Dr Abrham T Bemrew IM resident

Dr Abrham T Bemrew IM resident Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr Abrham T Bemrew IM resident, Digital creator, Addis Ababa , Tikure Anbsa Hospital, Addis Ababa.

እስከ አሁን ድረስ በማህበራዊ ሚዲያ ቻናላዬ ላይ ታካሚዎችን ለማገዝ የጤና ነክ መረጃዎችን በማጋራት ቆይቻለሁ።
አሁን ደግሞ በተመረጡ የግል ህክምና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራሁ እገኛለሁ።

እናተም ርህራሔ በ ተሞላበት ግልጽ
በ ሆነ ቋንቋ ና ቀለል ባለ አካሄድ ባለቤቱን ያሳተፈ ህክምና ከ ፈልጉ እኛ ጋር ይምጡ።
ስልክ ቁጥር፡+251931802532

🚨 ሄለን ህይወቷን ከሚያሳጣ ህመም ተርፋለች… ነገር ግን ከህመሟ በኋላ የጀመረውን ህመም ማንም አላሰበም። 💔ሄለን የ14 ዓመት የሀይስኩል ተማሪ ነበረች። 🧒🏽🎒አንድ ቀን ድንገት የእግሮቿ መስ...
10/08/2026

🚨 ሄለን ህይወቷን ከሚያሳጣ ህመም ተርፋለች… ነገር ግን ከህመሟ በኋላ የጀመረውን ህመም ማንም አላሰበም። 💔

ሄለን የ14 ዓመት የሀይስኩል ተማሪ ነበረች። 🧒🏽🎒
አንድ ቀን ድንገት የእግሮቿ መስነፍ ጀመረ። በቀናት ውስጥ ግን ሁኔታዋ እየተባባሰ ሄደ። በመጨረሻም በከባድ ሁኔታ ሆስፒታል ገብታ ICU ውስጥ ለሦስት ወራት ያህል ቆየች። 🏥

ራሷን በራሷ መተንፈስ እስከማትችልበት ደረጃ ደርሳ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ እርዳታ አስፈልጓት ነበር። 🫁
ለቤተሰቧ ያ ጊዜ ቀላል አልነበረም። 💔
ግን ሄለን ታገለች። 💪❤️

ከብዙ ወራት የህክምና እና የክትትል ጊዜ በኋላ በመጨረሻ ከህመሟ አገገመች። 🙏❤️
15ኛ ዓመቷንም በሆስፒታሉ ICU ውስጥ ሳለች አክብራ ነበር። 🎂🏥

የእሷ ታሪክ በሆስፒታሉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽም ተጋርቶ ነበር። ዓላማውም ሌሎችን ለማበረታታት፣ ለቤተሰቧ ድጋፍ ለመስጠት እና የህክምና ትግሏን ለማሳየት ነበር። ❤️🤝

እና ሄለን አገግማ ወደ ትምህርት ቤት ተመለሰች። ❤️🎓
ሁሉም ነገር አልቋል ብለን እናስብ ነበር።
ግን ለሄለን ህመሙ እዚያ አላበቃም። 💔
ቀድሞ ይቀርቧት የነበሩ ጓደኞቿ ከእሷ መራቅ ጀመሩ።

በትምህርት ቤት ስትሄድ የማታውቃቸው ሰዎች ስለእሷ ማውራትና መጠቋቆም ጀመሩ። 👀💬
ቀድሞ ከጓደኞቿ ጋር በመሳቅ ወደ ትምህርት ቤት ትሄድ የነበረችው ሄለን፣ አሁን ግን ብዙ ጊዜ ብቻዋን መሄድ ጀመረች። 😔💔

ከበሽታው አካላዊ በሽታ ተሻሽላለች፤ ነገር ግን ከህመሟ በኋላ የመጣው መገለል እና ብቸኝነት አሁንም እየፈተናት ነው። 💔

እዚህ ላይ አንድ ጠቃሚ ጥያቄ እንጠይቅ። 🤔
የታካሚን ታሪክ ለመልካም ዓላማ ስናጋራ፣ ከዚያ በኋላ በታካሚው ሕይወት ላይ ምን እንደሚፈጠር አስበን እናውቃለን? 🤔

ሀኪሞቿና ቤተሰቧ ታሪኳን ለበጎ ዓላማ አጋርተውት ሊሆን ይችላል። ❤️
ነገር ግን መልካም ዓላማ ሁልጊዜ የሚያመጣውን ውጤት አናውቅም ። ⚠️

አንድ ፎቶ ወይም አንድ ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ ከተጋራ በኋላ ከታካሚው ጋር አብሮ ሊኖር ይችላል። 📱🌐

ዛሬ የምንለቀው ታሪክ ነገ በታካሚው ላይ ያልጠበቅነውን ነገር ሊያመጣ ይችላል፤ ብሎም ሰዎች በምን መልኩ እንደሚያጠቁን አናውቅም። ⚠️💔

ዛሬ የምንለጥፈው ፎቶ ነገ በብዙ ሰዎች እጅ ሊገባ ይችላል። 📸🌍
ስለዚህ የታካሚ ግላዊነትን መጠበቅ የህግ ወይም የሙያ ግዴታ ብቻ አይደለም። ⚖️

