Girum Computer School

Girum Computer School Girum Computer School allows you to have a great knowledge about our current world 💪

 ሰሞኑን ወደ በርካቶቻችን በSMS እንደዚህ አይነት ሊንክ የያዙ አጫጭር መልእክቶች እየተላኩልን ይገኛሉ።ይህ ዘዴ በተለምዶ "smishing" ሲሰኝ አጭበርባሪዎች ወደ በርካታ ስልኮች sms የ...
22/11/2024



ሰሞኑን ወደ በርካቶቻችን በSMS እንደዚህ አይነት ሊንክ የያዙ አጫጭር መልእክቶች እየተላኩልን ይገኛሉ።

ይህ ዘዴ በተለምዶ "smishing" ሲሰኝ አጭበርባሪዎች ወደ በርካታ ስልኮች sms የሚልኩበት ዘዴ ነው።

እነዚህ መልዕክቶች የሚላኩት ከኖርማል ስልክ ቁጥር ነው። አብዛኞቹም ሊንኮች የtelegram link ናቸው እነዚህ የtelegram ሊንኮች pyramid scheme ወደ ተባለው እንዲሁም ብዙዎች ወደ ተበሉበት አሰራር የሚመዘግቡና የሚያስገቡ ሰዎች ጋር ይወስዳችኋል።

Pyramidal scheme ማለት በርካቶች ከስረው ትንሽ ሰዎች ብቻ የሚያተርፉበት አሰራር ነው። ለምሳሌ ያክል FIAS እኛ ሀገር የነበረ እና ብዙ ሰው ገንዘቡን የተበላበት pyramidal scheme አሰራርን የሚከተል ድርጅት ነበር።

ባጠቃላይ በsms ሆነ በማንኛውም social media ላይ የሚላኩላችሁን ሊንኮች ምንነታቸውና ማን እንደላካቸው ሳታጠሩ ባትከፍቱ የተሻለ ነው።

የቲክቶኩ መስራች Zhang yiming የቻይና ቁጥር አንድ ባለሀብት ሆነ።የByte dance ድርጅት ባለቤትና የቲክቶኩ መስራች Zhang yiming ከዚህ ቀደም ለወራት ሀለተኛ ደረጃን ይዞ የ...
19/11/2024

የቲክቶኩ መስራች Zhang yiming የቻይና ቁጥር አንድ ባለሀብት ሆነ።

የByte dance ድርጅት ባለቤትና የቲክቶኩ መስራች Zhang yiming ከዚህ ቀደም ለወራት ሀለተኛ ደረጃን ይዞ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በቻይና ቁጥር አንድ ባለሀብት መሆን ችሏል።

የ41 አመቱ ጎልማሳ አሁን ላይ ያለው ሀብት $49.3b ሲሆን 2023 ከነበረው ጋር ሲነፃፀር 43% ብልጫ አሳይቷል።

በተጨማሪም ByteDance ከባለፈው አመት 60% የገቢ ጭማሪ አሳይቷል።

ByteDance በስሩ የሚያስተዳድራቸው ኩባንያዎች
⚫Toutiao
⚫TikTok
⚫TikTok Music
⚫BuzzVideo
⚫CapCut
⚫Lark
⚫Baike.com
⚫PICO
⚫Lemon8
⚫Whee

ከእነዚህ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው Tiktok በአለማችን ተወዳጅ የማህበራዊ ሚዲያ ቢሆንም በርካታ ሀገራት በተለያዩ ሰበቦች ይህንን ሚዲያ እያገዱት ይገኛሉ።

አትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል  " የደቡብ ቁልቢ " የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገረሙጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከዞና...
27/01/2024

አትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል
" የደቡብ ቁልቢ "

የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገረሙጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከዞናችን ዋና ከተማ ወልቂጤ በ52 ኪ.ሜ እና የእዣ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው አገና በ10 ኪ.ሜ ርቀት በስተ-ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ነው።
ካቴድሪያሉ በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን በስደት ከአክሱም ፂዮን "ወሰናይ " ተብለው ይጠሩ በነበሩት አባት ከብዙ በጉዞአቸው ላይ ከነበረው ብዙ ተዓምር በኋላ ይዘው በማምጣት እንደሰየሙት በጉራጌ ሀገረ-ስብከት የእዣ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስራአስኪያጅ እና የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ብርሃን ብስራት አካለ ወልድ ይናገራሉ ።

