ኢትዮ አዲስ ቲዩብ የአዕምሮ መረጃ ማዕከል

  • Home
  • ኢትዮ አዲስ ቲዩብ የአዕምሮ መረጃ ማዕከል

ኢትዮ አዲስ ቲዩብ  የአዕምሮ መረጃ ማዕከል Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኢትዮ አዲስ ቲዩብ የአዕምሮ መረጃ ማዕከል, News & Media Website, .

18/06/2025

በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለው ውጥረት እንደገና ባየለበት ሁኔታ፣ ኢራን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለስምንተኛ ጊዜ የሚሳኤል ጥቃት በእስራኤል ላይ መፈጸሟ ተዘገበ። በሌላ በኩል በቴህራን እና ካራጅ የፍንዳታ ድምፆች አሁን ላይ መሰማታቸውን ዘግበዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ የሿሿ የተባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡*...
17/06/2025

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ የሿሿ የተባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል ለመከላከልና አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥናት ላይ በመመስረት እና ማስረጃ በማሰባሰብ ባደረገው እንቀስቃሴ ከዚህ ቀደም በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በቂርቆስ፣ በቦሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በልዩ ልዩ ስፍራዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ አስራ አንድ አባላት ያሉት ሁለት ቡድኖችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀል ለመፈጸም ይገለገሉባቸው የነበሩ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 53234፣ ኮድ 3 ኦ/ሮ 50777 እና ኮድ 2 አ/አ B 50438 ተሽከርካሪዎችን መያዙንና ከዚህ ቀደም በፈፀሙት የሿሿ ወንጀል አስፈላጊው ማስረጃ ተሰብስቦ አራት የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ፖሊስ መምሪያው ገልጿል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በግለሰቦቹ ላይ ምርመራውን አጠናክሮ እንደቀጠለና አስፈላጊውን ማስረጃ እያሰባሰበ በመሆኑ ከዚህ ቀደም በእነዚህ ተሽከርካሪዎች የሿሿ ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በግንባር በመቅረብ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በመለየትና በመምረጥ ማስረጃ መስጠት የሚችል መሆኑን ጥሪውን አስተላልፏል።
*
አዲስ አበባ ፖሊስ

ኢራን የሞሳድን ህንፃ በሚሳኤል ደበደብኩ አለች +++++++++++++++++++++  | ኢራን ዛሬ ጠዋት በሄርዝሊያ የሚገኘውን የሞሳድን ህንፃ በሚሳኤል ደበደብኩ ስትል አስታውቃለች።ከቴል አቪ...
17/06/2025

ኢራን የሞሳድን ህንፃ በሚሳኤል ደበደብኩ አለች
+++++++++++++++++++++

| ኢራን ዛሬ ጠዋት በሄርዝሊያ የሚገኘውን የሞሳድን ህንፃ በሚሳኤል ደበደብኩ ስትል አስታውቃለች።

ከቴል አቪቭ በስተሰሜን የሚገኘውን የወታደራዊ መረጃ እና የሞሳድ ህንፃ በሚሳኤል መምታቱን የኢራን ሚሊተሪ ዘግቧል።

ዛሬ ማለዳ ላይ ትክክለኛ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን የሩሲያው ስፑትኒክ የዜና አገልግሎት እና አልማያዲን ቲቪን ጨምሮ ሌሎች የሚዲያ ምንጮች ዘግበዋል።

ጥቃቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ መባባስ እየጨመረ መምጣቱን ይጠቁማል ተብሎለታል።

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ሚሳኤሉ በቀጥታ ህንፃውን ዒላማ ያደረገ ነው።
በእስራኤል በኩል እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ የቁሳቁስ እና የሰው ሞት የለም።

የኢራን ምድር ኃይል አዛዥ ተስኒም ኒውስ ለተባለው የኢራን መንግስት ሚዲያ እንደተናገሩት፤ የእስራኤል ስትራቴጂክ ቦታዎች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች የተራቀቁ ጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በመጪዎቹ ሰዓታት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ሄርዝሊያ የእስራኤል የስለላ ስራዎች ዋና ማዕከል ሲሆን፤ ማዕከሉ ላይ የተወሰደው ርምጃ ሁለቱን ሀገራት ወደ ከፋ ግጭት እንዳያስገባቸው ተፈርቷል።

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
#እስራኤል #ኢራን #ሞሳድ

ኢትዮጵያ ዳግም ተወከለች መልካም እድል!Miss Super Model World Wide 2025  በVIP አሸኛኘት ተደረገላትበሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ያሸናፊዎች አሸናፊ ዲሲምበር 1 2025 እ.ኢ....
17/06/2025

ኢትዮጵያ ዳግም ተወከለች መልካም እድል!