የታካሚው የመዳን ሂደት አንዱ አካል ነው። ❤️‍🩹
ሰዎች ስለጤናቸው፣ ስለበሽታቸው እና ስለህክምናቸው ከተያያዙ የጤና ባለሙያዎች ውጭ ማንንም እንዳያውቅ የመወሰን መብት አላቸው። 🔒

ይህንን መብት ማክበር ደግሞ ከእኛ ከሀኪሞችና ከሁሉም የጤና ባለሙያዎች መጀመር አለበት። ❤️🙏
ምክንያቱም ታካሚው የሚፈልገው ህክምና ብቻ አይደለም። 🩺
ክብር፣ ግላዊነት እና ከህመሙ በኋላ የመደበኛ ሕይወቱን በነፃነት የመኖር መብትም ያስፈልገዋል። ❤️‍🩹🔒

🙏 የታካሚን ታሪክ ከማጋራታችን በፊት፣ “ይህ ልጥፍ ዛሬ ምን ያህል ሰዎችን ያስተምራል?” ብቻ ሳይሆን፣ “ነገ በታካሚው ሕይወት ላይ ምን ያሳድራል?” ብለንም እንጠይቅ። 🤔❤️

ይህ ታሪክ ከእውነተኛ ሁኔታ የተነሳ ቢሆንም፣ የታካሚዋን ማንነትና ግላዊነት ለመጠበቅ ስም እና ሌሎች የሚለዩ ዝርዝሮች ተቀይረዋል። 🔒
እናንተስ የህክምና ኬዛችሁ በማህበራዊ ሚዲያ እንዲጋራ ትፈቅዳላችሁ ወይ? 🤔👇
🔒 🩺 ⚖️ ❤️ 🙏

🚨 "ከተጀመረ አይቋረጥም... ስለዚህ አልጀምርም!"ይህን አባባል ቀላል የማይባል የደም ግፊት ያለባቸው ታካሚዎችን ገምግመን መድኃኒት እንዲጀምሩ ስንመክር ብዙ ጊዜ የምንሰማው መልስ ነው።ይህ ...
05/08/2026

🚨 "ከተጀመረ አይቋረጥም... ስለዚህ አልጀምርም!"

ይህን አባባል ቀላል የማይባል የደም ግፊት ያለባቸው ታካሚዎችን ገምግመን መድኃኒት እንዲጀምሩ ስንመክር ብዙ ጊዜ የምንሰማው መልስ ነው።

ይህ አስተሳሰብ የመጣው በአጋጣሚ አይደለም። የደም ግፊትን እንደ ሌሎች ጊዜያዊ በሽታዎች በራሱ ይጠፋል ብሎ ከማሰብ፣ ወይም መድኃኒት ካልጀመርኩ ችግሩ ይጠፋል ብሎ ከመጠበቅ የሚመነጭ ነው።

በተጨማሪም የደም ግፊት ብዙ ጊዜ ምንም ዓይነት ምልክት ስለማይሰጥ፣ "ደህና ነኝ!" ብሎ ማሰብ ብዙ ሰዎችን ያሳስታል።

ነገር ግን የደም ግፊት በዝምታ የሚጎዳ በሽታ ነው። ❤️🫀

✅ በቀደም ብሎ መድኃኒት መጀመር እና በጥቂት መድኃኒት በጥሩ ሁኔታ መቆጣጠር ይቻላል።

❌ ነገር ግን ሕክምናውን ከዘገዩ፣ በኋላ ላይ የደም ግፊቱ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፤ ይህም ዛሬ የፈራችሁትን መድኃኒት በብዛት ወይም በተለያዩ አይነቶች እንድትወስዱ ሊያደርግ ይችላል።

💡 መድኃኒትን በጊዜው መጀመር ድክመት አይደለም፤ ኩላሊትን፣ ልብን፣ አንጎልን እና ዓይንን ከዘላቂ ጉዳት የሚጠብቅ ብልህ ውሳኔ ነው።

👨‍⚕️ ዶ/ር አብርሃም ተስፋሁን የውስጥ ደዌ ሬዝዳንት ሐኪም

#የደምግፊት #ጤና

Dr Abrham T Bemrew IM resident  🚨 "ክብደትዎ እየቀነሰ፣ ልብዎ በፍጥነት እየመታ፣ ሙቀትንም መቋቋም እየከበደዎት ነው? ምናልባት የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት (Hyperthyr...
04/08/2026

Dr Abrham T Bemrew IM resident


🚨 "ክብደትዎ እየቀነሰ፣ ልብዎ በፍጥነት እየመታ፣ ሙቀትንም መቋቋም እየከበደዎት ነው? ምናልባት የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት (Hyperthyroidism) ሊሆን ይችላል! ቶሎ ይወቁት፤ በጊዜው ከታወቀ እና ሕክምና ከተደረገለት በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል።" ⚠️

የ እንቅርት ሆሮሞን መብዛት ምንድን ነው?

