
02/08/2025
“ ዓለም ሲኒማ በመገናኛ “ በድምቀት ተመርቆ ተከፈተ፡፡
ለ22 ዓመታት ለሲኒማ ኢንዱስትሪው ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከተው ዓለም ሲኒማ አሁን ደግሞ ለመገናኛ እና
አካባቢው የፊልም ተመልካች በማራቶን የገበያ ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ሁለት ሲኒማ ቤቶች ከፍቷል፡፡
ዛሬ በተደረገው የምርቃት ስነስርዓት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሒሩት ካሳ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተመርቆ ተከፍቷል::
ዓለም ሲኒማ በመገናኛ ሁለት ደረጃውን የጠበቁ ሲኒማ ቤቶችን በ120 ሚሊየን ብር ወጪ የገነባ ሲሆን በአጠቃላይ ከ550 በላይ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ሲኖረው ከፍተኛ የምስል ጥራት እና ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም
የተገጠመለት እጅግ ምቹና ውብ ሲኒማ ቤት ሲሆን በሁለቱም ሲኒማ ቤቶች ከሐምሌ 26 ቀን ጀምሮ በ7:00 ፣ 8:00፣ 9:00 ፣ 10:00 ፣11:00 ፣ 12:00 ፣ 1:00 እና ምሽት 2:00 ሰዓት የተለያዩ ሀገርኛ ፊልሞችን ያሳያል።