Walia Media

Walia Media Follow for daily Daily information

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 215.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንና የደንበኞቹ ቁጥር 90 ሚሊዮን ማለፉን ገለጸ​ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 215.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግ...
23/07/2026

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 215.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንና የደንበኞቹ ቁጥር 90 ሚሊዮን ማለፉን ገለጸ

​ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 215.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

የተገኘው ገቢ የዕቅዱን 99.7 በመቶ ማሳካት የቻለ ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33.2 በመቶ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱ ተገልጿል።

​እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ፣ ተቋሙ የገቢ ምንጮቹን በማስፋትና የቴሌኮም አውታረ መረቡን በማሳደግ በርካታ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኗል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ የሞባይል ጣቢያዎችን ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ ማድረስ ተችሏል። በተጨማሪም የ4ጂ አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት 264 ከተሞችን ማቃለል የተቻለ ሲሆን፣ አዳዲስ 7 ከተሞችን በመጨመር በአጠቃላይ በ33 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል።

​በሌላ በኩል የተቋሙ ጠቅላላ የደንበኞች ቁጥር 90.1 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ይህም የዕቅዱን 101.7 በመቶ ማሳካት አስችሏል። ከነዚህም ውስጥ የድምፅ አገልግሎት ተጠቃሚዎች 86.9 ሚሊዮን፣ የብሮድባንድ ተጠቃሚዎች 51.5 ሚሊዮን እንዲሁም የፊክስድ ብሮድባንድ ተጠቃሚዎች 1 ሚሊዮን መድረሳቸውን መግለጫው አመላክቷል።

​ተቋሙ በዓመቱ 193 አዳዲስ አገልግሎቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 470 ምርቶችን ለደንበኞች ያቀረበ ሲሆን፣ ደንበኞች አገልግሎቶችን በተገቢው መንገድ መጠቀም እንዲችሉ የሚያግዝ የደንበኞች ትምህርት (Customer Education) ፕሮግራም እየተተገበረ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ታጥረው የተተዉ መሬቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ‼️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት የተቀመጡ መሬቶችን በማጣራት በሚቀጥሉት...
22/07/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ታጥረው የተተዉ መሬቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት የተቀመጡ መሬቶችን በማጣራት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ ይህን ያስታወቁት፣ በከተማ አስተዳደሩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድና የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው።

እንደ ከንቲባዋ ገለጻ፣ አዲስ አበባ መሬት ታጥሮ የሚቀመጥባት ከተማ መሆን እንደሌለባት ቀደም ሲል የተደረሰውን ስምምነት የሚጥሱ አካላት ተጨማሪ ዕድል እንደማይሰጣቸው አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል፣ በከተማዋ የሰላምና ደህንነት ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን በመግለጽ፣ በርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ያለ የደህንነት ችግር በሰላም መጠናቀቃቸውን አስታውሰዋል።

በተጨማሪም፣ የከተማዋ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት መዘመኑ ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጥናት መሠረት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአፍሪካ ከተመረጡ ስድስት ምርጥ ከተሞች መካከል በአሠራር ደረጃ አንደኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ በጤናው ዘርፍ የሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ሥነ-ምግባርና የአገልግሎት ጥራት መሻሻሉን፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የጤና አገልግሎትና የመሠረተ ልማት ሥራዎችም ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸሩ በእጥፍ መጨመራቸውን ገልጸዋል።

በኮንታ ልዩ ወረዳ እናትን ገድሎ ልጃቸውን የደፈረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ​በኮንታ ልዩ ወረዳ የግንባ አጋሬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አብርሃም አመለ ቦንጆሬ፣ በፈጸማቸው ሶስት ከ...
22/07/2026

በኮንታ ልዩ ወረዳ እናትን ገድሎ ልጃቸውን የደፈረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

​በኮንታ ልዩ ወረዳ የግንባ አጋሬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አብርሃም አመለ ቦንጆሬ፣ በፈጸማቸው ሶስት ከባድ ወንጀሎች በሞት እንዲቀጣ የኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።

​ተከሳሹ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከገበያ ስትመለስ የነበረችውን የ15 ዓመት ታዳጊ ጠልፎ ወደ ጫካ በመውሰድ ሊደፍራት ሲታገል፣ የልጇን ጩኸት ሰምታ የደረሰችውን እናት ወይዘሮ አይናቴ ኬቶን በጩቤ ወግቶ በመግደል ገደል ውስጥ ወርውሯታል።