የ እንቅርት ሆርሞን መብዛት በ ታይሮይድ እጢ የሚመነጨው የ ሆርሞን ከ መጠን በላይ ሲሆን፣ ይህም የ ሰውነት ስርዓተ ልውውጥን (Metabolism) ያዛባል።

ምልክቶቹ
• የ ሰውነት ክብደት መቀነስ
• ሙቀት አለመቋቋም
• ድካም
• የ ልብ ምት መዛባት
• እንቅልፍ ማጣት
• የ ፀባይ መቀያየር
• የ አይን መጉላት

ህክምና ባይደረግ ሊከሰቱ የሚችሉ ሁኔታዎች
• የ ልብ ስርዓት መዛባት እስከ ልብ ድካም ድረስ
• የ አጥንት መሳሳት
• የ ሴቶች የወር አበባ መዛባት
• የ ስኳር ህመም ቁጥጥር መበላሸት
• የ ስነ አዕምሮ ችግሮች

ለ ታይሮይድ ሆርሞን መብዛት አጋላጭ
ምክንያቶች

• Graves disease ግሬቭስ ህመም
• Toxic adenoma አመንጪ የ እንቅርት እጢ
• Multinodular toxic goiter ብዛት ያለው አመንጪ የ እንቅርት እጢ
• Thyroiditis የ እንቅርት ሆርሞን እጢ መቆጣት
• አንዳንድ መድሀኒቶች (ለምሳሌ Amiodarone)

🩺 የሚደረጉ ምርመራዎች

የ እንርቅርት ሆርሞን ፓናል ምርመራ TSH FT3 FT4

• TSH receptor antibody
• TPO
እነዚህ ምርመራዎች የ እንቅርት ሆርሞን መብዛቱን ለማረጋገጥ ይረዳሉ። እንዲሁም TSH receptor antibody የ Graves disease መኖሩን ለማወቅ ይረዳል።

ህክምናው

• Methimazole ሜቲማዞል
• Propylthiouracil (PTU) ፒትዮ
የ ተመረተው ሆርሞን በ ልብ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ
Propranolol ፕሮፕራኖል
Atenolol አቴኔሎል

• የ ቀዶ ህክምና
• የ ጨረር ህክምና

#ሸዋጅ ልምዶች
• "የ ታይሮይድ እንቅርት የለብኝም እና የ ሆርሞን መብዛት አይኖርብኝም" ብሎ ማሰብ

• የ ሆርሞን መቀነሻ መድሀኒት ወስዶ ለውጥ ሲኖር ያለ ሀኪም ግምገማ ማቆም

• የነበረ እንቅርት የ ቅርጽ ወይም የ እድገት ባህሪ ለውጥ ሲኖር ህክምና አለመፈለግ

ሲጠቃለል

የ ታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ምልክቶቹ ግልጽ ያልሆኑ ሊሆኑ ቢችሉም፣ የ ህይወትን ጥራት እና ጤና በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዱ ይችላሉ። በተለይም በ የደም ግፊትና በ ልብ ስርዓት ላይ ከባድ ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
📢 ይህ መረጃ ጠቃሚ ከሆነ ለቤተሰብዎና ለጓደኞችዎ Share ያድርጉ። ጤናን ማወቅ መከላከል ነው!

ማስተባበያ: ይህ ጽሑፍ ለአጠቃላይ የጤና መረጃ ብቻ ነው፤ የሀኪምና የታካሚ ግንኙነትን አይተካም።

👨‍⚕️ ዶ/ር አብርሃም ተስፋሁን የውስጥ ደዌ ሬዚዳንት




🚨 "ዶክተር... መድሀኒት አልጀምርም! በምግብ ብቻ አስተካክለዋለሁ... አንዴ ከጀመርኩ ዕድሜ ልኬን መውሰድ አለብኝ አይደል?" 🤔⚠️ ይህ እምነት ብዙ ሰዎችን ለስትሮክ፣ ለልብ ድካም እና ለ...
30/07/2026

🚨 "ዶክተር... መድሀኒት አልጀምርም! በምግብ ብቻ አስተካክለዋለሁ... አንዴ ከጀመርኩ ዕድሜ ልኬን መውሰድ አለብኝ አይደል?" 🤔

⚠️ ይህ እምነት ብዙ ሰዎችን ለስትሮክ፣ ለልብ ድካም እና ለኩላሊት ጉዳት እየዳረገ ነው!

ይህ አባባል እኛ ዶክተሮች የደም ግፊት መኖሩን አረጋግጠን መድሀኒት ልንጀምር ስንል ብዙ ጊዜ የምንሰማው ነው።

አዎ፣ ለልብ ተስማሚ አመጋገብ የደም ግፊትን ሊቀንስ ይችላል። ሆኖም አንተ/አንቺ በእውነት ሳይንሳዊ መረጃን ተከትለህ/ተከትለሽ ነው የምታደርገው? ወይስ በቲክቶክ እና በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወሩ በሳይንስ ያልተደገፉ "ተአምራዊ መጠጦች" ላይ ተስፋ አድርገሃል?

