Goh Tube

Goh Tube የእውነት ነፀብራቅ!! https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ ታህሳስ 6/ 2018 ዓ.ምየሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘበኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የ...
15/12/2025

ጎህ ታህሳስ 6/ 2018 ዓ.ም

የሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘ

በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙን ተናግሯል፡፡

የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ ሀገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ ሲሆን ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ሀገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል ተብሏል።

ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች: -

ከታሀሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ ወዲያውኑ ማቋረጥ ይጠበቅባችኋል ሲል አገልገሎቱ አሳስቧል።

ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች (Deposit Gateways) አገልግሎት መስጠት ማቆም አለባቸውም ተብሏል።

ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችን እና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው የማቆየት ግዴታ አለባቸው፤ ማስረጃን ማጥፋት፣ መቀየር ወይም ማሸሽ በወንጀል ሕጉ መሰረት ያስቀጣል ተብሏል።

የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ፔይመንት ኢንስቱርመንት ኢሹወርስ እና ፔይመንት ሲስተም ኦፕሬተሮች ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ የሁሉም የውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ በመሰረዙ፣ በእናንተ በኩል የውርርድ ድርጅቶቹ የሽያጭ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ  ታህሳስ 2/ 2018 ዓ.ምሕወሃት የትግራይን ሕገመንግሥታዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና በትግራይ ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ለማስፈን በሙሉ ...
11/12/2025

ጎህ ታህሳስ 2/ 2018 ዓ.ም

ሕወሃት የትግራይን ሕገመንግሥታዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና በትግራይ ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ለማስፈን በሙሉ ኃይሉ ለመታገል መወሰኑን ተናገረ

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አደጋ ላይ የወደቀው፣ አደራዳሪ አካላት እና ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ግፊት ባለማድረጋችው የተነሳ ነው በማላት ወቅሷል።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ የትግራይ ጸጥታ ኃይል አባላት የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲፋጠኑ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎቻቸው እንዲሟሉ ውሳኔ ማሳለፉንም አስታውቋል።

በክልሉ በመልካም አስተዳደር መስክ የሚታየው ሙስና እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ችግሩ በተደራጀ የጅምላ ንቅናቄ እንዲፈታ ስምምነት ላይ መድረሱንም ተናግሯል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ  ታህሳስ 1/2018 ዓ.ምከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በአቅም ችግር ምክንያት ስራውን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡ ተሰማአሻም በቴሌቪዥንም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ከዛሬ ታህሳስ...
10/12/2025

ጎህ ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም

ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በአቅም ችግር ምክንያት ስራውን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡ ተሰማ

አሻም በቴሌቪዥንም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን የቦርድ አባላቱ ተናግረዋል።

ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባላት በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተችበት ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ስታደርስ የመቆየቷን ያስታወሰው መግለጫው ሆኖም አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ስራዋን ለመቀጠል አቅም ስለሌላት በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን አሳውቋል።

ስለሆነም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉም ቦርዱ ተናግሯል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ ሕዳር 30 /2018 ዓ.ምምርጫ ቦርድ በአቶ ጌታቸው ረዳ  ለሚመራው ስምረት የክልል ፓርቲነት ህጋዊ እውቅና ሰጠየ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር...
09/12/2025

ጎህ ሕዳር 30 /2018 ዓ.ም

ምርጫ ቦርድ በአቶ ጌታቸው ረዳ ለሚመራው ስምረት የክልል ፓርቲነት ህጋዊ እውቅና ሰጠ

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ባሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ ለሚመራው ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) የክልል ፓርቲነት ህጋዊ እውቅና ሰጥቷል።

በቀድሞው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተመሠረተው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ በጥቅምት ወር አቶ ጌታቸው ረዳን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የተሰጠው ፖርቲው፣ በትግራይ ክልል አዲስ የፖለቲካ እይታ ለማቅረብ እና “ ህወሓትም ሆነ ኢህአዴግ በዓለም ማሕበረሰብ ዘንድ ይቀርብባቸው የነበረ ሂስን ከመሰረቱ ለሚያርም” የተመሰረተ መሆኑን መስራቾቹ ተናግረዋል።

