AGEW TV

AGEW TV Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from AGEW TV, TV Channel, Addis Abeba, Addis Ababa.

የዜና እና የወቅታዊ መረጃ ገጽ ነው።
አዳዲስ መረጃ ለማግኘት Like Page የሚለውን
በመጫን Follow ያድርጉ!
መረጃ ሲኖራችሁ፣ የሚዲያ ሽፋን ስትፈልጉ በውስጥ መስመር inbox ያድርጉልን ወይም በቴሌግራም
ገጻችን በኩል ላኩልን።
👉Voice of Voiceless ✅

🌐 https://linktr.ee/agewtv

🎉 Facebook recognized me as a consistent post creator this week!
23/07/2026

🎉 Facebook recognized me as a consistent post creator this week!

እግዚአብሔር ይመስገን አንድም ሰው ሳይጓዳ በታምር ተርፈዋል🙏በቀን 16/11/2018 ዓ/ም ከአዲስ አበበ ወደ ቁልቢ ገብረኤል የሚሄድ ልዩ  ባስ ሂርና አካባቢ አደገኛ ቁልቁለት ላይ ሲደርስ 8...
23/07/2026

እግዚአብሔር ይመስገን አንድም ሰው ሳይጓዳ በታምር ተርፈዋል🙏

በቀን 16/11/2018 ዓ/ም ከአዲስ አበበ ወደ ቁልቢ ገብረኤል የሚሄድ ልዩ ባስ ሂርና አካባቢ አደገኛ ቁልቁለት ላይ ሲደርስ 8 ሰዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ የመገልበት አደጋ ሲደርስ ተጓጆች ላይ ምንም አይነት አደጋ ሰይደር በታምር ተርፈዋል ተብሏል።
AGEW TV

ከ60% በታች ያገኘ ፕሬዝዳንት ከስልጣኑ ይነሳል! የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎችን ሊያናውጥ የሚችል አዲስ መመሪያ ይፋ አደረገ።"በትምህርት ሚኒስቴር የወጣው አዲሱ የመንግስት ከፍተኛ ትም...
22/07/2026

ከ60% በታች ያገኘ ፕሬዝዳንት ከስልጣኑ ይነሳል!
የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎችን ሊያናውጥ የሚችል አዲስ መመሪያ ይፋ አደረገ።"

በትምህርት ሚኒስቴር የወጣው አዲሱ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመሪያ (ቁጥር 1146/2018) ዋና ዋና ነጥቦች በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፦

​1. የቅጥር ሒደትና የነጥብ ድልድል (30/30/40)

​የእጩዎች ምልመላ በሁለት ገለልተኛ ኮሚቴዎች የሚመራ ሲሆን፣ የምርጫ ነጥቡ እንደሚከተለው ይደለደላል፦

​30%፦ የትምህርት ዝግጅትና አካዳሚክ ማዕረግ (ከፍ ባለ ቁጥር ነጥቡ ይጨምራል)።

​30%፦ ተቋም በመገንባትና በአመራርነት የተሳለፈ የስራ ልምድ።

​40%፦ ስልታዊ (ስትራቴጂያዊ) ዕቅድና አቀራረብ።

​2. መሰረታዊ መስፈርቶች

​ዜግነትና ስነ-ምግባር፦ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ የጡረታ ዕድሜው ያልደረሰ፣ እንዲሁም በሙስና፣ በእምነት ማጉደልና በከባድ ዲሲፕሊን/ፍትሐብሔር ክስ ስሙ ያልጠፋ።

​የአካዳሚክ ማዕረግ፦ ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ወንድ እጩዎች ቢያንስ ረዳት ፕሮፌሰር መሆን አለባቸው።

​የስራ ልምድ፦ ቢያንስ 2 ዓመት በፕሬዝዳንትነት ወይም 3 ዓመት በምክትል ፕሬዝዳንትነት/ዲንነት ያገለገለ።

​የሴቶች ማበረታቻ፦ በቂ የሴት እጩ በሌለበት ወቅት፣ የአካዳሚክ ማዕረግ ሳይጠበቅባቸው በሁለተኛ ዲግሪ (MA/MSc) መወዳደር ይችላሉ።

