Amharic News

Amharic News ሼርና ላ� ሼርና ላይክ በማድረግ ለሌሎች በማካፈል ቤተሰብ ይሁኑ::

30/12/2025

ባሉበት የሒሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ!

ውድ የባንካችን ደንበኞች፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሠረት፤ ሁሉም ደንበኞች የባንክ አገልግሎቶች ለማግኘት እና ሒሳብ ለማንቀሳቀስ የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

በዚህ መሠረት ባንካችን ደንበኞች ወደቅርንጫፍ ቀርበው የሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ከሚያጣምሩበት አሠራር በተጨማሪ ባሉበት አገልግሎቱን የሚያገኙበትን አማራጭ አመቻችቷል።

በመሆኑም ከታች በተቀመጠው የአሠራር ቅደም ተከተል መሠረት የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (16 አሀዝ-FAN Number) በማስገባት የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያጣምሩ::

1. ይህን ማስፈንጠሪያ https://cbefayda.cbe.com.et/ በመጫን/ በማስገባት ገፁን ይክፈቱ፣
2. የሂሳብ ቁጥርዎን አስገብተው ‘Get OTP’ የሚለውን ይጫኑ፣
3. ሒሳብ ሲከፍቱ ያስመዘገቡትን የስልክ ቁጥር በሚጠቀሙበት የተንቀሳቃሽ ስልክ የተላከልዎትን የአንድ ጊዜ የሚስጥር ቁጥር (OTP) አስገብተው “Verify OTP” የሚለውን በመጫን ያረጋግጡ፣
4. “Log with OTP” የሚለውን ይጫኑ፤
5. የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (16 አሀዝ-FAN Number) አስገብተው ‘Get OTP’ የሚለውን ይጫኑ፣
6. በድጋሚ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ የተላከልዎትን የአንድ ጊዜ የሚስጥር ቁጥር (OTP) አስገብተው “Verify” የሚለውን በመጫን ያረጋግጡ፣
7. “Allow” የሚለውን ይጫኑ፣
8. “Accept and Update” የሚለውን ሲጫኑ “Update complete. Pending Approval” የሚል መልእክት ይመጣልዎታል። ጨርሰዋል።
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

28/12/2025

የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ቅጥር ማስታወቂያ

በክልል ምርጫ አስፈፃሚ ምልመላ ወቅት ከፍተኛ ትችት ሲያስተናግድ የነበረው ምርጫ ቦርድ ለጣቢያ አስፈፃሚ ማስታወቂያ አውጥቷል።

"የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ለማከናወን በርካታ የቅድመ ምርጫ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። በመሆኑም ቦርዱ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል።

በዚኽም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የምታሟሉ በሁሉም ክልሎች ላይ “በምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት” ማገልገል የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ፤ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ https://nebe-election.org/recruitment በመጠቀም ከታኅሣሥ19 እስከ ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት እንድትመዘገቡ ቦርዱ ያሳውቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡-

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ በሚያቋቁማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክልሉን የስራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችሉ
• የሥራ ቆይታ ፦ ለ2 ወር፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ"

(ቱልት /ዉሻ ምላስ ተብሎ ይጠራል)   ከሣር የሚመደብ ዕፅ መጠሪያ ስም ነው  ይህ ዕፅ ለማመን የሚከብዱ ከዘመናዊው ህክምና አቅም በላይ የሆኑ  8  የበሽታ ዓይነቶችን በሚደንቅ ሁኔታ የመፈ...
16/11/2025

(ቱልት /ዉሻ ምላስ ተብሎ ይጠራል)

ከሣር የሚመደብ ዕፅ መጠሪያ ስም ነው ይህ ዕፅ ለማመን የሚከብዱ ከዘመናዊው ህክምና አቅም በላይ የሆኑ 8 የበሽታ ዓይነቶችን በሚደንቅ ሁኔታ የመፈወስ አቅም ያለው ዕፅ ነው።

