15/02/2026
አስቸኳይ ጥሪ ለሀዳሮ ጡንጦ ወረዳ መንግስት ሠራተኞች በሙሉ
የከምባታ ዞን አመራር የለመደውን የሸፍጥ አዋጅ በመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ላይ አውጥቷል
እንደሚታወቀው የከምባታ ዞን በሌላ ሰው ትከሻ ቆሞ ረዥም እየመሰለ ኖሯል አሁንም ረዥም ለመምሰል እየጠራ ይገኛል። ከዚህ በፊትም ለዱራሜ ከተማ ኮብል ስቶን ንጣፍ ስራ እንደ ዞን የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ላይ ተፈርዶበት ሌላው ወረዳዎች በከፊል አንዳንድ ወረዳዎች እምቢ ስሉ ሀደሮ ጡንጦ እና ሀዳሮ ከተማ ደመወዙን መስዋዕት አድርጎ ሰርቷል።
ይህ ብቻ አይደለም በሚገርም ሁኔታ አምባርቾ ተራራ ፣ህጋ ት/ቤት እና ከምባታ ቴሌቪዥን የመሳሰሉት ሁሉም የተመሠረተው በመንግሥት ሰራተኛ ደመወዝ መወጫ እና የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ለማዳበሪያ ዕዳ ተቆርጧል እየተባለ በዞን ማዕከል በማስቀረት ነው።
ይህ አልበቃ ያለው የከምባታ ዞን አመራር የከምባታ ህልውና እና ማንነት ጉዳይ የሆነው የአምበርቾ ኢኮ ቱሪዝም ልማት በሚል ከዞኑ አጠቃላይ መንግስት ሠራተኞች የ1ወር ደመወዝ ለመቁረጥ አስተባባሪ ኮሚቴ ወስኗል። ከአጠቃላይ አመራር ጋርም የጋራ ተደርጓል።
ከሚቀጥለው ሰኞ ቀን ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች ወይይት መድረክ ለማካሄድ የአመራር ስምሪትም ተሰጥቷል።
መንግስት የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ችግር ለመደገፍ ከሌላው በጀት ድጋፍ እያደረገ ባለበት ወቅት ገበያ መረጋጋት እንኳን ያልቻለው የከምባታ ዞን የመንግስት ሠራተኛ ደመወዝ ለመቁረጥ ራዕይ አልባ አስተባባሪ ኮሚቴ ወስኗል።
ሀደሮ ጡንጦ ወረዳን በሚመለከት የከምባታ ዞን ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል።
ሀ) ከዚህ በፊት ያልተከፈለ 28% በሌላ ጊዜ ያልተከፈለ 50% የጥር ወር ደግሞ 50% የመንግስት ሠራተኛ ደመወዝ ያልተከፈለ ወረዳ ነው።
ይህ እንኳን ሰይቆረቁረው አሁን ለልማት ደመወዝ ለመቁረጥ መጥተዋል።
ለ) ለወረዳው በየ ወሩ መውረድ ያለበት ወጪ መርጃ 25,000,000 ሲገባው 16,000,000 ብቻ እያወረደ መዋቅሩ ስቃይ ላይ ነው ያለው።
ሐ) ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ወጪ መርጃ ስወርድ ስራ ማስኬጃ አብሮ አይወርድም።
መ) ስራ ግብር በሚመለከት እንዲሁም ከመንግሥት ሰራተኛ የሚሰበሰበው እዛው ዞን ላይ ነው የሚቀረው። ምላሽ ያልተገኛ ጉዳይ ነው።
ሠ) የወረዳ ገቢዎች ያልሰበሰቡትን የሰራተኛ ስራ ግብር ሰብስበነል ተብሎ ሪፖርት ይደረጋል።
ረ) በየአመቱ በምክር ቤት የጸደቀውን ካፕታል ፕሮጀክት ገንዘብ ከሽ የለም እየተባለ እዛው ዞን ማዕከል ለሌላ ዓላማ ይውላል።
ሰ) ከዚህ በፊትም ጎጎታ ኬሪ በሚል የተሰበሰበው ገንዘብ ከምባታን እንጂ ማንም ያለመ የለም።
እንግዲህ ይህ አልበቃ ያለው የከምባታ ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ የመንግስት ሠራተኛውን ክስ ለማውለቅ ተዘጋጅቷል።
በመሆኑ አጠቃላይ የወረዳችን አመራሮችም ሆነ መንግስት ሠራተኞች ታሪካዊ ስህታት እንደትሰሩ ተጠንቀቁ።
የፖለቲካ ውምብድናን ፈጽመን እንቃወማለን!