24/04/2026
ባለፈው የቅርብ ጓደኛውን አሰሩት፣ ከዛ በኋላ ደግሞ ምክትል ማናጀሩን አሰሯት። ከትናንት ወዲያ ደግሞ ከለሊቱ 6 ሰአት ላይ መኖርያ ቤቱ ድረስ በመሄድ - በቴዲ መኖርያ ቤት የሚገኘውንና ሌላኛው ጓደኛውን DJ ዊሽን ለመውሰድ ያለ መጥሪያ የቴዲ አፍሮ መኖርያ ቤት መጥተው "በለሊት ቤት አልከፍትላችሁም.." ስላሏቸው ተመልሰው ሄደው ነበር። አሁን ደግሞ CMC አካባቢ የሚገኘውንና አቡጊዳ የተሰኘውን የሙዚቃ ስቱዲዮውን ሰብረው በመግባት እቃዎቹን በሙሉ ጭነው ወስደዋል እየተባለ ነው። በ ቴዲ አፍሮ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ላይ የሚፈፀሙት ተከታታይ እስሮች እና አሁን ደግሞ በስቱዲዮው ላይ ደረሰ የተባለው ነገር በጣም የሚያሳስብ ነው። የልጆችህ አምላክ ይጠብቅህ..!