በማንኛውም ቦታ የሚበቅል ቅጠሉ የውሻ ምላስ የሚመስል ሰፋፊ አገዳው ቀይ የሆነ ከሣር የሚመደብ የሳር አይነት ነው።

የውሻ ምላስ የሚለውን ስያሜ በአማረኛ ቋንቋ ያገኘውም የቅጠሉ ቅርፅ የውሻ ምላስ የሚመስል ቅርፅ ስላለው ነው ይላሉ ።

ቱልት/ የውሻ ምላስ ከሚፈውሳቸው የበሽታ ዓይነቶች መካከል ጥቂቶቹ፦

ለቋቁቻ ወይም ለባርሌ በሽታ ይሆናል። በሽታው ብዙ ጊዜ የአንገት አካባቢን ያጠቃል ለዚህ የበሽታ ዓይነት ቅጠሉን ወቅጦ ትንሽ በእሳት ሞቅ እያደረጉ ለ7 ቀን ቢቀብት ያጠፋል።

ለፊት ማድያት በሽታም ለቆዳችን ከሚስማማ ቅባት ጋር ለውሶ ቢቀቡት ይፈውሳል።

ለቁርጥማት ህመም ፍሬውን ደቁሶ ለ1 ቀን 1የሻይ ማንኪያ ሙሉ በማር ለውሶ መውሰድ በቂ ነው ።ለ10 ቀን ከምግብ በፊት ቢሆን ይመረጣል።

ስሩን ካኘክነው ጊንጥ የምትባለዋ የበረሐዋ ተናካሽ አውሬ ብትነክሰንም አያመንም መርዟን ያከሽፈዋል ማለት ነው።

ለዓይነማዝ ወይም ለማንኛውም የዓይን ህመም ሥሩን ከፍትግ ገብስና ከምስር ገለፈት ጋር ወቅጦ በቅቤ አንጥሮ መቀባት ነው ፈፅሞ ይድናል።

ሆዱን እየነፋው ለሚቸገር ሰው ለሥራይ ወይም ሌላ በሽታ ስሩን ከቀጠጥና ሥር ጋር ወቅጦ በማር ወይም በወተት አፍልቶ ማጠጣት ነው፦መጠኑን በሚመለከት ከሁለቱም ዓይነት ውህድ 1የሻይ ማንኪያ ዱቄት በቂ ነው፡፡

ለሽንት ማጥ በሽታና የከፋ የሐሞት ጠጠርን ለማውጣት ሥሩን በውኃ ቀቅሎ ከወተት ጋር ቀላቅሎ መጠጣት ወይም ከሰመሬታ ገብስ ጠላ ጋር ቀላቅሎ ለ፩ ቀን ፩ የውሃ ብርጭቆ መጠጣት በቂ ነው፦በሽታው ዕስኪድን ድረስ መደጋገም ይቻላል፡፡

ለድክመተ ወሲብ ብቻውን ይሆናል፡፡
አጠቃቀም
ስሩ ተቆርጦ ዕንዳይቀር በአንካሴ ወይም በማንኛውም መቆፈሪያ በጥልቀት ቆፍሮ ማውጣት ተቆፍሮ ከወጣ በኋላ ላም አርጎ ወቅጦ በተወቀጠ ኑግ ለውሶ በገብስ ጠላ
ለ7 ተከታታይ ቀናት በቀን 1ጊዜ 1የውሃ ብርጭቆ መጠጣት በቂ ነው፦ ስሩ ከመሬት ተቆርጦ ከቀረ አይሠራም፡፡

ለሪህ በሽታ ስሩን ወቅጦ በሱፍ ውኃ በጥብጦ አጥልሎ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል በትንሽ በትንሹ እየጨመሩ በቀይ ጤፍ እንጀራ እየፈተፈቱ መብላት ።

በሆድ ውስጥ ላለ ኪንታሮትና በፊንጥጣ ዙሪያ ጎልቶ ላልወጣ ኪንታሮት ፍቱን መፍትሔ ነው።

አጠቃቀም

ቅጠሉን እንደሐበሻ ጎመን በዕርጥቡ ለቅሞ በደንብ አጥቦ ልክ ዕንደጎመን ድቅቅ አርጎ ከትፎ ለአልጫ ጎመን ወጥ የሚገቡትን ግባቶች አስገብተው ከሠሩ በኋላ በጥቁር ጤፍ ዕንጀራ ከምግብ በፊት እየፈተፈቱ መብላት ነው፡፡ አወሳሰዱ ዕንደኪንታሮቱ ጥንካሬ ይለያያል።

መልካም ጤንነት ተመኘዎሎ ዶ/ክ ቤዛ አያሌው

 !!!******=====*****በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ መቆም አድማ  ተጠርተዋል።"ነገ በጠቅላላ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች  የስራ  መቆም  አድማ ...
12/11/2025