ሲቀጥል፣ የሕይወት ዘይቤ ለውጥ እና አመጋገብ ብቻ የሚበቃው የደም ግፊት መጠን ከ130 -140/80-89 ሚሜ በታች ሲሆን እና ሌላ ተጨማሪ የልብ ወይም ተያያዥ የጤና ችግር ከሌለ ነው።

ከ3 እስከ 6 ወር የሕይወት ዘይቤ ለውጥ በኋላ የደም ግፊት መጠኑ ከ130/80 በታች የማይወርድ ከሆነ ግን መድሀኒት መጀመር ይኖርበታል።

የደም ግፊት መጠናቸው 140/90 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ እና እንደ የልብ ድካም፣ የልብ ደም ስር መዘጋት፣ ስትሮክ፣ የረጅም ጊዜ የኩላሊት በሽታ፣ የልብ መድከም ወይም ከደም ግፊት ጋር የተያያዘ የዓይን ሬቲና ጉዳት ያለባቸው ሰዎች የደም ግፊት መድሀኒት መጀመር ይኖርባቸዋል።

💬 **እርስዎስ ይህን "አንዴ ከጀመርኩ አልተወውም" የሚለውን አስተሳሰብ ከዚህ በፊት ሰምተው ያውቃሉ? አስተያየትዎን ያጋሩ።

🔄 ይህ መረጃ አንድን ሰው ከስትሮክ ሊያድን ይችላል፤

ሼር ያድርጉ።

ምንጭ: የ አሜሪካ ልብ ህክምና ማህበር

ማሳሰቢያ: ይህ ጽሑፍ ለጤና ግንዛቤ ማሳደግ ብቻ ነው፤ የሀኪም-ታካሚ ግንኙነትን አይተካም።

ዶ/ር አብርሃም የውስጥ ደዌ ሬዝዳንት ሀኪም

#የደምግፊት

#የልብጤና





#የጤናግንዛቤ

🌍 የደም ግፊት (Hypertension) – ጸጥ ያለው ወረርሽኝ-በ  #ዓለም 1.28 ቢሊዮን ሰዎች የ ደም ግፊት አለባቸው በ  #ኢትዮጵያ ደግሞ ከ 5 ሰዎች አንዱ ነገርግን አብዛኞቻችን እስከ...
28/07/2026

🌍 የደም ግፊት (Hypertension) – ጸጥ ያለው ወረርሽኝ

-በ #ዓለም 1.28 ቢሊዮን ሰዎች የ ደም ግፊት አለባቸው በ #ኢትዮጵያ ደግሞ ከ 5 ሰዎች አንዱ ነገርግን አብዛኞቻችን እስከ ስትሮክ ድረስ አናውቅም ። ይህን አስፈላጊ መረጃ ከ ዶር አብርሃም ያንብቡ ።

ይህ በሽታ በየአመቱ ወደ 10.4 ሚሊዮን ሞት ያደርሳል – ይህም ከልብ ህመም፣ ከስትሮክ (ጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ/መዘጋት) እና ከኩላሊት ጉዳት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥሩ ከፍተኛ ሲሆን፣ ከአምስት ሰዎች አንዱ የደም ግፊት እንዳለበት ይታወቃል። ግን የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ህክምና የሚጀምሩት ውስብስብ ችግር ከተፈጠረ በኋላ ነው።

---

🩺 1. ፍቺ (Definition) እና ምርመራ (Evaluation)

የደም ግፊት ማለት ደም በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጥረው ግፊት ከመደበኛው በላይ መጨመር ነው። ብዙ ጊዜ ምልክት ስለሌለው "ጸጥ ያለ ገዳይ" (Silent Killer) ተብሎ ይጠራል።

እንዴት ይታወቃል? 🤔

· በቤት ውስጥ በእጅ ላይ በሚታሰር መለኪያ (Sphygmomanometer)።
· በህክምና ተቋም ተደጋጋሚ በሆነ መለካት (በአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቀናት)።

📊 ጤናማ የደም ግፊት መጠን ስንት ነው?

ደረጃ ሲስቶሊክ (ከፍተኛ) ዳያስቶሊክ (ዝቅተኛ)
✅ ጤናማ < 120 ሚሜ እና < 80 ሚሜ
⚠️ ከፍ ያለ (Elevated) 120–129 ሚሜ እና < 80 ሚሜ
🟡 ደረጃ 1 (Stage 1) 130–139 ሚሜ ወይም 80–89 ሚሜ
🔴 ደረጃ 2 (Stage 2) ≥ 140 ሚሜ ወይም ≥ 90 ሚሜ
🚨 የድንገተኛ ህክምና አስፈላጊ ≥ 180 ሚሜ ወይም ≥ 120 ሚሜ

---

💣 2. ውስብስቦች (Complications) – "የጊዜ ቦንብ"

የደም ግፊት ህመም በውስጣችን እያለ ብዙ ጊዜ ምልክት አያሳይም፣ ነገር ግን ካልታከመ በማንኛውም ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፦

· 🧠 የጭንቅላት ደም ስር መዘጋት / መፍሰስ (Stroke)
· ❤️ የልብ ድካም እና የልብ ደም ስር መዘጋት (Heart Attack & Failure)
· 👁️ የዓይን መጥፋት (Retinopathy)
· 🫘 የኩላሊት ጉዳት (Kidney Failure) – ዳያሊስስ እስከሚያስፈልግ ደረጃ
· 🦵 የእግር የደም ቧንቧ መዘጋት (Peripheral Artery Disease)

---

🔬 3. መንስኤ (Etiology)

ሁለት ዋና ዋና አይነቶች አሉ፦

1️⃣ የመጀመሪያ ደረጃ (Primary/Essential) – 90% የሚሆነው

· መንስኤው በትክክል የማይታወቅ።
· ብዙውን ጊዜ ከ30 አመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ይከሰታል።
· ከቤተሰብ ታሪክ፣ ከእድሜ እና ከአኗኗር ዘይቤ ጋር ይዛመዳል።

