27/07/2026
ቀዳሚው ኢስላም በኢትዮጵያ
✅✅✅✅✅✅✅✅✅
በአሕመዲን ጀበል
💥💥💥💥💥💥
ኢትዮጵያ ከመካ ቀጥሎ እንደ ሀገር ኢስላምን በመቀበለል 2ኛ ሀገር ነች። ኢስላም በኢትዮጵያ ከመዲና በ7 ዓመት በላይ፥ ከየመን፥ኦማን፥ኳታርና ባህሬን ከእያንዳንዳቸው በ13 ዓመታት ይቀድማል።
ከሶማሊያና የተባበሩት ዐረብ ኢምሬት ደግሞ በ15 ዓመት፥ ከኢራንና ኢራቅ በ18 ሲቀድም ፥ከሶሪያ፥ ፍሊስጤምና ዮርዳኖስ ደግሞ በ21 ዓመታት ይቀድማል። ከግብጽ ደግሞ በ25 ዓመት፥ ከሊቢያ በ32 ዓመታት ሲቀድም ከአፍጋኒስታን እና ከሱዳን ደግሞ በ37 ዓመታት ቀድሞ ደርሷል። ከቱኒዚያና አልጄሪያ በ55 ዓመት፥ ከሞሮኮ ደግሞ በ67 ዓመት ይቀድማል።
ከስፔን(አንደሉስ) እና ፖርቹጋል ደግሞ በ96 ዓመት ይቀድማቸዋል። ከዑዝቤኪስታን በ95፥ ከፓኪስታን በ96፥ከህንድ በ97 ዓመታት ቀድሟል።
ከካዛኪስታንና ቱርክ በ135 ዓመታት ሲቀድም ከባንግላዴሽ ደግሞ በ385 ሲቀድም ከማሌዚያ እና ኢንዶኔዢያ በ585 ዓመታት ቀድሞ ተሰብኳል። እንዲህ እያለ ኢስላም በኢትዮጵያ መሰበኩ ከመካ ከተማ ዉጭ ያሉትን ሁሉንም የዓለም ሀገራትን ይቀድማል።
በዓለም ታሪክ ከመካ በስተቀር በሀገሩ ኢስላም 1456 ዓመታት የቆየባት አንድም ሀገር ከኢትዮጵያ በቀር የለም።
ዛሬ በሒጅራ ዘመን አቆጣጠር 1448 ሲሆን ኢስላም በኢትዮጵያ የደረሰው የዘመን መቁጠሪያው መጀመር(ከነቢዩ ወደ መዲና ስደት) ሰባት ዓመት ቀድሞ በመድረሱ የኢስላም ታሪክ በኢትዮጵያ 1456 ዓመት ሆኗል።
ከዚህ የተነሳ ኢስላም ከሂጅራ የዘመን አቆጣጠር (ካላንደር) ጭምር የቀደመ ታሪክ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች።ኢትዮጵያ ይህን ስፍራ እንድታገኝ የተመረጠችው በኛ በሙስሊሞች ሳይሆን በኢስላም ራሱ ነው።
«ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የኢስላምና የሀገር ባለቤቶችና የታሪኩ መሠረቶች»
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
አንዳንድ አካላት ኢስላም ከዐረብ ሀገራት ጋር ተያይዞ እንዲታይ ይሻሉ። በአላህ የተመረጠልንን ኢስላምን የግድ ከሀገራት ጋር ማያያዝ ካስፈለገ ከየትኛውም ሀገር በላይ ለዚህ ብቁ የምትሆነው ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት። ምክንያቶቹ ደግሞ በርካታ
ናቸው።
1) የአላህ ነቢይ የሆኑትን ነቢዩ ሙሐመድን(ሰዐወ) ሞግዚት ሆና ያሳደገችው ኢትዮጵያዊቷ ዑሙ አይመን በረካ መሆኗ።
2) ከየትኛውም የዓላም ሀገር ኢስላም ከመካ ቀጥሎ መዲና እንኳን ሳይገባ ወደ ኢትዮጵያ የገባ መሆኑ።
3) የነቢዩ ሰሀቦችን ከለላ የሰጠ፣በጊዜው መካ ዉስጥ 40 ሙስሊሞች ብቻ ቀርተው ኢትዮጵያ ዉስጥ 101 ሰሀቦች የነበረ መሆኑ።
4) በኢስላም ታሪክ የመጀመሪያው ሙአዚን ኢትዮጵያዊው ቢላል ኢብኑ ረባህ መሆኑ።
5) እንደ መሪ ነጃሺ ከአፍሪካም ሆነ ከዓለም የመጀመሪያው ሙስሊም መሪ መሆኑ።
6) በነቢዩ ሙሀመድ ኢትዮጵያ "የእውነት ምድር" ተብሏ መወደሷ።
7) ንጉሥ ነጃሺ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) "እርሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት" መሪ መባሉ።
8) ወደ ኢትዮጵያ የገባው ኢስላማዊ አስተምህሮ የትኛውም መዝሀብ፣መንሀጅ፣ሱሉክ (ለምሳሌ ተሰዉፍ፣ሱፍያ)፣አሰሪ፣አሽዓሪ፣ሺዓ፣ወዘተ የሚሰኙ ቅጥያዎች ጭምር ሳይፈጠሩ ኢስላምና ሙስሊም ብቻ ተብለው የሚጠራ ስያሜን የያዘ መሆኑ።
ከነዚህ በተጨማሪ በርካታ ነጥቦች ሊዘረዘሩ ይችላሉ።
እስልምና ወደ ኢትዮጵያ የገባው አብዛኛዎቹ የዓለም ሀገራት ከመቀበላቸው ቀድሞ በመሆኑ ኢትዮጵያ በኢስላም ታሪክ ውስጥ የአስተማሪነት እንጂ የተማሪነት ስፍራ የላትም።
በመሆኑም ከኢትዮጵያ በኋላ እስልምናን የተቀበሉ ሀገራትን እንደ ተፅዕኖ ፈጣሪ አድርጎ ማሰብ ወይም የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ታማኝነት መጠራጠር የታሪክ ድንቁርና ነው።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀገራቸውን ድንበር ሲያስከብሩ፣ ባህሏን ሲገነቡና ታሪኳን ሲጽፉ የኖሩ የመሠረት ድንጋዮች ናቸው።
ኢስላም በሀገራችን የጸናው በወረራ ሳይሆን በፍትሕ፣ በጽድቅና በራሳቸው በኢትዮጵያውያን መልካም ፈቃድና እንግዳ ተቀባይነት ነው።
ይህ ከመካ ቀጥሎ በዓለም ሁለተኛ የመሆን ታሪካዊ ምዕራፍ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን የታሪክ ሀብትና ኩራት ነው።
ይህንን ታላቅ የፍትሕና የአብሮነት ውርስ ጠብቆ ማቆየትና ለእውነተኛው የፍትህ፣ እኩልነትና ሀገር ግንባታ ታሪክ ለመጻፍ መቆም የዚህ ትውልድ የማይታጠፍ አደራ ነው።
አበቃሁ። ቸር እንሰንብት!
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
የአሕመዲን ጀበል የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ! ሊንኩ ከሥር በአስተያየት መስጫው ስር ተጠቅሷል።👇
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