የስምረት የውጭ ግንኙነት አስተባባሪ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ከዚህ ቀደም ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት፤ ፓርቲው የተመሰረተው “ዓለማችን አሁን የደረሰችበት አስተሳሰብ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የአካባቢያውን እና የሀገሪቱን አጠቃላይ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም ትግራይ ወስጥ በተለይ አርሶ አደሩ፣ በወጣቱና በምሁሩ እየተቀጣጠለ ያለው የለውጥ ፍላጎት ለማሟላላት ታሳቢ ያደረገ አስተሳሰብ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ነው” ብለዋል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ  ሕዳር  29 /2018 ዓ.ምኢትዮጵያ በ10 ዓመት፤ ከተቻለም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ትገነባለች ተባለዛሬ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ዝግጅት...
08/12/2025

ጎህ ሕዳር 29 /2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በ10 ዓመት፤ ከተቻለም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ትገነባለች ተባለ

ዛሬ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ዝግጅት፣የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ መጀመር ይፋ ተደርጓል።

በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንም ስራዬን መጀመሬን እወቁት ብሏል።

የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱን ለመገንባት ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (አይ.ኤ.ኢ.ኤ) የሚያስቀምጣቸውን 19 መሠረታዊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቃል ተብሏል።

ኢትዮጵያም ይህንኑ መስፈርት አሟልታ በተቆጣጣሪ ኤጀንሲው እገዛና ክትትል ለመስራት ዝግጁ ነች ተብሏል።

የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ሲናገሩ እንደሰማነው የስራው ሂደት ሶስት ምዕራፎች ይኖሩታል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ስራውን ለመጀመር ዝግጁ መሆን የሚበሰርበት የዛሬው አይነት ሂደት ነው ብለዋል።

ሁለተኛው ምእራፍ አማራጭና የግንባታ ቦታን መለየት፣የቴክኖሎጂ መረጣ የጨረታ ሂደትና ሌሎችንም ስራዎች ያጠቃልላል ብለዋል።

ሶስተኛው ምእራፍ የግባታውን ስራ ማጠናቀቅን የሚመለከት እንደሆነ አብራርተዋል።

እያደገ ባለው የሀይል ፍላጎት ውስጥ የኒክሊየር ሀይል ተጨማሪ አማራጭ እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጤሞቲዮስ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱን ተዓማኒ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በፍጥነት መገንባት አለባት ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የዓለም አቀፉ የኒክሊየር ኃይል ማመንጫ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭ(ዶ/ር) ናቸው።

ኢትዮጵያ ከሁለት ወር በፊት የኒክሊየር የኃይል ማመንጫውን ለመገንባት ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ነው።

ዛሬ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ጋር በትብብር የተሰናዳው ዝግጅትም ወደ ስራ መገባቱን ማብሰሪያ ትልቁ ምእራፍ ነው መባሉን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ ሕዳር 26 /2018 ዓ.ምየቀድሞው የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው።አቶ ታዬ ዛሬ ...
05/12/2025

ጎህ ሕዳር 26 /2018 ዓ.ም

የቀድሞው የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው።

አቶ ታዬ ዛሬ አርብ ኅዳር 26/2018 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ጥፋተኛ በተባሉበት ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ነው።

የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ሕገ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው በቤታቸው ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ60 ጥይቶች ጋር ተገኝቷል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ  ሕዳር  25 /2018 ዓ.ምየህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ እንዲሳተፉ  የድጋፍ ፊርማ እንዲያቀርቡ የሚደነግገዉን የህግ አዋጅ እንዲታገድ ወሰነምክር ቤት 5ኛ ...
04/12/2025

