25/03/2026
የኤርትራ ወታደራዊ ልዑካን መቐለ መግባታቸው ተነገረ‼
የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በየካቲት ወር መጨረሻ ቀናት መቐለ መግባታቸውን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገበ።
በብሪጋዴር ጄኔራል እዮብ ፋሰሃዬ የተመራው ይህ ልዑክ፣ ከመቐለ መግባቱም ባለፈ ከትግራይ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ (ማንጁስ) ጋር መወያየቱ ተመልክቷል።
ይህ ስብሰባ መካሄዱ የተነገረው፣ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የፌዴራል መንግሥቱን የኮሪደር ልማት የሚተች መግለጫ ባወጣበት ወቅት መሆኑ ዘገባውን አነጋጋሪ አድርጎታል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከኤርትራ መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል።
Mereja = Wasu Mohammed