Newspaper role

Newspaper role Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Newspaper role, Media/News Company, Addis Ababa.

25/09/2026
12/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት

በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያይተናል።
‎
‎ከጉባኤው ጎን ለጎን ባደረግነው ውይይት በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የውይይትን አስፈላጊነት እና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረናል።

በፍፁም ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው!! በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የተስተዋለውና አንድ አሽከርካሪ የትራፊክ ደንብ በመጣሱ ምክንያት ቅጣት ሲጣልበት ከትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ወደ...
02/09/2026

በፍፁም ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው!!

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የተስተዋለውና አንድ አሽከርካሪ የትራፊክ ደንብ በመጣሱ ምክንያት ቅጣት ሲጣልበት ከትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ወደ አካላዊ ግጭትና ድብድብ ሲገባ የሚያሳየው ምስል እጅግ አሳፋሪ ነው።

ህግ አስከባሪዎች የራሳቸውን የግል ፍላጎት ሳይሆን የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ በስፍራው የተገኙ የመንግስት እና የህዝብ ወኪሎች ናቸው። እነሱን መንካት፣ መሳደብ ወይም መደብደብ ቀጥታ ህግንና ስርዓትን እንደመደብደብ፣ እንዲሁም የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ እንደመጣል ይቆጠራል።

በዚህ ድርጊት ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮች አብዛኛውን ጊዜ የሚያተኩሩት "ቅጣቱ በዛ" ወይም "ለምን ታርጋ ይፈታል" በሚሉ የቅጣት አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ነው። ነገር ግን ትልቁና መሰረታዊው ጥያቄ መሆን ያለበት፣ "አሽከርካሪው ገና ከመነሻው ለምን የትራፊክ ህግን ጥሶ ተገኘ?" የሚለው ነው።

የትራፊክ ህጎች የተነደፉት የዜጎችን ውድ ህይወት ለመታደግ እና የሀገርን ሀብት ከውድመት ለመጠበቅ ነው። የትራፊክ አደጋ በሰው አካል፣ ህይወት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰው ዘግናኝ ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ ስንት ቤተሰብን በትኗል፣ ስንቱን አካል ጉዳተኛ አድርጓል። ይህንን እልቂት ለማስቆም፣ ስርዓት እንዲከበርና አደጋዎች እንዲቀንሱ ከተፈለገ፣ ህግን መተላለፍ የሚያስከትለው ዋጋ እጅግ ከባድ ሊሆን ይገባል።

ያደጉትን ሀገራት ተሞክሮ ብንመለከት፣ ለምሳሌ በአሜሪካ የትራፊክ ህግን መተላለፍ የሚያስከትለው የገንዘብ ቅጣት እጅግ በጣም ከፍተኛ እና አንዳንዴም የመንጃ ፈቃድን እስከማሳጣት የሚያደርስ ነው። ከቅጣቱ ክብደት የተነሳ አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ ህግን ላለመጣስም ይጥራሉ።

ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ግን "ትንሽ ተሳሳቱ፣ ስለዚህ ትንሽ ይቀጡ" የሚል የተሳሳተ አመለካከት ይስተዋላል። በሰው ህይወት ላይ የሚቀለድበት "ትንሽ ጥፋት" የለም፤ ምክንያቱም አንዲት ትንሽ የምትመስል የትኩረት ማጣት ወይም የህግ ጥሰት የብዙዎችን ህይወት በሰከንዶች ውስጥ ልትቀጥፍ ትችላለችና። ህግ ህግ ነው፤ ጥፋት ከተፈጸመ ተመጣጣኝ እና ዳግም እንዳይደገም የሚያደርግ አስተማሪ ቅጣት ሊኖር ግድ ይላል።

አንድ ግለሰብ የራሱን ጥፋት ለመሸፈን፣ ወይም ከቅጣት ለማምለጥ ብሎ የህግ አስከባሪዎችን በጉልበት ለማሸነፍ መሞከሩ ፍጹም አጸያፊና ስርአት አልበኝነት ነው።

ይህ ዓይነቱ ድርጊት ማህበረሰባዊ ቀውስን የሚጋብዝ እና በምንም ዓይነት መለኪያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

የህግ አካላት ስራቸውን በአግባቡ ሲሰሩ ሊደገፉና ሊበረታቱ እንጂ፣ በአደባባይ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው አይገባም። ማንኛውም ዜጋ ቅሬታ ካለው በሰለጠነና በህጋዊ መንገድ ማቅረብ ሲችል፣ አቋራጭ እና የጉልበት መንገድን መምረጥ ትልቅ ድንቁርና ነው።

ማህበረሰባችን ይህንን አሳፋሪ ድርጊት በጽኑ ሊያወግዘው እና የህግ የበላይነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከበር በጋራ ሊቆም ይገባል። ህግን ማክበር የፍርሃት ሳይሆን የስልጣኔ እና የኃላፊነት ስሜት መገለጫ መሆኑን ተረድተን፣ ለህግ እና ህግን ለማስከበር ለቆሙ አካላት ተገቢውን ክብር መስጠት የሁላችንም የማይደራደር ግዴታ ነው።

የመሪ አስተዋጽኦ**************ለአንድ ሀገር ወይም ማህበረሰብ ለውጥ መነሻና መድረሻን የሚያውቅ ባለራዕይ መሪ በጣም አስፈላጊ ነው። መሪ ደግሞ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር ...
27/04/2026

የመሪ አስተዋጽኦ
**************
ለአንድ ሀገር ወይም ማህበረሰብ ለውጥ መነሻና መድረሻን የሚያውቅ ባለራዕይ መሪ በጣም አስፈላጊ ነው። መሪ ደግሞ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር አርዓያ መሆን አለበት።

የለውጡን ግልጽነት መፍጠርና ሌሎችን ማብቃት ከለውጥ መሪ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው። መሪ እንቅፋቶችን በብልሃት በመለየት ስልታዊ መፍትሄ መስጠት ይጠበቅበታል። ፈጠራን ማበረታታት፣ ለውጤት እውቅና መስጠት እና ሂደቱን ማፋጠን ከለውጥ መሪ የሚፈለግ ሌላኛው ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያና አዲስ አበባችን እነዚህን እና ሌሎች የለውጥ መሪ ባህሪያትን የሚያሟሉ መሪዎች ባገኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ በክፍለ ዘመን ያልታየ የላቀ ሁለንተናዊ ለውጥን ተቀዳጅተዋል። የተመዘገቡት ለውጦች የተለየ ውጫዊ ድጋፍ ላይ ያልተንጠለጠሉና በራስ አቅም ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው የለውጡን ቀጣይነት ያረጋግጣል።

ጠ/ሚ/ር አብይ እና ከንቲባ አዳነች በሀገራችንና በከተማችን ያስመዘገቡት ውጤት ላለፉት ዓመታት አርዕስተ ዜና የሆኑና እየሆኑ የሚቀጥሉ የሀገር ታሪክና ኩራት ናቸው።

እነዚህ መሪዎች በለውጥ እሳቤያቸው፣ በውጤታማ ስትራቴጂያቸው፣ በቆራጥ ዓላማቸውና በእረፍት የለሽ ትጋታቸው ሀገራችንንና ከተማችንን ወደ ተምሳሌት ሀገርና ከተማ ይመራሉና ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።

23/04/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Newspaper role posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share