ጎህ ሕዳር 25 /2018 ዓ.ም

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ እንዲሳተፉ የድጋፍ ፊርማ እንዲያቀርቡ የሚደነግገዉን የህግ አዋጅ እንዲታገድ ወሰነ

ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባዉን ዛሬ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አሻሽሎ አዋጅ 1397/2018 ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ከዚህ በፊት በነበረዉ አዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 32 ንኡስ አንቀጽ ሁለት መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ለሚያቀርቧቸዉ እያንዳንዳቸው እጩዎች የድጋፍ ፊርማ እንዲያቀርቡ ይጠይቃል።

7ተኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ከሚደረገዉ ዝግጅት አንዱ በምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት የድጋፍ ፊርማ ሲሆን፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ ፊርማ ለማሰባሰብ በቂ ጊዜ ባለመኖሩ የድጋፍ ፊርማ ለማሰባሰብ የተደነገገዉ አንቀጽ እንዲታገድ ለምክር ቤቱ የጽሁፍ ጥያቄ አቅርበዋል።

በመሆኑም የፖለተካ ፓርቲዎች ይህንን ጥያቄ እያቀረቡ የድጋፍ ፊርማዉ ተግባራዊ ይደረግ ቢባል በምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚጎዳ በመሆኑ አዋጅ 1162/2011 ታግዶ አዋጅ 1397/2018 ተግባራዊ ማድረግ ማስፈለጉም ተነግሯል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ  ሕዳር  25 /2018 ዓ.ምየትግራይ የጸጥታ ሃይሎች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ጽ/ቤት መክበባቸው ተሰማየትግራይ የጸጥታ ሃይል አባላት “ደሞዝ ዘግይቷል” በሚል ትጥቃቸውን በመያዝ መቀ...
04/12/2025

ጎህ ሕዳር 25 /2018 ዓ.ም

የትግራይ የጸጥታ ሃይሎች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ጽ/ቤት መክበባቸው ተሰማ

የትግራይ የጸጥታ ሃይል አባላት “ደሞዝ ዘግይቷል” በሚል ትጥቃቸውን በመያዝ መቀለ የሚገኝውን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ህንጻ ከበው አርፍደዋል ተብሏል።

ከ70 በላይ የሚሆኑ የሰራዊት 31 አባላት ትናንት ረቡዕ ምሽት አራጉሬ (እንደርታ) አካባቢ የሚገኝውን ካምፓቸውን ለቀው እንደወጡ ቢቢሲ ዘግቧል።

ዛሬ ጠዋት የአስተዳደር ህንፃውን መክበባቸውን የዘገበው ቢቢሲ መሳሪያዎቹ ከካላሽንኮቭ እስከ ዲሽቃ ይደርሳል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የቅርብ አዛዦቻቸው ሊያናግሯቸው ቢሞክሩም ታጣቂዎቹ“ከፍተኛ አዛዦች ወደ እኛ ይምጡ” ሲሉም ተደምጠዋል።

የፌደራል መንግሥቱ በጀት በወቅቱ ባለመልቀቁ በትግራይ ክልል ደመወዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ህወሃት በተናጠል ለፌደራል መንግስቱ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ ሕዳር 25/2018 ዓ.ምኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የ ግብፅን የቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ውድቅ አደረገች በአፍሪካ ቀንድ ተላላኪ፣ ደካማ እና የተከፋፈሉ ጥገኛ መንግስታትን ለ...
04/12/2025

ጎህ ሕዳር 25/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የ ግብፅን የቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ውድቅ አደረገች

