10/02/2026
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ሙስሊም አዋርድ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
አዳዲስ መልቲሚድያ ፕሮዳክሽን ከኮማንደር ሚድያና ኮሚኒኬሽን ጋር በመተባበር በኢስላማዊ እሴት ኢትዮጵያዊ መልክ በሚል መሪ ቃል የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሙስሊም አዋርድ (EMA Award) ዝግጅት ከጥቅምት 3 ቀን 2018 እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ሲያከናውን ቆይቷል። ዝግጅቱ ይፋ ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ በህዝብ ጥቆማ ዕጩ ሆነው ለቀረቡ ግለሰቦች ፣ ዝግጅቶችና ተቋማት በይፋዊ ድህረ ገፃችን አማካኝነት ድምፅ ሲሰጥ ቆይተዋል።
የህዝብ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላም በባለሙያ ዳኞች አማካኝነት ዝግጅቱ እንደሚይዘው የዳኞች ድምፅ መጠን መሰረት ፣ ድምፅ የተሰጠ ሲሆን የዚህ ዓመት ተሸላሚዎችን ጥር 30 ቀን 2018 ቦሌ ፍላሚንጎ በሚገኘው አዲሱ የወጣቶች አርት ኮምፕሌክስ ውስጥ ተጋባዥ እንግዶች፣ እጩዎችና የእጩ ቤተሰቦች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርዓት ተጠናቋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የ 2025 የኢማ አዋርድ ተሸላሚዎች ናቸው።
ሸይኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ (ረሂመሁሏህ) ለሀገርና ለዲን ላበረከቱት የማይተካ አስተዋፅኦ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነዋል።
1. የአመቱ ምርጥ ሙስሊም ወንድ ጋዜጠኛ - ዲኑ አሊ
2. የአመቱ ምርጥ ሙስሊም ሴት ጋዜጠኛ - ሶፊያ ጁሃር
3. የአመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፕሮግራም - ኸሚስ ምሽት
4. የአመቱ ምርጥ የፌስቡክ ተፅዕኖ ፈጣሪ (ወንድ )- ሙጂብ አሚኖ
5. የአመቱ ምርጥ የፌስቡክ ተፅዕኖ ፈጣሪ (ሴት ) - አቲካ አህመድ አሊ
6. የአመቱ ምርጥ የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ (ወንድ) -ሀምዛ ሺፋ
7. የአመቱ ምርጥ የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ (ሴት) - ጠበቃ አዲስ መሃመድ
8 በቲክቶክ ኢስላማዊ መረጃ አቅራቢ - አሚር
9 በቲክቶክ ኢስላማዊ ትምህርት አቅራቢ - ሀምዛ ሺፋ
10. የአመቱ ምርጥ ሙስሊም ዩቱበር - መስኮት ቲዩብ
11. የአመቱ ምርጥ የድርሰት ስራ - "ኢፋዳ" በፉአድ ሙና
12. የአመቱ ምርጥ ፎቶግራፈር - አህመድ ነጋ
13. የአመቱ ምርጥ የነሺዳ ሥራ - ኑር አምባ-ዋሪዳ
14. የሐላል ቱሪዝም (የሀገር ውስጥ ጉዞ) - ሙስሊም ውሜንስ ግሩፕ
15. የሐላል ቱሪዝም የዑምራ አገልግሎት አቅራቢ - ዙበይር ትራቭል በመሆን የዚህ ዓመት ተሸላሚ ሆነዋል።
በቲክቶክ ኢስላማዊ መረጃ አቅራቢ የሆነው አሚር የዑምራ አሸናፊ የሆነ ሲሆን ሽልማቱንም አያ ቱር ኤንድ ትራቭል አቅርቧል።
አዳዲስ መልቲ ሚድያ ፕሮዳክሽን ይህ ዝግጅት እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ፣ የሚድያ ተቋማት፣ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ፣ በየዘርፉ እጩ ሆነው የቀረቡ ግለሰቦች፣ ኡስታዞች ፣ መሻኢኾችን ሁሉ ያመሰግናል።
በቀጣይም በዝግጅቱ ሂደት የነበሩ በጎ ጎኖችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላት ዝግጅቱን ወደ ላቀ ከፍታ ለማድረስና ህዝባቸውንና ሀገራቸውን ከፍ ለማድረግ እየሰሩ የሚገኙ ባለሙያዎች በላቀ ሁኔታ ለማመስገን ለተሻለ ዝግጅት እንደሚተጋ ለመግለፅ ይወዳል።
በመጨረሻም ይህ ዝግጅት ዓመታዊ መርሃግብሩን ጠብቆ ለማከናወን ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅቶች መጀመራቸውን እየገለፅን የመጀመርያው ዓመት ዝግጅት የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደረጉና ከጎን የነበሩትን በሙሉ በድጋሚ ለማመስገን ይወዳል።
አዳዲስ መልቲሚድያ ፕሮዳክሽን
በኢስላማዊ እሴት ኢትዮጵያዊ መልክ
የካቲት 03/2018
አዲስ አበባ