Goh Tv

Goh Tv ለመረጃ ተደራሽነት ሁሌም እንተጋለን!!

ለግንባታ ሚሊዮኖች ብር ከፈሰሰበት በኋላ ሥራ አቁሞ የተዘጋው የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲመለስ የ850 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ፀድቆለታል ተባለ፡፡ ፋብሪካው በ2,000 ሄክታር ቦ...
22/05/2025

ለግንባታ ሚሊዮኖች ብር ከፈሰሰበት በኋላ ሥራ አቁሞ የተዘጋው የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲመለስ የ850 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ፀድቆለታል ተባለ፡፡

ፋብሪካው በ2,000 ሄክታር ቦታ ላይ የአገዳ ልማት እየተከናወነለት መሆኑን ሰምተናል፡፡

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ይህ ሁሉ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ በ2018 ዓ.ም ማገባደጃ ወይም 2019 መግቢያ ምርት ማምረት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የአየር ጠባዩ የሚስማማ ውሀውም የተንጣለ ቦታ በመሆኑ ሌሎች የሰብል ምርቶችን ለማምረት ወደ ስራ ተገብቷል ተብሏል።

የጣና በለስ ስኴር ፋብሪካ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በአመራር የተሻለ እንዲሆነእ በየደረጃው እየተደገፈ ነው ተብሏል።

ወሬውን የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) ነግረውናል።

ለዚህ ፕሮጀክት የተፈቀደው 850 ሚሊየን ብር ድጋፍ ደረጃ በደረጃ ስራዎች እየታዩ እና እየተቆጠሩ የሚለቀቅ መሆኑንም ሰምተናል።

ተህቦ ንጉሴ

ለመረጃ ተደራሽነት ሁሌም እንተጋለን!!

ከ2011 ዓ.ም ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት እየቀነሰ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ተናገረ ከ2011 ዓ.ም ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት እየቀነ...
22/05/2025

ከ2011 ዓ.ም ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት እየቀነሰ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ተናገረ

ከ2011 ዓ.ም ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት እየቀነሰ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን አደረኩት ባለው ጥናት አስታውቋል።

ለዚህም የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም እና የሰላምና ፀጥታ ችግር በምክንያትነት የሚነሳ ጉዳይ ነው።

ከተጠቀሰው ዓመት ወዲህ የምርት ፍላጎትና ምርታማነት አለመጣጣም መኖሩን ከአሶሴሽኑ ሰምተናል።

በመሆኑም የዜጎች የመግዛት አቅምም አብሮ መዳከሙ ነው የተገለፀው።

እነዚህን የተጠቀሱ ችግሮች ለመፍታት የግብርና ኢንቨስትመንትን መጨመርና ለግብርናው ዘርፍ የሚመደበውን ዓመታዊ በጀት ማሳደግ አንደኛው አማራጭ መሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ሰላምና ፀጥታ ላይ ያሉ ችግሮችን መፍታት የሚቻልበትን አማራጭ መፍጠር ብሎም የገበያ ትስስር መፍጠር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት መፍትሄ ነው ተብሏል።

ዮሐንስ አበበ

ለመረጃ ተደራሽነት ሁሌም እንተጋለን!!

የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ከዛሬ ጀምሮ በመላው ቡርኪናፋሶ የወሲብ ድረገፆችን ሙሉ ለሙሉ አግደዋቸዋል ተባለ።ትራኦሬ ማንኛውንም የብልግና ምስል የሚያሰራጩ ድረገፆችን መዘጋታቸው...
22/05/2025

የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ከዛሬ ጀምሮ በመላው ቡርኪናፋሶ የወሲብ ድረገፆችን ሙሉ ለሙሉ አግደዋቸዋል ተባለ።

ትራኦሬ ማንኛውንም የብልግና ምስል የሚያሰራጩ ድረገፆችን መዘጋታቸውን ተከትሎ "እንዚህ የብልግና ደረገፆች ህዝባችንን ከማባላግ ባለፈ እሴታችንን በእጅጉ በመሸርሸር ህዝባችንን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካን እያደነዘዘ የሚገኝ አደገኛ ነገር ነው" ያሉ ሲሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የሀገራቸውን እና የአፍሪካን እሴት እንዲያስጠብቁ አሳስበዋል።

ይህን የኢብራሂም ትራኦሬን ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ በርካቶች አድናቆት እየቸሩት ይገኛሉ።

ለመረጃ ተደራሽነት ሁሌም እንተጋለን!!

ጎህ ቲቪ

23/12/2023

Address

Addis Abeba
Addis Abeba

Telephone

+251111257936

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goh Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share