wale vision

wale vision +251914398215

ኣትሌት ኣማን ጴጥሮስ ኣብ ውድድር ማራቶን 2ይ ደረጃ ብምውፃእ ውድድሩ ዛዚሙ።ናይ ሃገረ ጀርመን ዜግነት ዘለዎ ትግራዋይ ኣትሌት ኣማን ጴጥሮስ ናይ ቶክዮ ዓለም ሻምፒዮና ብማራቶን ካልኣይ ብም...
16/09/2025

ኣትሌት ኣማን ጴጥሮስ ኣብ ውድድር ማራቶን 2ይ ደረጃ ብምውፃእ ውድድሩ ዛዚሙ።

ናይ ሃገረ ጀርመን ዜግነት ዘለዎ ትግራዋይ ኣትሌት ኣማን ጴጥሮስ ናይ ቶክዮ ዓለም ሻምፒዮና ብማራቶን ካልኣይ ብምውፃእ ውድድሩ ዛዚሙ፡

ኣትሌት ኣማን ነቲ ርሕቐት 2 :09:48 ብምዝዛም ንሃገሩ ጀርመን ናይ ብሩር መዳልያ ተዓዋቲት ክትከውን ገይርዋ።

ኣትሌት ኣማን ጴጥሮስ ኣብ እዋን ወራር ፅንተት ንህዝቢ ትግራይ ኣብ ዝተፈላለዩ መድረኻት ዓለም ድምፂ ዝኾነ ኣትሌት እዩ።

ፀወታ 5ይ ሰሙን እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ
16/09/2025

ፀወታ 5ይ ሰሙን እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ

"አርሴማ" ማለት፦ በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፋችና የተሽለመች መልከ መልካም ውብ ማለት ነው።ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ቅድስት አርሴማ በዓለም ላይ...
16/09/2025

"አርሴማ" ማለት፦ በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፋችና የተሽለመች መልከ መልካም ውብ ማለት ነው።

ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡

ቅድስት አርሴማ በዓለም ላይ ተወልዳ ዓለሙን ንቃ ለሰማያዊው መንግሥት የተጋች ታላቅ ሰማዕት ናት።

እናታችን ቅድስት አርሴማ ደም ግባቷ ያማረ ግን የናቀችው ሐብትና የዚህ ዓለም ብልጭልጭነት ያላታለላት ናት።

በአንገቷ የሐብል ጌጥ ሳይሆን የሰይፍ ስለት ያለፈ የክርስቶስ ሙሽራ ነች።

ቅድስት አርሴማ በውበቷ ምክንያት አላዊያን ነገሥታት ልባቸው ቀለጠ፤ እናታችን ደግሞ ልቧ በክርስቶስ ፍቅር ቀልጦ ነበርና ከክርስቶስ ፍቅር የሚለያትን የናቀች ናት።

በመጨረሻም በመስከረም ፳፱ ቀን እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን ተቀበለች።

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ምልጃና በረከት ይደርብን🙏

ምኑ ጉድ ነውእናትና ልጅን ያገባው ወጣት !ነገሩ እንዲህ ነው እናት ሴት ልጇ ስለ ባሏ በተደጋጋሚ በነገረቻት መልካም ነገሮች ምክንያት ሴትዮዋ  በሰውዬውን የማግባት ፍላጎት ያድርባታል።  ልጅ...
16/09/2025

ምኑ ጉድ ነው
እናትና ልጅን ያገባው ወጣት !

ነገሩ እንዲህ ነው እናት ሴት ልጇ ስለ ባሏ በተደጋጋሚ በነገረቻት መልካም ነገሮች ምክንያት ሴትዮዋ በሰውዬውን የማግባት ፍላጎት ያድርባታል። ልጅም ይሄን አውቃ ባሏን ከእናቷ ጋር ሼር ለማድረግ ተስማምታ ባሏን ሼር አደረገቻት።

አሁን እናትና ልጅ ሁለት ልጆች ሊሰጡት በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ከሱም ቤተሰብ በመመስረታችን ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል። 🙂

የሚወለዱት ልጆች ዝምድና ምንና ምን ሊሆን ነው?🤦‍♂️

መስከረም 5/2018                                                 #የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን...
14/09/2025

መስከረም 5/2018


#የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን ወርሐዊ መታሠቢያ በዐል እንኳን አደረሰን

👉አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ #እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

👉በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን #ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ

👉አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው "ስብሐት #ለአብ ስብሐት #ለወልድ ስብሐት ከፅልመት ወደ ብርሐን ያመጣኸኝ ብለው አመስግነዋል

👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ፃድቁ አቡነ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

👉የፃድቁ አባታችን ረድኤት በረከታቸው አይለየን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉 መስከረም 5/2018 ዓ/ም💞💞💞🙏🙏🙏

የሩሲያ ድሮን የኔቶ አየር ክልልን ጥሶ በመግባቱ ሮማኒያ ተዋጊ ጄቶቿን ወደ አየር አወጣች  |  በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት፣ ሩሲያ በዩክሬን መሠረተ ልማቶች ላይ ...
14/09/2025

የሩሲያ ድሮን የኔቶ አየር ክልልን ጥሶ በመግባቱ ሮማኒያ ተዋጊ ጄቶቿን ወደ አየር አወጣች

| በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት፣ ሩሲያ በዩክሬን መሠረተ ልማቶች ላይ በምትሰነዝረው ድንገተኛ የድሮን ጥቃት ምክንያት፣ የሮማኒያ አየር ክልል ጥሰት እንደተፈጠረ የሮማኒያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም የኔቶ አባል የሆነችው ሮማኒያ ሁኔታውን ለመከታተል ተዋጊ ጄቶቿን ወደ አየር አውጥታለች።

የመከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ ሁለት F-16 ተዋጊ ጄቶች ወደ አየር ከተላኩ በኋላ፣ በሮማኒያ አየር ክልል ውስጥ የነበረ አንድ ድሮን መለየታቸውን እና ከራዳር እስኪጠፋ ድረስ መከታተላቸውን ገልጿል።

ድሮኑ ከቺሊያ ቬቼ መንደር አቅራቢያ ከራዳር ውጪ መሆኑን ነው መግለጫው የጠቆመው።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፣ የሩሲያ ድሮን ከሮማኒያ ግዛት እስከ 10 ኪሎ ሜትር ዘልቆ መግባቱን እና ለ50 ደቂቃ ያህል በኔቶ አየር ክልል ውስጥ እንደቆየ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ጠቅሰዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህንን ድርጊት ሩሲያ ጦርነቱን እያሰፋች እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል።

ይህ ክስተት ፖላንድ የሩሲያን ድሮኖች አየር ክልሏን ከጣሱ በኋላ የኔቶን ምስራቃዊ ድንበር ለመከላከል ዕቅድ መያዙን ካስታወቀች ከጥቂት ቀናት በኋላ መከሰቱ፣ በአካባቢው ያለውን ውጥረት የበለጠ አባብሶታል ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ በ1 ትሪሊዮን ብር የመንግስትና የግል አጋርነት ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ፣ በከተማዋ በመንግሥትና በግል አጋርነት (Publi...
14/09/2025

በአዲስ አበባ በ1 ትሪሊዮን ብር የመንግስትና የግል አጋርነት ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ፣ በከተማዋ በመንግሥትና በግል አጋርነት (Public-Private Partnership) ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት 60 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን፣ ሌሎችም በቅድመ ጥናት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከፕሮጀክቶቹ መካከል የገበያ ማዕከሎች (ሞሎች)፣ የወንዝ ዳር ልማት አካል የሆኑ ፕላዛዎች እና የመዝናኛ ስፍራዎች ተጠቃሽ መሆናቸው ተመላክቷል።

የዓለማችን የምንጊዜም ዉዱ መርከብ አደጋ 🙏😥በማርች 2022 ፌሊሲቲ ኤስ የተባለች መርከብ በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ አዞረስ በተባለ ስፍራ አቅራቢያ በእሳት ተያይዛ ሰጠመች። በዚህም በሺዎች...
14/09/2025

የዓለማችን የምንጊዜም ዉዱ መርከብ አደጋ 🙏😥

በማርች 2022 ፌሊሲቲ ኤስ የተባለች መርከብ በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ አዞረስ በተባለ ስፍራ አቅራቢያ በእሳት ተያይዛ ሰጠመች። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ የቅንጦት መኪናዎችን ወደ ውቅያኖስ ወለል ሰደደች።

ከጭነቶቿ መካከል በዓለም ላይ ተፈላጊ የሆኑ እንደ ፖርሽ፣ አውዲ፣ ቤንትሌይ እና ላምቦርጊኒ ያሉ ብራንዶች ይገኙበታል። ይህም በባህር የተዋጠ እጅግ በጣም ከፍተኛ ሀብት ነበር።
ይህ የመርከብ አደጋ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ እጅግ አስገራሚ ከሆኑ ዘመናዊ የመርከብ አደጋዎች አንዱ ሆኗል።

ከአስራ ሶስት አመት በፊት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የአባይ ወንዝን በመገደብ የሀይል ማመንጫ ፣ የመስኖ እርሻና ፣ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ሲያስቀምጡ የመዲናው ነዋሪ ከፍተኛ ...
14/09/2025

ከአስራ ሶስት አመት በፊት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የአባይ ወንዝን በመገደብ የሀይል ማመንጫ ፣ የመስኖ እርሻና ፣ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ሲያስቀምጡ የመዲናው ነዋሪ ከፍተኛ የድጋፍ ሰልፍ መስቀል አደባባይ በመትመም አደረገ።

ህይወታቸው ካለፈ በኃላም ..."አባይን የደፈረ መሪ" .. በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደማቅ አሸኛኘትና ቃላቸውን ለመፈፀም ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ቃልኪዳን ገባ።

ዛሬ ደግሞ የህዳሴው ግድብ ግንባታን ጠቅልሎ ለጠ/ሚ አብይ በመስጠት ሰልፍ እየተደረገ ነው። የተገባው ቃልኪዳን ፣ አባይን የደፈረ በሚል የተሰጠው ስያሜ በቅፅበት ተቀይሮና ለአብይ ሙሉ ክሬዲት ተሰጥቶ እየተመሰገነ ነው።

አዲስ መሪ በመጣ ቁጥር የተሰራውን ጥሩ ነገር ክሬዲት ጠቅልሎ በመውሰድ ... ሀጢያቱን ደግሞ ያለፈው ላይ በማላከክ እራስን የጥሩ ታሪክ አሻራ አድርጎ መቆለል የኢትዮጵያ መሪዎች መገለጫ ነው። ህዝቡ ደግሞ ለመጣው ሁሉ ፣ በጫና ፣ በፍርሃት ፣ ውስጥ ሆኖ ሰልፍ መውጣቱን #ይቀጥላል 🤔

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when wale vision posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category