13/06/2026
ውጤታማ ተግባቦት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ
__________
"ውጤታማ ተግባቦት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ለጤናው ዘርፍ አመራሮችና ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች የተዘጋጀ የውጤታማ ተግባቦት ስልጠና በአፍርካ ሊደርሽፕ የልህቀት ማእከል እየተሰጠ ይገኛል።
የጤናው ዘርፍ ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ ትልቁ ኃላፊነት የተግባቦት ስራ መሆኑን በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው ያስረዱት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ በተለይም በአሁኑ ወቅት የተግባቦት ስራ ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ውጤታማ ተግባቦት ለአመራር ከክህሎትም በላይ ውጤታማ መሣሪያው መሆኑን ያስረዱት ዶ/ር መቅደስ፤ የዘርፉ አመራሮች ከአውደ ጥናቱ ያገኙትን እውቀት በስራቸው ለሚገኙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች በማጋራት ክህሎታቸውን እንዲገነቡ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል...More
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB