ ለመሆን የሚሽቀዳደሙ እግሮች ከየጎጆው በብዛት እየተመሙ ይገኛሉ።

እነ አቶ ኢብራሂም ቤትም ምን እናድርግ? ምን እንስጥ? ብለው ምክር ይዘዋል።

ፈንጠር ብላ ራሷ ካረባቻቻው እና መሬት እየጫሩ ከሚገኙ ሦስት ዶሮዎች አጠገብ የተቀመጠችው አዳጊ፣ “እኔ ዶሮዬን እሰጣለው” አለች። ቤተሰቡ ሁሉ በግርምት ተመለከቷት።

“ልጅ መሆኔን አትመልከቱ፤ ከነዚህ ሦስት ዶሮዎቼ መካከል ይህን ትልቁን (ገዘፍ ያለውን አውራ ዶሮ እየጠቆመች) ለሕዳሴ ግድብ መስጠት አፈልጋለው። ግድቡ እኮ የሁላችንንም ድጋፍ ይፈልጋል። ደግሞም ተማሪዎች በየአገሩ በአቅማቸው ቦንድ እየገዙ እንደሆነ ሰምቻለሁ። እኔም ለኢትዮጵያ ይህን ባደርግላት ደስታዬ ነው” ስትል ደፈር ብላ ተናገረች።

አባቷ በደስታ እቅፍ አድርገው ሳሟት። ቤተሰቡ ሁሉ መረቃት።

የያኔዋ የ7 ዓመቷ አዳጊ ሰሚራ ኢብራሂም በደስታ እየተፍነከነከች፣ እሷን ለማከል ጥቂት የሚቀረውን ግዙፍ አውራ ዶሮ ይዛ በፍፁም ቸርነት የሕዳሴ ዋንጫ ተቀምጦ ድጋፍ ወደሚሰበሰብበት ስፍራ ሄደች።

በገቢ ማሰባሰቢያው የታደሙት በአዳጊዋ አድራጎት ተገረሙ። “ይህ ዶሮ እዚሁ በጨረታ ይሸጥ” ተባለ።

ሁሉም ለአሸናፊት ተረባረበ። በመጨረሻው ዶሮው 17 ሺህ ብር በጨረታ ተሸጠ። በገንዘቡ ልክ በስሟ ቦንድ ተገዛላት።

በታላቁ ሕዳሴ ግድብ አሻራዋን አኖረች። የከለላ ሕዝብ መዳፏን እየሳመ አመሰገናት፤ በምርቃት አረሰረሳት።

ዘመን ተሻጋሪው ግድብ ላይ በልጅነቷ አሻራዋን ያኖረችው ሰሚራ ኢብራሂም ዛሬ 17 ዓመት ሆኗታል።

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 አግኝቶ የሕዳሴ ግድብ ለዚህ ደረጃ በመብቃቱ ምን ተሰማሽ? ብሎ ጠይቋታል።

“ፈጣሪ ዕድሜ ሰጥቶኝ ይህን ስላሳየኝ በጣም ደስ ብሎኛል። ደስታዬን ለመግለፅ ቃላት የለኝም። ወደፊትም ገና ብዙ መልካም ነገሮች እንደምናይ አምናለሁ” ብለዋለች።

“በእርግጥ የእኔ ብቻ አይደለም፤ በሁላችን ርብርብ ነው ግድቡ እዚህ የደረሰው። ሁሉም የቻለውን ያደረገለት ግድብ ነው።” ስትል የኢትዮጵያውንን የትብብር መንፈስ ገልጻች።

“ለሀገር መሥዋዕት ለመክፈል ትልቅ ትንሽ አይልም፤ ሁላችሁም ሀገራችሁን ውደዱ፤ በቻላችሁት ልክ ሀገራችሁን ጥቀሙ።” ስትልም መልዕክቷን አስተላልፋለች።

ሰሚራ የሷ ትውልድ ምልክት ናት፤ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ እንዳረፈበት ኅያው ምስክር ሲቆጠር፣ ከእርሷ ነው የሚጀመረው።

በዮናስ ወልደየስ

30/08/2025

የጌድኦ እናት ክፉ 😭 ገጠማት 15 ወገኖቻችን በሙሉ አፈር ተመልሶባቸዋል ...

ከጌድጎ እናት ጎን እንቁም !

ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን🇪🇹🇪🇹✔️ ቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ➛ $10 ቢሊዮን ዶላር ✔️ ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ ➛ $2.5 ቢሊዮን ዶላር✔️ YY Project (ህዳሴ...
29/08/2025

ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን🇪🇹🇪🇹

✔️ ቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ➛ $10 ቢሊዮን ዶላር

✔️ ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ ➛ $2.5 ቢሊዮን ዶላር

✔️ YY Project (ህዳሴ ግድብ ፪) ➛ $5.3 ቢሊዮን ዶላር

✔️ MM Project (ግቤ ፭) ➛ $4.7 ቢሊዮን ዶላር

✔️ ከአዲስ አበባ ወደ ክልሎች የፍጥነት መንገድ ➛ $11 ቢሊዮን ዶላር

ሀ| አዲስ አበባ ➛ ደብረብርሃን➛ኮምቦልቻ➛ደሴ
ለ| አዲስ አበባ ➛ ፍቼ/ሰላሌ➛ደብረማርቆስ
ሐ| አዲስ አበባ ➛ አምቦ
መ| አዲስ አበባ ➛ ጅማ

✔️ TA Project (የብረታብረት ፋብሪካ) ➛ $1.9 ቢሊዮን ዶላር

✔️ በርበራ ወደብ ➛ጅግጅጋ➛ድሬድዋ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር ➛ $3 ቢሊዮን ዶላር [በኢሜሬትስ የሚሸፈን]

✔️ የአዋሽ➛ኮምቦልቻ➛ወልድያ/ሐራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ = [$257 ሚሊዮን ዶላር የተያዘ]

✔️ የኮሚዩኒኬሽን ሳተላይት ማምጠቅ ➛ $302 ሚሊዮን ዶላር የተያዘ

[...ይቀጥላል...]

Via Getnet ✍️

29/08/2025
28/08/2025

ኢትዮጵያ ባለራዕይ መሪ አላት - አሊኮ ዳንጎቴ
**************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ተፈረመአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ...
28/08/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደርገው ጉዞ አንድ ሌላ እጥፋት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ፈርመናል ነው ያሉት።

2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ይህ ሜጋ ፕሮጀክት በዓመት እስከ ሶስት ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ኢትዮጵያን ከዓለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ እንደሚያደርጋት ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀው፤ ለዘመናት ለተፈተኑት አርሶ አደሮቻችን አስተማማኝ የማዳበሪያ አቅርቦት በማረጋገጥ ለምግብ ሉዓላዊነት መንገዳችንም ወሳኝ ርምጃ መውሰዳችንን ያመላክታል ብለዋል።

በመላው አኅጉሩ ኢትዮጵያ ያላትን ተወዳዳሪነት በማጠናከር ሕዝባችንን እና ነጋችንን የሚጠቅሙ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንቶችን የመከወን ጽኑ አቋማችንን ያሳያል ነው ያሉት።

የዛሬውን የፊርማ ስምምነት ተከትሎ ፋብሪካው በሚቆምበት ስፍራ ፕሮጀክቱን በይፋ የምናስጀምር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን ታሪካዊ ጉዞ ጀምረናል ሲሉ ገልጸዋል።

ለአርሶአደሮቻችን፣ ለኢኮኖሚያችን እና ለኢትዮጵያ ነገ ስንል እንጨርሰዋለን በማለት አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቆንጆ Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share