​ተከሳሹ እናትን በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ካደባየ በኋላ የጠለፋትን ታዳጊ ልጅ አስገድዶ መድፈሩን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እና የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች አረጋግጠዋል።

​በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት፣ ተከሳሹ በፈጸማቸው በጭካኔ የመግደል፣ በታዳጊ ልጅ ጠለፋ እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ጥፋተኛ በማለቱ የሞት ቅጣት እንዲወሰንበት አድርጓል።

" ከሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች ነው የተያዙት " - አቶ ጃይላን አብዲ"እጅግ አደገኛ ናቸው" የተባሉ ሰው አዘዋዋሪዎች መያዛቸውን የኢትዮ...
22/07/2026

" ከሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች ነው የተያዙት " - አቶ ጃይላን አብዲ

"እጅግ አደገኛ ናቸው" የተባሉ ሰው አዘዋዋሪዎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከ60 በላይ ስደተኞች ለሞት እና በርካታ ሴቶች ለመደፈር ተጠያቂ ናቸው " ያላቸውን አደገኛ 17 ተጠርጣሪ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መያዙን አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ በ"መሐመድ ጣሂር አደም (ወርዲ)" የሚመራው ቡድን ሰዎችን ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት በመልመል በጂቡቲና በየመን በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያዘዋውር ነበር።

እነዚህ አደገኛ የሰው አዘዋዋሪዎች ከ40,000 በላይ ሰዎች እንዳዘዋወሩ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ እንደሰበሰቡ ተገልጿል።

ተጎጂዎች በየመን ውስጥ በመጋዘኖች ታግተው ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ሲገለጽ፣ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲልኩ ለማስገደድ የስቃይ ቪዲዮዎች ይላኩ እንደነበር ተጠቁሟል።

በምርመራውም ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውና በርካታ ሴቶች መደፈራቸው መረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ጄይላን አብዲ፣ ተጠርጣሪዎቹ ሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች መያዛቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።

ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹ የምርመራ ፋይል ለፍትሕ ሚኒስቴር መተላለፉን ገልጿል።

በስማቸው የነበሩ ቤቶች ፣ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶችም መታገዳቸው ታውቋል።

የ20 ዓመት ሴት ልጅ የገዛ ልጁን አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኘነት ያደረገው አባት በእስራት ተቀጣ     ሐምሌ 14, 2018 ዓ.ም ምዕራብ ዓባያ ወረዳ።   በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ...
21/07/2026

የ20 ዓመት ሴት ልጅ የገዛ ልጁን አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኘነት ያደረገው አባት በእስራት ተቀጣ

ሐምሌ 14, 2018 ዓ.ም ምዕራብ ዓባያ ወረዳ።

በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ መንደር ሰባት ነዋሪ የሆኑት ኢንስፐክተር ግርማ ጌታቸው እና ከወ/ሮ መስከረም ሙሉጌታ የተወለደችው ልጅ ሐና ግርማ ዕድሜዋ 20 ዓመት የደረሰና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን መንግሥት ባስታጠቀው ሽጉጥ በማስፈራራት በቀን 6/9/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ቡና እያፈለች ባለችበት ኳላ በመምጣት በጉልበት ወደ መኝታ ክፍል በማምራት የለበሰችሁን ቀምስ በማወለቅ ክብረ ንጽህና በመገርሰስ በጉልበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈፅም ልጅቷ ባሰማችው የድረሱልኝ ጥሪ ጎረቤት በመሰማት መደፈራዋን ከአንደበቷ ሰምተው ሲያረጋግጡ ለፖሊስ ጥቆማ በማድረግ የማጣራት ስራ በመስራት በህግ ሲታይ ቆይቶ የምዕራብ አባያ ወረዳ ፍ/ቤት በተከሳሹ ላይ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 9 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል ሲል ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።

12 ሰዎች በመኪና አደጋ አጣን 😢በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ በተከሰተ የመኪና አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።አደጋ የደረሰው በቀብሪበያህ ወረዳ...
20/07/2026

12 ሰዎች በመኪና አደጋ አጣን 😢
በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ በተከሰተ የመኪና አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

አደጋ የደረሰው በቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ የአይሱዚ መኪና ፎርስ ተብሎ ከሚጠራው ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ሲሆን በአደጋው የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 3 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተገልጿል።

የክልሉ የትራፊክ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ነው የተገለፀው ።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር ድርጅት መስራች አባል ሆነች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የድርጅቱን የምስረታ ስምምነት በኢትዮጵያ ስም በሻንጋይ...
20/07/2026