2️⃣ ሁለተኛ ደረጃ (Secondary) – 10% የሚሆነው

· መንስኤው የሚታወቅ ሲሆን፣ ከሌሎች በሽታዎች ጋር የተያያዘ ነው፦
· የተለያዩ የሆርሞን መዛባቶች (ለምሳሌ ታይሮይድ)🧬
· የእንቅልፍ እስትንፋስ መቋረጥ (Sleep Apnea) 😴
· የተወሰኑ መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት
· ከእርግዝና ጋር የተያያዘ (Preeclampsia) 🤰

---

🧪 4. ምርመራ (Laboratory Workup)

አንዴ የደም ግፊት ከተረጋገጠ፣ ሐኪምዎ የሚከተሉትን ምርመራዎች ያዛል፦

· 🩸 የደም ምርመራ (CBC፣ RFT፣ Electrolytes) – የኩላሊት እና የደም ህዋስ ጤናን ለማወቅ።
· 🫘 የስኳር ምርመራ (FBS) – የስኳር በሽታ ለማወቅ።
· 🧈 የኮሌስትሮል ምርመራ (Lipid Profile) – ለልብ ስጋት ግምገማ።
· ❤️ የልብ ኤሌክትሪክ (ECG) እና አልትራሳውንድ (Echocardiography) – የልብ መጠን እና ስራ ለመመልከት።
· 🧬 የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ ( TFT)

---

💊 5. ህክምና (Treatment / Rx)

ህክምናው ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፦

🥗 ሀ) የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ (Lifestyle Modification) – የመጀመሪያው እርከን

· 🏃 የአካል እንቅስቃሴ – በሳምንት አብዛኛው ቀን ቢያንስ 30 ደቂቃ መራመድ።
· ⚖️ ክብደት መቀነስ – 5-10% ክብደት መቀነስ ግፊትን በእጅጉ ይቀንሳል።
· 🧂 የጨው መጠን መቀነስ – በቀን ከሁሉም ምግብ የምናኘው የ ጨው መጠን ከ 2300 ሚግ በታች።
· 🍷 አልኮል እና ማጨስ መቀነስ / ማቆም – ሙሉ በሙሉ ማቆም ጥሩ ነው።
· 🥦 ጤናማ አመጋገብ – ፍራፍሬ፣ አትክልት እና አነስተኛ ስብ ያላቸውን ምግቦች መመገብ።

💊 ለ) መድሀኒት (Pharmacological Therapy)
ሐኪምዎ ከታች ከተዘረዘሩት መድሀኒቶች አንዱን ወይም ጥምር መድሀኑት ሊያዝ ይችላል፦

· አምሎዲፒን (Amlodipine) – የካልሲየም ቻናል አጋጅ
· ኢናላፕሪል (Enalapril) – የኤሲኢ አጋጅ (ACE inhibitor)
· ሃይድሮክሎሮቲያዚድ (Hydrochlorothiazide) – የሽንት ማስወጣት መድሀኒት (Diuretic)
· ካርቬዲሎል (Carvedilol) / ሜቶፕሮሎል (Metoprolol) – የቤታ አጋጆች (Beta-blockers)
· ሜቲልዶፓ (Methyldopa) – በተለይ ለነፍሰ ጡር እናቶች ደህንነቱ የተመሰከረ ነው።

⚠️ ማስታወሻ፦ መድሀኒቱን ያለ ሐኪም ትዛዝ አያቁሙ እና መጠኑን በራስዎ አይለውጡ!

---

🛡️ 6. መከላከያ (Prevention)

የደም ግፊትን መከላከል ከማከም በጣም ቀላል ነው። እነዚህን ተግባራት ይከተሉ፦

· 📏 የደም ግፊትዎን በየጊዜው ይለኩ – ከ18 አመት ጀምሮ ቢያንስ በየአመቱ አንድ ጊዜ።
· 🥗 ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ (DASH አመጋገብ በመባል የሚታወቀው)።
· 🧘 ውጥረትን (Stress) ይቆጣጠሩ ።
· 🚭 ትምባሆ እና አልኮልን ያስወግዱ።

---

📝 ማጠቃለያ

የደም ግፊት በሽታ በጣም የተስፋፋ፣ ነገር ግን በቀላሉ ሊታወቅ እና ሊታከም የሚችል በሽታ ነው። "ጸጥ ያለ ገዳይ" ቢባልም፣ ጥቂት ቀላል እርምጃዎችን በመውሰድ ጤናማ ህይወት መኖር ይቻላል።

ዛሬውኑ የደም ግፊትዎን ይለኩ፣ ለራስዎ እና ለቤተሰብዎ የወደፊቱን ጤና ያረጋግጡ! ❤️🏥

---

⚠️ ማስተባበያ (Disclaimer)
ይህ ጽሑፍ ለአጠቃላይ የጤና መረጃ እና ትምህርት ብቻ ነው የተዘጋጀው። የሀኪም-ታካሚን ግንኙነት አይተካም። ማንኛውም የጤና ችግር ካጋጠምዎ ወደ ቅርብ የጤና ተቋም በመሄድ ሙያዊ ምክር ያግኙ።

---

✍️ አዘጋጅ፦ዶ/ር አብርሃም ተስፋሁን
የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሬዝዳንት ሀኪም 🩺



#ጤና
#የደምግፊት
#ኢትዮጵያ

☕️ ቡና እና የልብ ጤና ❤️    ቡና መጠጣት የ  ልብን ጤና ይጠብቃል ወይስ ይጎዳል?ይህ በየቀኑ በጣም የምጠየቀው ጥያቄ ነው።መልሱ ግን "አዎ" ወይም "አይ" ብቻ አይደለም።☕️ ቡና ለአን...
27/07/2026

☕️ ቡና እና የልብ ጤና ❤️

ቡና መጠጣት የ ልብን ጤና ይጠብቃል ወይስ ይጎዳል?