Miss Super Model World Wide 2025 በVIP አሸኛኘት ተደረገላት

በሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ያሸናፊዎች አሸናፊ ዲሲምበር 1 2025 እ.ኢ.አ በቦናንዛ ሆቴል በተደረገው የቁንጅና ውድድር ላይ አንደኛ የወጣችው ሀሴት ደረጀ ስትሆን በዚህ ውድድር ላይ ሁለተኛ የወጣችው ሩታ ይርጋለም ዘንድሮ በፊሊፒንስ ማኔላ ከተማ (Miss Super Model World Wide) 2025 Pageant ኢትዮጵያን በመወከል የምትሳተፍ ይሆናል፡፡

ዘንድሮ በፊሊፕንስ ማኒላ ከተማ የሚዘጋጀው አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር በርካታ ሀገሮች የሚሳተፉበት ትልቅ የቁንጅና ውድድር ሲሆን ይህ ውድድር የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማስተዋወቅ መንግስት እየሰራ የሚገኛውን ስራ ከማስተዋወቅም አንፃር የኢትጵያን መልካም ገፅታ ለውጩ አለም ለማስተዋወቅ የሚረዳ ትልቅ አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ነው ፡፡

ዛሬ በእለተ 09/10/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በቤተሰቦቿና በስራ ባልደረቦቿ በተገኙበት በቪአይፒ በኩል ያሸኛኝት ስነ- ስርአት ተከናውኗል ይህን ውድድር ለመሳተፍ አዘጋጆቹና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነ-ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ የኣንበሳውን ድርሻ ተወቷል፡፡

መልካም እድል ለኢትዮጵያ !!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል ቴሌአቪቭ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ተናገረ።አየር መንገዱ"በእስራኤል በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቴልአቪቭ የምናደርገውን በረራ በጊዜያዊ...
16/06/2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል ቴሌአቪቭ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ተናገረ።

አየር መንገዱ"በእስራኤል በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቴልአቪቭ የምናደርገውን በረራ በጊዜያዊነት የተቋረጠ መሆኑንን እንገልፃለን"ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።

በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላት ሁሉ ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ አሳውቃለሁ ብሏል።

እስራኤል ከኢራን ጋር ወደተባባሰ ጦርነት እየገባች መሆኑ ይታወቃል።
ሸገር ሬዲዮ

15/06/2025

በእሳት ሲነድ ያደረው መካከለኛው ምስራቅ
+++++++++++

| መካከለኛው ምስራቅ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ለሶስት ቀናት የፈጀ አደገኛ ወታደራዊ ግጭት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተከስቷል።

ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል በአስርተ ዓመታት ውስጥ ከታዩት ደም አፋሳሽ እና አውዳሚ ቀጥተኛ ግጭቶች አንዱ ነው።

ለሶስተኛ ተከታታይ ቀናት እስራኤል እና ኢራን የሚሳኤል፣ የጄት እና ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተለዋውጠዋል።

በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው አለማቀፋዊ ስጋት ወደ ውይይት ይመለሱ የሚል ብዙ ሽምግልናዎች ቢቀርቡም ሊደማመጡ አልቻሉም።