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር ድርጅት መስራች አባል ሆነች

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የድርጅቱን የምስረታ ስምምነት በኢትዮጵያ ስም በሻንጋይ መፈረማቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር ድርጅት ከሆኑት 29 መስራች አገራት አንዷ መሆንዋን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው፣ ስምምነቱ የተፈረመው ሐሙስ ዕለት የ2018ቱ የዓለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ከመጀመሩ አስቀድሞ በተካሄደ ይፋዊ ስነ-ስርዓት ላይ ሲሆን፣ ይህም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ትብብር የሚሰራውን አዲሱን ዓለም አቀፍ ድርጅት መመሥረቱን ያበሰረ ነው።

እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱን በሻንጋይ የሚያደርገው ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ትብብርን እና ዓለም አቀፋዊ አስተዳደርን ለማሳደግ የሚተጋ ራሱን የቻለ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሆኖ ይንቀሳቀሳል።

ድርጅቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር መርሆዎችን በተከተለ እና ሰብአዊ እሴትን ማዕከል ባደረገ መልኩ፣ የኤአይ ልማት ጠቃሚ፣ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ሁሉንም ያካተተ እና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ያለመ ነው።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ስምምነቱን በቻይና ስም የፈረሙ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በስነ-ስርዓቱ ላይ መገኘታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

"ኦሮሚያ ክልል 'ጠፍቶ' ለማየት የሚመኙ አሉ፤ ምኞታቸው ግን በፍጹም አይሳካም"  አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል "ጠፍቶ" ለማየት የሚመኙና "ኦሮሚያ" የሚለውን ቃል መስማት የማይፈልጉ ...
18/07/2026

"ኦሮሚያ ክልል 'ጠፍቶ' ለማየት የሚመኙ አሉ፤ ምኞታቸው ግን በፍጹም አይሳካም" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኦሮሚያ ክልል "ጠፍቶ" ለማየት የሚመኙና "ኦሮሚያ" የሚለውን ቃል መስማት የማይፈልጉ አካላት እንዳሉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በአዳማ ከተማ በተካሄደ የመንግሥት አመራሮች መድረክ ላይ ርዕሰ መሥተዳድሩ በኦሮምኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ ምኞት "በፍጹም" ሊሳካ እንደማይችልና ክልሉ ይበልጥ እየጠነከረና ውጤታማ እየሆነ እንደሚሄድ አረጋግጠዋል።

አቶ ሽመልስ የእነዚህን አካላት ማንነት በስም ባይጠቅሱም፣ ንግግሩን ያደረጉት የክልሎች አወቃቀር ጉዳይ ለአገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጀንዳነት በቀረበ ማግስት ነው።

በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ሴት መስሎ በመቅረብ ህብረተሰቡን ለመሸወድ እና የተለያየ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የከተማ ...
17/07/2026

በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ሴት መስሎ በመቅረብ ህብረተሰቡን ለመሸወድ እና የተለያየ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር በሜጦማ ቀበሌ ልዩ ስሙ መምህራን መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ታውቋል።

አቡሽ የተባለውና የትውልድ ስፍራው በምዕራብ ባደዋቾ ቆቶ ቀበሌ የሆነው ይህ ግለሰብ ወንድነቱን በመደበቅ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሴትነት በመለወጥ ህዝብን ሲያታልል እንደነበር ተገልጿል።

ግለሰቡ የወንጀል ዓላማውን ለማሳካት የሴት ቀሚስ ፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር (ዊግ) እና የሴት ጡት መያዣ በመጠቀም ራሱን በመለወጥ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ነበር።

የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር አድማሱ ሱሎሮ እንደገለጹት ግለሰቡ በተደረገበት የህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ጥልቀት ያለው ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

ቅዳሜ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ሊደረግ ነው‼በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እና እስራትን ለመቃወም፣ ለመጪው ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የ...
17/07/2026

ቅዳሜ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ሊደረግ ነው‼

በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እና እስራትን ለመቃወም፣ ለመጪው ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተጠራው ሰልፍ ከመንግሥት ፈቃድ ማግኘቱን አስተባባሪዎቹ አስታወቁ።

የትግራይ ሰላምና የለውጥ ምክር ቤት የጠራው ይህ ሰልፍ፤ በትግራይ ወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን አፈሳ ለማውገዝ፣ የታሰሩ እናቶችን ድምፅ ለማሰማት እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ ለመጠየቅ ያለመ ነው ተብሏል። በሰልፉ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Walia Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share