!!!
******=====*****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ መቆም አድማ ተጠርተዋል።
"ነገ በጠቅላላ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የስራ መቆም አድማ ተጠርተዋል ።
*****
የአድማውም ምክንያት መንግስት ለሰራተኞች የጨመረውን ደመወዝ ጭመሪ አምባገነኑ እንዳሻው እምቢ በማለቱ የተነሳ ነው በነገው ዕለት መምህራን ፣የጤና ባለሙያዎች ፣የግብርና ባለሙያዎች እና ሁሉም የቢሮ ባለሙያዎች ዝግ በማድረግ አደባባይ ወቶ ድምፅ ልያሳሙ ነው።
*****
ይህንን የሰማው አቶ እንዳሻው የሁሉንም ዞን አሰተዳደሮች ከሰዓት ስብሰባ ጠርተዋል እስኪ ምን እንደመመፈጣር አብረን እናያለን እስከዛ ድምፅ ሁናን"

12/11/2025
10/11/2025

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ይፈፀማል::

10/11/2025

‎በክልሉ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ይፈፀማል:- አቶ ተፈሪ አባተ

‎ኅዳር 1/2018 ዓ.ም

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈፀም የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ።

‎በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እንደሀገር ከመስከረም ወር 2018 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገውን አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

‎አቶ ተፈሪ በሰጡት መግለጫ በክልሉ አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ መክፈል የሚያስችል ሀብት ከኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መተላለፉን አስታውቀዋል።

‎እንደሀገር መንግስት የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን የገለጹት አቶ ተፈሪ፥ ይህንኑ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

‎ቢሮው በክልሉ ሥር የሚገኙ መዋቅሮች አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ለመፈፀም የሚያግዙ መረጃዎችን አጣርተው እንዲያደረሱ ሲጠባበቅ መቆየቱንም ገልጸዋል።

‎በክልሉ ሥር ከሚገኙ 12 ዞኖች እና 3 ሪጂዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በአሁኑ ሰዓት ሁሉም መረጃዎች ተደራጅተው መምጣቱን ያስታወቁት አቶ ተፈሪ፥ የመስከረም እና የጥቅምት ወር አዲሱ ጭማሪ ደመወዝ እንዲከፈል ለባንክ መላኩን ገልጸዋል።

‎በክልሉ ስር የሚገኙ ሁሉም ዞኖችና ሪጂዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ድረስ ገንዘቡን ከባንክ ማግኘት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎በመሆኑም ሁሉም መዋቅሮች የመንግስት ሠራተኞች ውዝፍ ክፍያውን በሁለት ቀናት ውስጥ በመፈፀም ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

‎በክልሉ የልዩ ስኬል ደመወዝ ተከፋዮች የዐቃቤ ህግ ፤ ዳኞች እና ገቢዎች በተመለከተ እና የበረሀ አበል ክፍያ የሚፈፀምባቸው መዋቅሮች በአዲስ መልክ ተሰልቶ የሚደርስ ስለመሆኑ አቶ ተፈሪ አስረድተዋል።

‎ከኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር የተላለፈው ሃብት መዋቅሮች ባላቸዉ የሰዉ ሃይል ስሌት መሠረት የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባስተላለፈው መረጃ መነሻ በማድረግ የተላከ መሆኑን የገለጹት አቶ ተፈሪ፥ ለተፈፃሚነቱ በየደረጃው ያለው አመራር በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመራ አሳስበዋል።

👉የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ

09/11/2025

እኛ የአላህ ነን ወደ እሱም ተመላሾች ነን!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአንጋፋው የታሪክ ምህሩና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል።

ፕሮፌሰር ላጲሶ በህይወት በነበሩበት ዘመን ለሀገራቸው ኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር ትልቅ አበርክቶ የነበራቸው ሲሆን የተለያዩ የታሪክ መፅሀፍቶችን ፅፈው ያሳተሙና በዘርፉ አንቱታን ያገኙ ታላቅ ምሁር ነበሩ።

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሀገረ መንግስት ግንባታ ያደረጉትን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ያበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ታሪክ የማይረሳው ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ ቤተሰቦችና ለመላ ኢትዮጵያን መፅናናትን ይመኛል።