ይህ በየቀኑ በጣም የምጠየቀው ጥያቄ ነው።

መልሱ ግን "አዎ" ወይም "አይ" ብቻ አይደለም።

☕️ ቡና ለአንዳንድ ሰዎች ችግር ላያመጣ ይችላል፤ ለሌሎች ግን የልብ ምትን ወይም የደም ግፊትን ሊጨምር ይችላል።

ለምን?

ሰውነታችን ካፌይንን በተለያየ ፍጥነት ይቀይራል።

👉 አንዳንዶች "ፈጣን metabolizer" ናቸው፤ ካፌይኑ በፍጥነት ይወጣል።

👉 አንዳንዶች ግን "ዘገምተኛ metabolizer" ናቸው፤ ካፌይኑ ረጅም ጊዜ በሰውነት ይቆያል።

ስለዚህ ሁሉም ሰው እኩል ምላሽ አይሰጥም።

❤️ ቡና በልብ ላይ ምን ተጽእኖ አለው?

✅ የልብ ምትን ለጊዜው ሊጨምር ይችላል።

✅ የደም ግፊትን ለአጭር ጊዜ ሊያሳድግ ይችላል፤ በተለይ ቡና በመደበኛነት የማይጠጡ ሰዎች ላይ።

✅ አብዛኛው ሰው በመጠነኛ መጠን ሲጠጣ የልብ አመታት መዛባትን (Arrhythmia) አያመጣም።

✅ አንዳንድ ጥናቶች ደግሞ መጠነኛ ቡና መጠጣት ለስትሮክና ለልብ ህመም ተጋላጭነትን ሊቀንስ እንደሚችል ያሳያሉ።

☕️ ስንት ሲኒ ይመከራል?

✔️ በቀን ከ400 mg በታች ያለ ካፌይን ለአብዛኛው ጤናማ ሰው ደህና ነው።

✔️ ይህ በአማካይ 3–5 ሲኒ የኢትዮጵያ ቡና ሊሆን ይችላል (እንደ ጠንካራነቱ ይለያያል)።

⚠️ መቼ መጠንቀቅ አለብዎት?

❌ ቡና ከጠጡ በኋላ የልብ ምት በጣም ከጨመረ

❌ የልብ ትርታ ከተዛባ

❌ የደረት ህመም ወይም ማዞር ከተፈጠረ

➡️ የቡና መጠንዎን ይቀንሱ እና ሐኪም ያማክሩ።

✅ መደምደሚያ

☕️ ቡና ጎጂ አይደለም፤ መድኃኒትም አይደለም።

"መጠን" እና "የራስዎ ሰውነት ምላሽ" ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ናቸው።

☕️❤️ ይጠጡ... ግን በመጠን!

📌 ይህን መረጃ ለቤተሰብዎና ለጓደኞችዎ Share ያድርጉ።

💬 እርስዎ በቀን ስንት ሲኒ ቡና ይጠጣሉ? ከቡና በኋላ የልብ ምት መጨመር አጋጥሞዎታል? በኮመንት ያጋሩ።

#ቡና #የልብጤና #የደምግፊት #ጤና

🎉🎊 እንኳን ለ100ኛ ዓመት ክብረ በዓል አደረሰ! 🇪🇹🧪በዛሬው ዕለት በተለምዶ "ፓስተር" ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት አክ...
16/07/2026

🎉🎊 እንኳን ለ100ኛ ዓመት ክብረ በዓል አደረሰ! 🇪🇹🧪
በዛሬው ዕለት በተለምዶ "ፓስተር" ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት አክብሯል። 🎂🎉
ላለፉት 100 ዓመታት ተቋሙ፦ 💉 በክትባት ልማትና ምርምር 🔬 በላቦራቶሪ አገልግሎት 🦠 በበሽታ መከላከልና ቁጥጥር 🚨 ድንገተኛ ወረርሽኞችን በመቆጣጠር 📚 በጤና ምርምር
ለኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል። 👏🇪🇹

👨‍⚕️ እንደ ውስጥ ደዌ ሐኪም፣ ተቋሙ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በከፍተኛ ጥራት የሚሰጣቸውን የላቦራቶሪ ምርመራዎች እጅግ እናደንቃለን። 🙏