በአፍሪካ ቀንድ ተላላኪ፣ ደካማ እና የተከፋፈሉ ጥገኛ መንግስታትን ለመፍጠር ያላትን ፍላጎት ኢትዮጵያ በፅኑ ተቃውማለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ረቡዕ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ባወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ፣ ከፍተኛ የግብፅ ባለሥልጣናት በአባይ ወንዝ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ፀብ አጫሪ ንግግራቸውን እያባባሱ እና “በፍጹም ንግግርን ወደ ጎን ቸል በማለት እየተቀበሉ አይደለም” በማለት ተችቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርብ ጊዜያት ከካይሮ በኩል የተሰጡ አስተያየቶችን የግብፅ መንግሥት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን እውነታዎች ለመቀበል ያለመቻሉ መገለጫዎች ናቸው ብሏል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው አክሎም፣ አንዳንድ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አሁንም በቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ውስጥ የተዘፈቁ መሆናቸውን እንዲሁም በአባይ ወንዝ ላይ የብቸኛ ባለቤትነት ወይም የጠቅላይነት አመለካከት አላቸው ሲል በፅኑ ኮንኗል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ግብፅ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን በተደጋጋሚ ማንሳቷን አጥብቆ የተቸ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ካይሮ ለመተው እየከበዳት ያሉትን የቅኝ ግዛት ቅሪቶችን የምትሸከምበት ጫንቃም ሆነ የምታስተናግድበት ምንም ቦታ የላትም ሲል አበክሮ ገልጿል።

እነሱ [ግብፆች] የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን በመጥቀስ ስለ ‘ታሪካዊ መብቶቻቸው’ ያወሳሉ ያለው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ ይህ የተሳሳተ አካሄድ እና ጥረት የአስተሳሰብ እና አመራር ውድቀት ነው። ኢትዮጵያን በፍጹም የማያስበረግጋትን ይህን የጃጀ የጨዋታ መመሪያ እና መርህ ለመተው ጊዜው አሁን ነው ሲል አፅንኦት ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ግብፅ የአፍሪካ ቀንድን ለማተራመስ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ጥረት ማድረጓን በመጥቀስ የወቀሰ ሲሆን፤ አያይዞም የግብፅ ባለሥልጣናት “ተላላኪ፣ ደካማ እና የተከፋፈሉ ጥገኛ መንግስታት”ን ለማስፈን በማሰብ “በኢትዮጵያ ላይ ያተኮረ ቢሆንም በኢትዮጵያ ብቻ ያልተገደበ ቀጠናውን የማተራመስ ዘመቻ” ታካሄዳለች ሲል ከሷል።

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

ጎህ ሕዳር 24/2018 ዓ.ምበአፍሪካ አገልግሎት ለማግኘት 75 ሚሊዮን ዜጎች ጉቦ እንደሚከፍሉ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ተናገረ በአለም አቀፍ ደረጃ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ እየተንሰራፋ እን...
03/12/2025

ጎህ ሕዳር 24/2018 ዓ.ም

በአፍሪካ አገልግሎት ለማግኘት 75 ሚሊዮን ዜጎች ጉቦ እንደሚከፍሉ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ተናገረ

በአለም አቀፍ ደረጃ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ እየተንሰራፋ እንደሚገኝ የተናገረው ተቋሙ በአፍሪካ ያለው ግን የከፋ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በተቋሙ ጥናት መሰረት፣ ባለፉት ዓመታት በአህጉሪቱ ያለው የሙስና መጠን 58 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በአፍሪካ ዜጎች ጉቦ የሚከፍሉት ከሰሩት ወንጀል ለማምለጥ አሊያም አገልግሎት ለማግኘት መሆኑንም ትራንስፓረንሲ ጠቁሟል ።

ተቋሙ መረጃውን ይፋ ያደረገው በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የአለም የሙስና ቀን በማስመልከት ነው።

በአህጉሪቱ በሙስና ይሳተፋሉ ተብለው በዋናነት ከተጠቀሱት መካከል የህግ አካላት ይገኙበታል ተብሏል።

የጉምሩክ ሰራተኞችና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ደግሞ በተከታይነት ተቀምጠዋል፡፡

https://t.me/+s_rwaEvptzQ0YmU0

Address

Addis Abeba

Telephone

+251111257936

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goh Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share