ጥቅምት 30፣ 2018 ዓ.ሒ (ጁማደል አል -አወል 18፣ 1447 ዓ.ሒ )
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት

ሲዳማ ክልል የተስተካከለው አዲሱ ደመወዝ መክፈል እንደማይችል ገለፀ።የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ  ከደቂቃዎች በፊት በተቋሙ ማህበራዊ ገፅ ላይ እንደገለፀው አዲሱ ደመወዝ መክፈል እንደማይችል አስታው...
07/11/2025

ሲዳማ ክልል የተስተካከለው አዲሱ ደመወዝ መክፈል እንደማይችል ገለፀ።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት በተቋሙ ማህበራዊ ገፅ ላይ እንደገለፀው አዲሱ ደመወዝ መክፈል እንደማይችል አስታውቋል።

የጥቅምት ወር የሰራተኞች ደሞዝ በቀድሞ ደመወዝ እንደሚከፈል የገለፀ ሲሆን በየመስሪያ ቤቱ በአረገው ደመወዝ ሰርቶ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አዲሱን የደሞዝ ማሻሽያ ምክንያት በማድረግ ህገወጥ 13,000 ሺ ሠራተኛች የመደብ መታወቂያ ጥቁር የሌላቸውን ዝርዝር መረጃ ዉስጥ በማጨቅ አጠቃላይ 125,000 ሺ ሠራተኛች ደመወዝ መጠየቁን ተገልጿል።

የክልሉ ፓብልክ ሰርቪስ በኩል የተላከው መረጃ እና የፈደራሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሚያቀው የሰው ኃይል ቁጥር 112ሺ ጋር ስነጻጸር የ13ሺ መነሻዉ ያልታወቀ ሰዉ ሃይል ተገኝቷል ነዉ የተባለው።

በሌላ በኩል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዓመታዊ የሰራተኞች የደመወዝ ወጪ 4.6 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል።

ከተማዋ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ አሰባሰብና አፈጻጸም መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ 4.8 ቢሊየን ብር በመሆኑ፤ ቀሪው ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር የልማት ሥራዎችን ለማከናወን አስቸጋር ያደርገዋል ተብሏል።

መንግሥት የዘጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉና የደመወዝ ጭማሪውም ከጥቅምት ወር ደመወዝ ጋር ተካቶ እንደሚከፈል ማወጁ ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎ የክልል መንግሥታት በፋይናንስ ልማት ቢሮና በፓብልክ ሰርቪስ ቢሮ አማካይነት መረጃ እንድቀርብ መታዘዙም ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎ በክልሉ ፓብልክ ሰርቪስ ቢሮ አማካይነት የ112ሺ ሠራተኛች ዝርዝር መረጃ የተላከ ስሆን፤ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በኩል ደግሞ 125ሺ ሠራተኞች ደመወዝ መጠየቁ ታውቋል::

ይህንን ልዩነት ለማስተካከል የክልሉ ፋይናንስ የላከዉ መረጃ በደንብ እንዲፈተሽ ጠቅላይ ምንስተሩ አቅጣጫ አስቀምጧል ተብሏል።

''ለአዲሱ ደመወዝ ክፍያ እስከ ሁለት ሳምንት በትዕግሥት ጠብቁኝ ''የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ  ከፌዴራል የተላለፈው እና በክልሉ ደረጃ ያለው መረጃ ባለመጣጣሙ በተፈጠረው ክፍተት እስከአሁን...
07/11/2025

''ለአዲሱ ደመወዝ ክፍያ እስከ ሁለት ሳምንት በትዕግሥት ጠብቁኝ ''

የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ

ከፌዴራል የተላለፈው እና በክልሉ ደረጃ ያለው መረጃ ባለመጣጣሙ በተፈጠረው ክፍተት እስከአሁን አዲሱን የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ መክፈል አልቻልኩም ያለው የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ እስከ ሁለት ሳምንት የተፈጠረውን ክፍተት አስተካክዬ እስከምከፍል በትዕግሥት ጠብቁኝ በማለት በቢሮ ይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ በኩል ትህትና በተሞላው አገላለጽ ጠይቋል ።

በክልሎች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት ያጋጠመው ኮሚሽኑ በፈጠረው የቀመር ሥሌት አረዳድ ችግር ነው ተባለ‼️በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በማዕከ...
05/11/2025