​3. የስራ ዘመንና የአገልግሎት ገደብ

​የስራ ዘመን፦ የፕሬዝዳንት የአንድ ጊዜ የስራ ዘመን 6 ዓመት፣ የምክትል ፕሬዝዳንት ደግሞ 4 ዓመት ነው።

​የዕድሜ ገደብ፦ በማንኛውም ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ ሁለት ጊዜ በፕሬዝዳንትነት ያገለገለ ድጋሚ መወዳደር አይችልም (ምክትል ፕሬዝዳንት ግን ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር ይችላል)።

​ሁለተኛ ዙር፦ አንድ ፕሬዝዳንት ያለ ውድድር ለ2ኛ ዙር የሚቀጥለው የተቋሙ አፈጻጸም ከፍተኛ ሆኖ በሚኒስቴሩ ሲጸድቅ ብቻ ነው።

​4. ግምገማና ከኃላፊነት መነሳት

​አመራሩ በየ3 ወሩ በቦርድ ይገመገማል።

​በሁለት ተከታታይ የስድስት ወር ግምገማዎች ውጤቱ ከ60% በታች ከሆነ፣ በጤና እክል፣ ወይም በከባድ ዲሲፕሊንና ሙስና ጥፋተኛ ከሆነ ከኃላፊነቱ ይነሳል።

​5. የቅሬታ አቀራረብ

​በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተወዳዳሪ ውጤቱ በወጣ በ10 ቀናት ውስጥ ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ቅሬታ ማቅረብ ይችላል፤ በውሳኔው ካልተስማማ ደግሞ ለትምህርት ሚኒስቴር ይግባኝ ማለት ይችላል።
AGEW TV

21/07/2026

እና ዲባዋ ዋታይ ካንቲን😂😳

19/07/2026

ለአገው ህዝብ መታገል ማለት በአገው ስም ተደራጅቶ መደበቅ ሳይሆን አገውነትን አንግቦ ስለአገው ህዝብ መብትና ክብር ግንባርን ሰጥቶ መታገል መቻል ነው።
© AGEW TV

ሳይንስ ሙዝዬም(አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ)
18/07/2026

ሳይንስ ሙዝዬም(አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ)

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

18/07/2026

የባህል አምባሳደራችን❤

በአገው ህዝብ ባህል ቋንቋና ታሪክ ለ4 እና 5 ተከታታይ አመታት በፅዓት እየተሻገረች የምትገኝ የአገው ህዝብ ብርቅዬ ወጣት!!
AGEW TV

ይህ ታሪካዊ ቦታ የት ነው? ስሙስ ማን ይባላል?AGEW TV
17/07/2026

ይህ ታሪካዊ ቦታ የት ነው? ስሙስ ማን ይባላል?
AGEW TV

 💪ኦሮሞነቴን እየካድክ ሲዳማነቴን እያንጓጓጠህ ቅማንትነቴን እየጨፈለቅህ አገውነቴን እየጠላህ ትግራዋይነቴን እና ሌሎች ያልገለጽኳቸውን ማንነቶቼንም እያወገዝክ "መጀመሪያ ሰው ነኝ" ብትል አል...
17/07/2026

💪

ኦሮሞነቴን እየካድክ ሲዳማነቴን እያንጓጓጠህ ቅማንትነቴን እየጨፈለቅህ አገውነቴን እየጠላህ ትግራዋይነቴን እና ሌሎች ያልገለጽኳቸውን ማንነቶቼንም እያወገዝክ "መጀመሪያ ሰው ነኝ" ብትል አልሰማህም። ምክንያቱም ሰው የሆነው አምላክም "የናዝሬቱ ኢየሱስ" (ሐዋ 3:6) ተብሎአልና። ስለዚህ ኦሮሞ ነኝ። ሲዳማ ነኝ። ቅማንት ነኝ። አገው ነኝ። ትግራዋይ ነኝ። ሌሎች የተለዩ እና የተገፉ ማንነቶችም ሆኑ የተከበሩቱ የእኔ ናቸው።