ዛሬ ሌሊትም ኢራን 3 የኢስራኤልን F-35 ጄቶችን መትቼ ጥያለሁ ብላለች።

በእየረሳሌም በበርሆቮት እና ባት ያም የሚገኘውን ዌይዝማን የሳይንስ ተቋምን ጨምሮ በቴል አቪቭ በሰሜናዊ እስራኤል ሀይፋ ወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ፣ ማከማቻዎች እና በርካታ አካባቢዎች ላይ ጥቃት ፈጽመናል ሲል የኢራን ጦር በመግለጫው ታናግሯል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥበቃዎች በዛሬው እለት ባደረጉት ጥቃት “ሀጅ ቃሰም”" የሚባለውን ታክቲካል መር ባሊስቲክ ሚሳኤል እና "ኸይበ" የተሰኘውን ሀይፐርሶኒክ ሚሳይል መጠቀማቸውን ገልጸዋል።

የእስራኤል ፖሊስ ከቴላቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ባት ያም የመብራት መቆራረጥ እና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።

ከ40 የሚበልጡ እስራኤላውያን የኢራን ሚሳኤል በተመታበት ባት ያም ቦታ ላይ አድራሻቸው አልታወቀም ሲል ዬዲዮት አህሮኖት ተናግሯል።

የእስራኤል የአምቡላንስ አገልግሎት በበኩሉ በኢራን በሚሳኤል ጥቃት አራት ሰዎች ሲገደሉ 200 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

እንደ ማጌን ዴቪድ አዶም ቃል አቀባይ በሚሳኤል ጥቃት 100 ሰዎች ቆስለዋል። በሻፊላህ አካባቢም 37 ሰዎች ቆስለዋል ሲል ተናግሯል።

ነገሩ እየተባባሰ የመጣው የእስራኤል ጦር በኢራን የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት፣ ከ"ኑክሌር ጦር መሳሪያ ፕሮጀክት" መሰረተ ልማት ጋር የተያያዙ ቦታዎችን እና ሌሎች ኢላማዎችን ማድረጋቸውን ካስታወቀ በኋላ ነው።

ጦሩ ባወጣው መግለጫ አየር ኃይሉ በቴህራን ውስጥ ከኢራን አገዛዝ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፕሮጀክት ጋር በተያያዙ በርካታ ኢላማዎች ላይ ባደረሱት ሰፊ ተከታታይ ጥቃት የነዳጅ መጋዘኖችንም ኢላማ አድርጓል ብሏል።

ኢላማዎቹ የኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት፣ የመከላከያ ፈጠራ እና ምርምር ለኒውክሌር ፕሮጀክት ዋና መሥሪያ ቤት እና ተጨማሪ ኢላማዎችን ያካተቱ ናቸው ሲል አክሏል።

በአረቡ ሙሀመድ
+++++++++++++++

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ

#እስራኤል #ኢራን #ኢትዮጵያ

14/06/2025

ኢራን የእስራኤል የኑክሌር ጣቢያ ላይ ጥቃት አደረሰች።

የመልሶ ማጥቃት እርምጃ እየወሰደች የምትገኘው ቴህራን ዛሬ ማለዳ በፈፀመችው ጥቃት ቴላቪቭ አቅራቢያ የሚገኘውን የኑክሌር ጣቢያ ኢላማ አድርጋለች ተብሏል።

14/06/2025

ኢራን ለትናንትናው የእስራኤል የአየር ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ የሚሳኤል ጥቃት እያደረገች መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።

የኢራን ጥቃት ኢላማ ያደረገው ቴል አቪቭ፣ ሃይፋ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና ስትራቴጂካዊ ተቋማትን ነው።

በአብዛኞቹ ከተሞች ሳይረን ድምፅ መጮሁ ተሰምቷል።

የኢራን አብዮታዊ ጠባቂ "በቀሉ ተጀምሯል እንቀጥላለንም" ማለቱን የኢራን ሚድያዎች ዘግበዋል።

13/06/2025

ሰበር ዜና
እስራኤል በኢራን 'የኒውክሌር መርሃ ግብር' ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች፤ ፍንዳታዎችም በመላ አገሪቱ ተሰምተዋል።

በህንድ የተከሰከሰው  አውሮፕላን - አዳዲስ መረጃዎች!• አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል -- በመስኮት ዘሎ ነው የተረፈው• የሟቾች ቁጥር 290 መድረሱ ተዘግቧል*በህንድ የአህመደዳብ ከተማ ፖሊ...
12/06/2025

በህንድ የተከሰከሰው አውሮፕላን - አዳዲስ መረጃዎች!

• አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል -- በመስኮት ዘሎ ነው የተረፈው

• የሟቾች ቁጥር 290 መድረሱ ተዘግቧል

*በህንድ የአህመደዳብ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነር ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ፣ ከተከሰከሰው አውሮፕላን አንድም ሰው በህይወት የተረፈ እንደሌለ ቢናገሩም፣ አሁን ላይ ግን አንድ ሰው በህይወት መገኘቱን ለህንድ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል፡፡

*ከተረፉት ግለሰቦች አንዱ እንግሊዛዊ ሲሆን፤ ከአውሮፕላኑ ውስጥ በመስኮትበመዝለል በ"ተዓምር" ከሞት መትረፉ ተዘግቧል፡፡

"አውሮፕላኑ ከመሬት ከተነሳ 30 ሰከንዶች በኋላ ከባድ ድምጽ ተሰማ፤ ከዚያ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፤ ሁሉም ነገር በከፍተኛ ፍጥነት ነው የሆነው" - በህይወት የተረፈው እንግሊዛዊ

*በአውሮፕላኑ 169 ህንዳውያን፣53 እንግሊዛውያን፣ እንዲሁም 7 የፖርቱጋልና 1 የካናዳ ዜግነት ያላቸው ተሳፋሪዎች ነበሩ - የሕንድ አየር መንገድ

*የሟቾች ቁጥር 290 መድረሱ የተዘገበ ሲሆን፤ እስካሁን 204 አስከሬኖች መገኘታቸውን የፖሊስ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል - ነገር ግን አውሮፕላኑ ሲከሰከስ ምን ያህሎቹ መሬት ላይ ወይም በአውሮፕላኑ ውስጥ እንደነበሩ አይታወቅም ብለዋል፡፡

*አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሃኪሞች ማረፊያ ቤት ላይ ነው - አንዲት እናት ወንድ ልጇ እንዴት ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ዘሎ ህይወቱን እንዳተረፈ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጻለች፡፡

*የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በህንድ በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ ልባቸው መሰበሩን ገልጸው፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

የቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ያለመከሰስ መብት ተነሳየሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር ምርጫ 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የምክር...
12/06/2025

የቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር ምርጫ 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤት አባሉን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

ግለሰቡ በስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም፣ በሙስና፣ በቀጥታ በኮንትሮባንድ ዝውውር ውስጥ መሳተፍ፣ ለኮንትሮባንድ አዟዟሪዎች በጥቅም ትሰስር ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና አደንዛዥ ዕጽ በማዘዋወር እንቅስቃሴ ውሰጥ መገኘቱን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ለምክር ቤቱ በዝርዝር አቅርቧል።

የምክር ቤት አባላት በግለሰቡ ዙሪያ የቀረበውን ዝርዝር መረጃ ካደመጡ በኋላ፤ ሌሎች ከግለሰቡ ጋር በጥቅም ትስስር የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው አካላት ላይ በጥልቀት ፍተሻ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።

ግለሰቡ ስልጣኑን መከታ በማድረግ የፈፀማቸው ነገር ግን በወንጀል ሪፖርቱ ውስጥ ያልተካተቱ በርካታ ኢ-ፍትሀዊ ድርጊቶች መኖራቸውን በምክር ቤት አባላቱ ተነሰቷል።

ምክር ቤቱ የግለሰቡ ያለመከሰስ መብትን ለማንሳት የቀረበለትን አጀንዳ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ምክር ቤቱ በሌላ በኩል የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ስያሜ "አፊኒ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን" እንዲሆን የቀረበለትን አዋጅ መርምሮ ውድቅ በማድረግ የሚዲያ ተቋሙ ቀድሞ ይጠራበት በነበረው ስያሜ "የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን" ሆኖ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳልፏል።

Via: EBC

12/06/2025

242 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ

242 ሰዎችን ከአሕመዳባድ አሳፍሮ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ አዲስ ቲዩብ የአዕምሮ መረጃ ማዕከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share