በክልሎች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት ያጋጠመው ኮሚሽኑ በፈጠረው የቀመር ሥሌት አረዳድ ችግር ነው ተባለ‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ያጋጠመው የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በሠራው የቀመር ሥሌት ላይ በተፈጠረ የአረዳድ ችግር ምክንያት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መምርያ ኃላፊ አቶ ፍሬው ኃይሌ፣ አምስቱ ክልሎች የበጀት ጉድለት እንዳጋጠማቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኃላፊዎችና የክልሎቹ ተወካዮች በተገኙበት በተደረገ ውይይት፣ ችግሩ የተፈጠረው ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሠራው የደመወዝ ጭማሪ ወይም ማስተካከያ ቀመር ሥሌትን በአግባቡ ካለመረዳት በመነጨ
ምክንያት እንጂ፣ ባጋጠመ የበጀት እጥረት ወይም በሌላ ምክንያት አለመሆኑንና መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

በውይይቱም ክልሎች በአማካይ፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደግሞ በእርከን ሒሳቡን መሥራታቸውን መናገራቸውን ያወሱት ኃላፊው፣ በዚህም ሒሳብ የሠሩበት መንገድ አንድ ዓይነት እንዳልሆነ መተማመናቸውንም ጭምር ጠቅሰው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ኮሚሽኑ ባቀረበው ሥሌት መሠረት የበጀት ምደባ ማድረጉን ገልጸዋል።

ጉዳዩን በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ‹‹የበጀት ጉድለት ያጋጠመባቸው ክልሎች ደመወዛቸው 4,6ዐዐ ብር የነበሩ ሠራተኞች በቀጥታ 6,9ዐዐ ብር ይሆንላቸዋል›› ተብሎ በሰው ቁጥር እንደተባዛ ጠቁመው፣ ይህ ግን መሀል ላይ ያሉትን ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ደረጃዎች ወይም እርከኖች መሠረት ያደረገ አይደለም ብለዋል፡፡ ሆኖም በእርከኑ መሠረት የተሠራው ሒሳብና የሠራተኛው ቁጥር አንድ እንደሚሆን አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል፡፡

ሦስት ሚሊዮን ብር፣ አሥር ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም እስከ አሥር ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አጋጥሞናል ብለው ጥያቄ ያቀረቡ ክልሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ሆኖም ሲቪል ሰርቪስ የሰጠው ምላሽ የአንድ ወይም የሁለት ሚሊዮን ብር የበጀት ልዩነት ሊፈጠር ይችላል እንጂ ይኼን ያህል አይሆንም የሚል መሆኑን፣ ይህም ከሆነ ደግሞ ክልሎች በራሳቸው ገቢ መሙላት የሚችሉ መሆኑን እንደተነገራቸው አስታውሰዋል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቀመሩን የሠራው እስከ 2016 ዓ.ም. ሰኔ ወር ባለው የመንግሥት ሠራተኛ ቁጥር መሠረት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ከዚያ በኋላ ቅጥር የፈጸሙ ክልሎች ላይ የሠራተኛ ቁጥር ልዩነት መምጣቱንና ይህንንም በጥያቄ መልክ ቀርቦ ነበር ብለዋል፡፡ ነገር ግን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቅጥር በማድረጉ ለእነዚህ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ከፌዴራል መንግሥት ሊደለድል እንደማይችል፣ ራሳቸው ክልሎች ኃላፊነቱን እንዲወስዱ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።

ለ12 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሚለቀቀው በጀት በየሦስት ወራት ለሦስት ጊዜያት ያህል ተከፋፍሎ ከግምጃ ቤት እንዲደርሳቸው እንደሚደረግ፣ በዚህም የመጀመሪያው ሦስት ወራት ማለትም የመስከረም፣ የጥቅምትና የኅዳር ወራት ደመወዝ መሠራጨት መጀመሩን ጠቁመዋል።
በኅዳር አጋማሽ፣ የታኅሳስ፣ የጥርና እንዲሁም የየካቲት፣ በየካቲት አጋማሽ ደግሞ፣ የመጋቢት፣ የሚያዝያ፣የግንቦትና የሰኔ ወራት እንደሚለቀቅ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ሪፖርተር ጋዜጣ

Address

Addis Abeba

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amharic News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share