በየዓመቱ ጥር 18 በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በመሳተፍ በድምቀት የሚከበረው ካቴድሪያሉ በአባታችን በአቡነ መልከ-ፄዲቅ ከተለያየ ቦታ በመምጣት እጅግ ቁጥር ያላቸው እንግዶች በክብረ -በዓሉ መገኘትና የተሳሉትን ስለት ቶሎ የሚሰማ መሆኑን ብዙዎቹ በመመስከራቸው ምክንያት " የደቡብ ቁልቢ " የሚል ስያሜ እንደሰጡትም የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ብርሀን ብስራት አካለወልድ ያስረዳሉ ።
በካቴድሪያሉ ከነሀስና ብር የተሰሩ ጥንታዊ መስቀሎች ፡ ፅዋዎች ፡ የተለያዩና እድሜ ጠገብ የብራና መፅሀፎች ፡ የጥበቃ መሳሪያዎችና በርካታ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞ ሀገርመሪ በነበሩ እንደ አፄ ሚኒሊክ ፡ ደጅ አዝማቾች ፡ ደጅ አዝማች ባልቻ ፡ ደጅ አዝማች ሀብተ -ጊዮርጊስ የተበረከቱ ቅርሶች በካቴድሪያሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰራው ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ መመልከት ወይም መጎብኘት ይቻላል ።

ካቴድሪያሉ ከሀይማኖት ስርዓት በተጨማሪ ከእምነቱ ተከታዮች ውጪ ያሉትም ጨምሮ በተለያየ ማህበራዊ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በደንና አካባቢ ጥበቃ ስራ አሻራ እያኖረ ያለና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ወገኖች በቋሚነትም ይረዳል ።
ይህን ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮዓዊ እና የበርካታ ቅርስ ባለቤት የሆነውን ካቴድሪያል እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ።

"አንትሮሽት" የጉራጌ የእናቶች በዓል  በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በቀጣነ  ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት መከበሩ ከአዣ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።አንትሮሽት በጉ...
25/01/2024

"አንትሮሽት" የጉራጌ የእናቶች በዓል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በቀጣነ ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት መከበሩ ከአዣ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

አንትሮሽት በጉራጌ ህዝብ ዘንድ እናቶችን ለማክበር እና ለድካማቸው እውቅና ለመስጠት የሚደረግ ክብረ በዓል ነው። ይህ ባህል በበርካታ ወገኖች ጥረት ከተረሳበት ዳግም እያንሰራራ ይገኛል።

ህዳር 4/2016ዓ.ም ===========በእኖር ወረዳ እናንገራ ቀበሌ የሚገኘው ውብ ጀፎሮ/ጀፎረየጉራጌ ህዝብ በዋነኛነት ከሚታወቅባቸው ውብ ሀብቶቹ መካከል አንዱ የመንደር አመሰራረቱ ነው።የጉ...
14/11/2023

ህዳር 4/2016ዓ.ም
===========
በእኖር ወረዳ እናንገራ ቀበሌ የሚገኘው ውብ ጀፎሮ/ጀፎረ

የጉራጌ ህዝብ በዋነኛነት ከሚታወቅባቸው ውብ ሀብቶቹ መካከል አንዱ የመንደር አመሰራረቱ ነው።

የጉራጌ የመንደር አመሰራረትም መሰረት የሚያደርገው ጀፎረ ሲሆን፣ ይህም አረንጓዴ ሳር ለብሶ ውብና ማራኪ ገጽ ያለውና ባህላዊ ጎጆ ቤቶች ታጅቦ በሁለት መንደሮች መካከል በትይዩ የሚገኝ ነው።

የአካባቢው ነዋሪዎች የጋራ መጠቀሚያ፣ መተላለፊያ፣ መግቢያና መውጫ የሆነ ሰፊ መሬት ነው።

የጉራጌ ጀፎረ አጭር ሳይሆን ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚዘለቅ ረጅም መንገድ ነው፡፡

በጆፈረ መንገድ ዳር ላይ አገር በቀል ዛፎች የሚተከሉ ሲሆን፣ ዛፎቹ ለባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓት እና ለሌሎች ባህላዊ ክንዋኔዎች እንደ ጥላ ያገለግላሉ፡፡

ይህንን ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው በእኖር ወረዳ የሚገኘው የእናንገራ ጀፎሮ ነው።
እነዚህ ውብ ሀብቶቻችን በጋራ እንጠብቅ የዕለቱ መልዕክታችን ነው።

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ጥቅምት11/2016ዓ.ም (ወልቂጤ)==================ከኮማንድ ፓስት የተሰጠ መግለጫ  ሰላም ወዳዱ ማህበረሰባችን በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ እና ወደ መደበኛ ስራው እንዳይመለስ የሚያደ...
22/10/2023