በዚህ ምክንያት ዘረኛ ብትለኝ ሰው የሆነው ክርስቶስ የአብርሃም ዘር፣ የዳዊት ዘር (ማቴ1:1) ተብሎአልና አይጨንቀኝም። ቅማንት ወይ አገው ወይ ሲዳማ ወይ ኦሮሞ ወይ ሌላ መባሌም ለቤተክርስቲያን አይጨንቃትም። ክርስቶስ ለሁሉም በሁሉም መሆኑን የተረዳነው ከናዝሬት ዘሩን በቆጠረ አምላክ ነውና።

ልሙጥነትን ብቻ እያሞካሹ ብዝሃነትን ግን እየካዱ ሰው ነኝ ማለት እርስ በርሱ ይጋጫል። ስብዕና ነጻ ፈቃድ (free will) አንዱ ጠባዩ ነው ካልን ብዝሃነት (diversity) እንዲያውም የስብዕና ማሳያ ነው። ምክንያቱም የነጻ ፈቃድ ውጤት ከልሙጥነት ወደ ብዝሃነት ሊያንደረድረን ይችላልና። ስብዕና አንዱ ጠባዩ ማኅበራዊነት ነው ካልን የሰው ልጅ በቋንቋ በባሕል በጋራ ትርክት እና ትዝታ ወይም ደግሞ በሃይማኖት ወይም ደግሞ በሌሎች መስፈርቶች ማኅበራዊነቱን የማሳየቱ ችግር ምኑ ላይ ነው?

ከእነዚህ ተለይቶ ለብቻ ያለ ቡድን የቆመ ሰውነት ትክክለኛው የስብዕና ማሳያ አይደለም። ምናልባት ምዕራባውያን መትረው ከሰጡን የሰው መስፈርት ጋር ሊጣጣም ይችላል። እርሱም ፍጹም የሆነ ግላዊነት (individualism) ነው። ግላዊነት ደግሞ ማኅበራዊነትን ከሚሰብክ ከክርስትናም ሆነ ከላይ ከገለጽኩት ስብዕና ጋር ፈጽሞ አይጠጣጣምም። ሃሳባዊ (ideal) ነው እንጂ ግዘፍ ነስቶ የቆመ እውነታ (reality) አይደለም።

ሥሉስ ቅዱስ እንኳን ይህ ማኅበራዊነት ስለሚገልጻቸው ነው "ሰውን በመልካችንና በምሳሌያችን እንፍጠር ያሉት።(ዘፍ 1:26) እኛም በእነሱ አርአያ እና አምሳል ስንፈጠር ከእኔነት ይልቅ ወደ ኬኛነት እንድናተኩር ተደርገን መፈጠራችንን ያጠይቃል። ይህ ማለት ግላዊ ማንነት የለንም ማለት አይደለም። ግላዊ ማንነትም ከነጻ ፈቃድ ማኅበረሰቡን መነሻ በማድረግ የሚፈጠር እንጂ መሠረት እና መነሻ የሌለው አይደለም። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ እርሱ እና እንደ አባቱ አንድ እንድንሆን የጸለየው ጸሎት (ዮሃ 17:22 እና 23) ከማህበራዊነት የተነጠለ ግለሰባዊነትን በማህበራችን ውስጥ እንደማይፈቅድ ማሳያ ነው።

ስለዚህ ከቡድናዊ እና ማኅበራዊ ማንነት ጋር የሚጣላ ስብዕና የለም። እንዲያውም የአምላክ ሰው መሆን ማሳያ ከእነዚህ ቡድኖቹ በአንዱ የይሁዳ ነገድ መጠራት ከሆነ በየትኛውም ብሔር ቋንቋና ባሕል መገለጽ ከስብዕና የወጣ አይደለም። የስብዕና ነጸብራቅ እንጂ።

ነገር ግን ክርስቶስ የሰውን ዘር በመዋሃዱ ምክንያት ከዚህ ከሚጠፋው ዘር በስጋ ተወልደን በመንፈስ የማይጠፋው ዘር አካል ሆነናል። ስለዚህ የክርስቶስ ዘር ነን ለማለት በመጀመሪያ እርሱ የተዋሃደው ዘር የስብዕና አንዱ አካል መሆኑን ማመን ይገባል።
AGEW TV

15/07/2026

አገውነት ብቻም ሳይሆን ውበት፣ባህል፣ታሪክ፣ቁልጭ ብሎ ይታያል❤💪

AGEW TV

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AGEW TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category