🧪 ከሚሰጣቸው ጥራት ያላቸው ምርመራዎች መካከል፦

✅ 1. የእንቅርት እጢ ሆርሞን ምርመራ (Thyroid Function Test)
✅ 2. የስርዓተ ተዋልዶ ሆርሞኖች ምርመራ (Testosterone, FSH, LH, Estrogen)
✅ 3. የሽንት ፕሮቲን ምርመራ (Urine Protein)
✅ 4. የስኳር በሽታ የ3 ወር ቁጥጥር ምርመራ (HbA1c)
✅ 5. የቲቢ ባክቴሪያ ማሳደግ (TB Culture) እና የመድኃኒት ተቋቋሚነት ምርመራ 🦠 ይህ ምርመራ የቲቢን በሽታ በከፍተኛ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እና መድኃኒት የተቋቋመ (Drug-resistant TB) መሆኑን ለመለየት በጣም ጠቃሚ ነው።

🌟 ጥራት ያለውን የላቦራቶሪ ምርመራ በተመጣጣኝ ዋጋ ከፈለጉ፣ EPHI (ፓስተር) ከሚመረጡ ተቋማት አንዱ ነው።
🎉 መልካም 100ኛ ዓመት! ለቀጣዮቹም 100 ዓመታት የበለጠ ስኬትና አገልግሎት እንመኛለን። 🇪🇹❤️
👨‍⚕️ ዶ/ር አብርሃም ተስፋሁን የውስጥ ደዌ ሬዝዳንት ሐኪም | ጤና አበረታች

ወደ ሆስፒታል ሲመጡ ጥሩ የሀኪም ታካሚ ግንኙንት እንዲኖራችሁ1. ቀደም ቀድም አለማለት ሀኪሙን አለማዳመጥ ይህም ሀኪሙ ታካሚውን  መጠየቅ ያለበትን እንዳይጠይቅ ያደርጋል ይህም በ ዚያች ባለች...
30/06/2026

ወደ ሆስፒታል ሲመጡ ጥሩ የሀኪም ታካሚ ግንኙንት እንዲኖራችሁ

1. ቀደም ቀድም አለማለት ሀኪሙን አለማዳመጥ ይህም ሀኪሙ ታካሚውን መጠየቅ ያለበትን እንዳይጠይቅ ያደርጋል ይህም በ ዚያች ባለችው አጭር ግዜ ሀኪሙ መጠየቅ ያለበትን ጥያቄ ጠይቆ ታማሚውን ያሳሰበውን ሰምቶ የሚፈለገውን ህክምና ለመስጠት ያስቸግራል

2. ማዳመጥ ከ ሀኪም ጋር ስለ ህመምዎት አለመከራከር ሀኪም የ ራስዎ ጤና እንዲሸሻል የ ሚሻ እንጅ .... ምንም ህመም ባይኖርብዎት ደስ የሚለው እንጅ
ተያዥዥ ችግር አለ ብሎ ሲስረዳዋት ማዳመጥ ና ጥያቄ እንጅ ኧረ እኔ "ኩሊሊት የለብኝም ኮሌስትሮል የለም" ብለው ግንኙነቱን ወደ ክርክር ከ ለወጡትና ለመስማት ካልፈቀዱ በ ግዜ ማግኘት ያለበዎት ህክምና እንዳያገኙ ያደርጋል

3. ከ ምንም በላይ ለ ሀኪሞት ክብር ማሳየት በ ህክምናው ስራዓት እምነት ማሳዳር እዚህ ላይ ጥያቄ ሲጠየቁ በ ስራት መመለስ አለበዎት ማንም ሀኪም ዲስርስፔክት የ ሚያደርግን ታኪሚ ማየት አይፈልግም

4. ህክምናዊ ማብራሪያውን ለ ሀኪሞት መስጠት ሀኪሞ መጠየቅ ያለበትን ጥያቄ ጠይቆ አካላዊ ምርመራ አድርጎ የ ተሰሩትን ምርመራ ገምግሞ ውሳኔ እስኪሰጥ መጠብቅ አንድንድ ታካሚዎች ገና ከ ምርመራ ክፍል እንደገቡ ሀኪማቸው ምን ህመም እንዳላቸው የሚይወስዱትን መድሀኒት ሳያይ" የ ደም ውጤቱ ምንድን ይላል" ይላሉ
ወዳጃ መጀመሪያ ሰላምታ ይቀድማል ብሎም ታካሚውን ከ ህክምና ካርዱ ጋር አንድ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የ እርስዎን የ ምርመራ ውጤት ማረጋግጥ ስራው ነው።

ተጨማሪ
አሁን ስለመጡበት ህመመ ና ተያያዥ ጉዳዮች ሲጠየቁ ካረዱ ላይ አለ ማለት ሀኪሙ እኮ መቸም ካርዱን ይመለከተዋል ግን እናተ ምን ያህል ስለበሽታው እንደምታውቁ አሁን ላይ የ ተለወጥውን ሁኔታ ማውቅ ይፈልጋል።

ዶር ### ይከታተለኛል

ጥሩ ነው ክትትል ማድረገዎ ሆኖም ከ አመት ሁለት በፊት ታዋቂ ዶክተር ጋር ስለቀረቡ በ ሽታው በ ቁጥጥር ስር ውሏል ወይንም ሙሉ ህክምናዊ መረጃ አለ ማለት አይደለም ዛሬ ሌላ ሀኪም ጋር ቀርበዋል ሙሉ የ ማከም ሀላፊነቱን ለ ዛሬው ሀኪም ሊሰጡ ይገባል

እናተም አስተያየታችሁን ጻፏበት

ዶር አብርሃም ተስፋሁን የ ውስጥ ደዌ ሬዝዳንት ሀኪም

For your "Smart Patient" series, I'd use these five:

14/05/2026

በ ኢትዮጵያ የ ተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከ 10 ሰው አንዱ በ ሄፕታተይስ ቢ በሽታ መያዙን ይጠቁማሉ።

😮 የሚገረመው ግን ቫይረሱ እንዳለ የሚያውቁት በ ጣም ጥቂቶች ናቸው።

📌 ለመሆኑ የ ሄፕታተይስ ቢ በሽታ ምንድን ነው?