ጥቅምት11/2016ዓ.ም (ወልቂጤ)
==================
ከኮማንድ ፓስት የተሰጠ መግለጫ

ሰላም ወዳዱ ማህበረሰባችን በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ እና ወደ መደበኛ ስራው እንዳይመለስ የሚያደርጉ ህገ-ወጥ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን ለዘላቂ ሰላም ሲባል የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ስራ እየሰሩ መሆኑን ይታወቃል።

በዚህ መሰረት፣
==========
1ኛ, በየቦታው የተለያዩ ትንኮሳዎችን በመፍጠር የከተማውን ማህበረሰብ እንዳይረጋጋ ማድረግ፣

2ኛ, በተሽከርካሪ እና በእግር የሚንቀሳቀሱ ዜጎች ላይ ህገ-ወጥ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው መቆም መቻል አለበት፣

3ኛ, ይህንን ጥብቅ መልዕክት ከተላለፈበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ መመሪያውን ሳይቀበል ወይም ተግባራዊ ሳያደርግ ቀርቶ በህገ-ወጥ ድርጊቱ የሚሳተፍ የየመዋቅሩ የቀበሌ አመራርና ግለሰብ በጸጥታው አካሉ ለሚወሰድበት እርምጃ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን !!

ከጊዜያዊ ኮማንድ ፓስት

መረጃው :- የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

ጥቅምት 08/2016 ዓ.ም===================የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ወልቂጤ ከተማ ወደ ተለመደው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሳለች።በከተማው የሚገኙ የመንግስትና የንግድ ተቋማ...
19/10/2023

ጥቅምት 08/2016 ዓ.ም
===================

የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ወልቂጤ ከተማ ወደ ተለመደው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሳለች።

በከተማው የሚገኙ የመንግስትና የንግድ ተቋማት ትራንስፓርትን ጨምሮ ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።

ከተማው በአራቱም አቅጣጫ የሚመጡ እንግዶች በተለመደው የጉራጌ የእንግዳ አቀባበል ባህል መሰረት ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል።

አሁን ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም የጸጥታ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው።

የወልቂጤ ከተማ የዛሬ የሰዓት በኋላ ገጽታ ነው።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን

ዘቢዳር ተራራ  (የመሰረተ-ወገራም- ዳሙ-ሲቢስቶ-ኑረና-አማውቴ ጨምሮ የተራራው ምስራቃዊ ክፍል) ሊለማ ነው፡፡የተራራው ቆላማው አካባቢ እና ከቡታጅራ አናት ከወይና-ደጋማዋ እስከ አማውቴ መጨረ...
18/10/2023

ዘቢዳር ተራራ (የመሰረተ-ወገራም- ዳሙ-ሲቢስቶ-ኑረና-አማውቴ ጨምሮ የተራራው ምስራቃዊ ክፍል) ሊለማ ነው፡፡

የተራራው ቆላማው አካባቢ እና ከቡታጅራ አናት ከወይና-ደጋማዋ እስከ አማውቴ መጨረሻ (በዘቢዳር ምስራቃዊ ክፍል) በተደጋጋሚ በሰደድ እሳት የሚጠቃ ስፍራ አንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡ የተራራው የብዝሐ-ህይወት ሃብት በመመናመኑም እፅዋትና ብርቅዬ እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል፡፡

ይህንን ችግር በዘለቄታዊነት ይቀይራል የተባለው እና ''ግሪን አፍሪካ ኢኒሼቲቭ'' የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ባለሐብቶች እና የመንግሥት መዋቅሮች ጋር በመሆን የአካባቢውን መራቆት በማስቀረት ለማልማት ወደ ስራ መግባቱ ተሰምቷል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የአካባቢው የቱሪዝም እድሎች ከማስፋቱም በተጨማሪ በሰንሰለታማ ተራራ ደን ጨፍጭፈው ለማስቀረት በማገዶና በከሰል ሽያጭ እንዲሁም በከፊል እርሻ ይተዳደሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በዚህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በማቀፍ የብዝኃ ህይወት ጥበቃ ይደረጋል ተብሏል።

በተጨማሪም የተራራው ደን፣ ውሃና አፈር መልሶ እንዲያገግም በማድረግ ለንብ_ማነብ፣ የቱሪዝም መስህብ እና የእንስሳት እርባታ ይካሔዳል ተብሏል፡፡

የሶዶ ለማ መተጃን ጠቅሶ ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር ፌስቡክ ገፅ ዘግቧል።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ

ወልቂጤ ከ6 ቀናት በኋላ  የሰላም አየር መንፈስ ጀምሯል 🙏
18/10/2023

ወልቂጤ ከ6 ቀናት በኋላ የሰላም አየር መንፈስ ጀምሯል 🙏

Address

Addis Abeba
Addis Abeba

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Girum Computer School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Girum Computer School:

Share