ሄፕታተይስ ጉበትን በ ተለየ ሁኔታ ከሚያጠቁት ቫይረሶች አንዱ ሲሆን የ ጉበትን ህዋስ ለ ረዥም ግዜ በ ማብግን

የ ጉበት ስራ እንዲስተጓገል በ ማድረግ እስከ ጉበት ካንሰር ያመጣል።
📌 መተላለፉ መንገዱስ

🩸 በ ዋናነት በ ሰውነት ፈሳሽ ማለትም በ ደም በ ግንኙነት
🤰 እንዲሁም በ እርግዝና ከ እናት ወደ ልጅ

📌 ምልክቱ

በ ግዜዊነት ቫይረሱ ሲይዘን

ትኩሳት
የ ምግብ ፍላጎት መቀነስ
የ ቀኝ ሆድ ላይኛው ክፍል ህመም
ማስመለስ
አይን ቢጫ መሆን

📌 በ ረዥምነት ቫይረሱ ሲኖር

አንድ ሰው ምርመራ እስካላደረገ ድረስ ሄፕታተይስ ቢ እንዳለበት ላያወቅ ይችላል።
⚠️ ሆኖም ቫይረሱ ጉበት መጒዳት ሲጀምር

ድካም
የ ሆድ እብጠት
ደም ማስመለስ
የ ሰገራ መጥቁር
ግዜአዊ የ ሆነ ንቃት መቀነስ

📌 ከ ጉበት ውጭ የ ሆኑ የ ሰውነት ክፍሎች ሲጠቁ ደግሞ

የ ተለያዩ የ ቆዳ ላይ ለውጦች
ቁርጥማት
የ ኩላሊት ህመም

📌 የ ሚደረጉ ምርመራዎች

🧪 hep s antigen
🧪 hep e antigen
🧪 hep core antibody
🧪 viral load
📊 እነዚያ ምርመራዎች ቫይረሱ በ ሰውነት ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ይገልጻሉ።
የ ጉበት ኢንዛይም ምርመራ
የ ሆድ/ጉበት አልትራሳውንድ
የ ጉበት ጠባሳን ለመለየት ፋይብሮ ስካን (fibro scan) ምርመራ
🧾 እንዲሁም ሌሎች መደበኛ ምርመራዎች

📌 ህክምናው

💊 በ ግዜአዊነት ከሆነ የ ድጋፍ ህክምና
📅 በ ረዥም ግዜ ቫይረሱ ካለ
🩺 ከ 3 እስከ 6 ወር ህክምናው ክትትል
🧪 የ ቫይረስ መጠን (viral load)
🧫 የ ጉበት ኢንዛይም መጠን
🖥️ የ ሆድ/ጉበት አልትራሳውንድ ምርመራ
💉 በ ህክምናው ክትትል መድሀኒት ያስፈልጋል ሲባል
💊 መድሀኒት መውሰድ

📌 እንዴት መከላከል ይቻላል?

🛡️ ቫይረሱ የሌለበት ሰው ክትባት መውሰድ ይችላል።
በተለይ
የ ጤና ባለሙያ
ያልተጠበቀ ግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያደርጉ
ለ ሄፕታተይስ ታካሚ እንክብካቤ የሚያደርጉ ሰዎች

በ ኢትዮጵያ ከ 2007 ዓም ጀምሮ ለ ህፃናት ክትባት ይሰጣል።

📌 ሸዋጅ ልምዶች

በ ህይወት ዘመን አንዴም ቢሆን የ ሄፕታተይስ ቢ ምርመራ አለማድረግ

ቫይረሱ መኖሩን እያወቅን ምንም የ ህመም ስሜት አይሰማንም በማለት ክትትል ማቆም

በ ቤተሰብ ውስጥ የ ሄፕታተይስ ቢ ታካሚ እያለ ምርመራ አለማድረግ ና ክትባት አለመውሰድ

መድሀኒት እየወሰዱ ጤና ሲሸሻል ማቆም

📌 ሲጠቃለል

ሄፕታተይስ ቢ በ ስፋት በ ማህበረሰቡ ውስጥ ያለ ግን ደግሞ ያልታወቀ የ ሚተላለፍ ጤና የሚጎዳ ተላላፊ በሽታ ነው።
📖 ይህ ጹህፍ ለ ጤና ግንዛቤ እንጅ የ ሀኪም ታካሚ ግንኙነትን አይተካም።
✨👨‍⚕️ ዶ ር አብርሃም ተስፋሁን 👨‍⚕️✨
🩺 የ ውስጥ ደዌ ሬዝዳንት ሃኪም 🏥

03/04/2026

Address

Addis Ababa , Tikure Anbsa Hospital
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Abrham T Bemrew IM resident posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share