Adet Town Communication

Adet Town Communication የአዴት ከተማ ወቅታዊ፣ ተዓማኒና ሚዛናዊ የመረጃ ምንጭዎ!

አዴት ከተማ ገበያ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ሳምንታዊ የግብይት መረጃ ሚያዚያ 24/2018 ዓም/አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን
04/05/2026

አዴት ከተማ ገበያ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ሳምንታዊ የግብይት መረጃ ሚያዚያ 24/2018 ዓም/አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን

አዴት ከተማ ገበያ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ሳምንታዊ የግብይት መረጃ ሚያዚያ 20/2018 ዓም/አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን
28/04/2026

አዴት ከተማ ገበያ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ሳምንታዊ የግብይት መረጃ ሚያዚያ 20/2018 ዓም/አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን

ፋይዳ (ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከማስቀረት አኳያ  ያለዉ ሚና፦የፋይዳ (ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) ሥርዓት ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የሚጫወተው ሚና ...
24/04/2026

ፋይዳ (ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከማስቀረት አኳያ ያለዉ ሚና፦

የፋይዳ (ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) ሥርዓት ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው። ይህ ሥርዓት በዋናነት ግልጽነትን በመፍጠርና ተጠያቂነትን በማስፈን ላይ የተመሰረተ ነዉ።

ሙስና በብዛት የሚፈጸመው የሐሰት ማንነትን በመጠቀም ነው። ፋይዳ መታወቂያ በባዮሜትሪክስ (የጣት አሻራ እና የዓይን ብሌን) ላይ የተመሰረተ በመሆኑ አንድ ሰው ከአንድ በላይ መታወቂያ ሊኖረው ስለማይችል ሕገ-ወጥ ጥቅማጥቅሞችን ለማስቀረት ይረዳል ማለት ነዉ።

አገልግሎቶች ከሰው ንክኪ ነፃ ሆነው በዲጂታል መንገድ እንዲሰጡ በማድረግ ለሙስና የሚጋብዙ አጋጣሚዎችን ይቀንሳል። አገልግሎት ፈላጊውና ሰጪው አካል ለፊት ለፊት ንክኪ ሳይጋለጡ በዲጂታል መታወቂያው አማካኝነት ጉዳያቸውን እንዲጨርሱ ያደርጋል። የተጭበረበሩ ሰነዶችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የንብረትና የፋይናንስ ስርቆቶችንም ይከላከላል ማለት ነዉ።

ከፍተኛ የሙስና ወንጀሎች የሚፈጸሙት በባንክና በፋይናንስ ተቋማት በኩል ነው። ፋይዳ ከመደበኛው የባንክ ሥርዓት ጋር ሲቀናጅ ግን ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን (Money Laundering) ለመከታተል ቀላል ይሆናል። ሌላዉ የሀብት ምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓትን በማጠናከር፣ ግለሰቦች ካላቸው ገቢ በላይ ያካበቱትን ሀብት በቀላሉ ለመለየት ያስችላል።

የመንግሥት ድጎማዎችና ድጋፎች (ለምሳሌ፦ ማዳበሪያ፣ ሴፍቲኔት፣ የጤና መድን) ለታለመላቸው ትክክለኛ ሰዎች መድረሳቸውን ያረጋግጣል። በመሃል የሚገቡ ደላሎችንና ጥቅማጥቅም የሚያባክኑ አካላትን ድርጊት ይገታል ማለት ነዉ።

ማንኛውም የዲጂታል እንቅስቃሴ ከግለሰቡ ልዩ መለያ (Unique ID) ጋር የተያያዘ ስለሚሆን አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ወይም አመራር ውሳኔ ሲያስተላልፍ በስሙና በማንነቱ በሲስተሙ ውስጥ ስለሚመዘገብ ለሰራው ስህተት ወይም ለፈጸመው ብልሹ አሰራር ተጠያቂ ለማድረግ የኦዲት ፈርጅ (Audit Trail) ይፈጥራል።

በአጠቃላይ የፋይዳ መታወቂያ ሥርዓት የሰው ተኮር አሰራርን ወደ ሥርዓት ተኮር በመቀየር፣ ለሌቦችና ለሙስና አራማጆች የሚመቹ ቀዳዳዎችን በቴክኖሎጂ ይደፍናል ማለት ነዉ።

የመንግሥት ሠራተኞች ሪፎርም፦ ቅነሳ ወይስ የአቅም ግንባታ?​በአሁኑ ወቅት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እየተተገበረ ያለው ሪፎርም "ሠራተኛን ለመቀነስ የታለመ ነው" በሚል የሚነሳው ሃሳብ መሠረተ...
23/04/2026

የመንግሥት ሠራተኞች ሪፎርም፦ ቅነሳ ወይስ የአቅም ግንባታ?
​በአሁኑ ወቅት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እየተተገበረ ያለው ሪፎርም "ሠራተኛን ለመቀነስ የታለመ ነው" በሚል የሚነሳው ሃሳብ መሠረተ ቢስ መሆኑን የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

​የሪፎርሙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
​ዓላማው፦ የሠራተኛውን የማስፈጸም አቅም (ዕውቀት፣ ክህሎትና ሥነ-ምግባር) ማሳደግ እና አሠራርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የተገልጋይን እርካታ ማረጋገጥ ነው።
​የምዘና ፋይዳ፦ ምዘና የሚደረገው የሠራተኛውን ክፍተቶች ለይቶ ለማሰልጠን እንጂ ከሥራ ለማሰናበት አይደለም። ብቁ ያልሆኑ ሠራተኞች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በሚሰጥ ሥልጠና ብቁ እንዲሆኑ ይደረጋል።
​ዲጂታላይዜሽን፦ አገልግሎቶችን ከወረቀት ንክኪ በማላቀቅ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል።
​"ሪፎርሙ ሠራተኛውን አምራች እና ብቁ የማድረግ ሥራ ነው፤ በአሉባልታ ከመወዛገብ ይልቅ ትክክለኛ መረጃዎችን ከመመሪያዎችና ከደነዶች መረዳት ይገባል።"
— አቶ እንዳላማው ይታይህ (የሪፎርም ድጋፍና ክትትል ዳይሬክተር)

​ባጭሩ፦ የማሻሻያ ሥራው ግቡ ሠራተኛ መቀነስ ሳይሆን የሥራ ምርታማነትን ማሳደግ እና ፍትሃዊ የአገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ነው።

በአዴት ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የክለቦች የእግር ኳስ ሻምፒዮን ውድድር በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል​አዴት | ሚያዝያ 12 2018 ዓ.ም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን) የአዴት ከተማን የስፖር...
20/04/2026

በአዴት ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የክለቦች የእግር ኳስ ሻምፒዮን ውድድር በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል

አዴት | ሚያዝያ 12 2018 ዓ.ም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን) የአዴት ከተማን የስፖርት ትኩሳት ከፍ የሚያደርግና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአዴት ከተማ የክለቦች "ሲቲ ካፕ" ውድድር በይፋ መጀመሩን የከተማው አስተዳደር ስፖርት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

​ይህ ውድድር በከተማዋ ታሪክ ለተጫዋቾችና ለስፖርት አፍቃሪያን አዲስ ተስፋን ሰንቆ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ደማቅ መድረክ ሆኗል።

​የዘንድሮው የከተማ ዋንጫ በከተማዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 8 ክለቦችን ያሳተፈ ሲሆን፣ ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ይካሄዳል። እያንዳንዱ ክለብ ለክብርና ለዋንጫው የሚያደርገው ፍልሚያ ለከተማዋ ወጣቶች ብቃታቸውን የሚያሳዩበት ወርቃማ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

​የአዴት ከተማ አስተዳደር ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማስተዋል አዳሙ ውድድሩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ምንም እንኳ ጽ/ቤቱ የበጀት እጥረት ቢኖርበትም ያለንን ውስን አቅም በመጠቀም የስፖርቱን ዘርፍ ለማነቃቃት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ይህንን ውድድር እውን አድርገናል በለዋል። ዓላማችን የስፖርት ቤተሰቡን ማነቃቃትና የወጣቶችን የስፖርት ተሳትፎ ማሳደግ ነው" ብለዋል።

​ውድድሩ መጀመሩ በከተማዋ ስፖርተኞች ዘንድ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል። ለረጅም ጊዜ እንዲህ ዓይነት መድረክ ሲናፍቁ የነበሩ ተጫዋቾች፣ ውድድሩ መጀመሩ ታላቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

​በሜዳው ተገኝተው ጨዋታውን የታደሙ የከተማዋ ነዋሪዎችም፣ ይህ ውድድር በአዴት ከተማ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ላይ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል የሚል ከፍተኛ ተስፋ አድሮባቸዋል።

​ይህ ውድድር እስከ ግንቦት መጨረሻ በከተማው ስታዲየም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ሜዳ በመምጣት ቡድኖቻቸውን እንዲያበረታቱ ጥሪ ቀርቧል።

ምን ያህል መራጮች ተመዘገቡ?የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚያከናውነው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስከ ሚያዚያ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. ያለው የመራጮች ምዝገባ አኅዛዊ መረጃ።አሚኮ
18/04/2026

ምን ያህል መራጮች ተመዘገቡ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚያከናውነው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስከ ሚያዚያ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. ያለው የመራጮች ምዝገባ አኅዛዊ መረጃ።

አሚኮ

አዴት ከተማ ገበያ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ሳምንታዊ የግብይት መረጃ ሚያዚያ 08/2018 ዓም/አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን/
17/04/2026

አዴት ከተማ ገበያ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ሳምንታዊ የግብይት መረጃ ሚያዚያ 08/2018 ዓም/አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን/

የአዴት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለከተማው ነዋሪዎች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ​ክቡራን የአዴት ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፤​በመጀመሪያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እ...
10/04/2026

የአዴት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለከተማው ነዋሪዎች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

​ክቡራን የአዴት ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፤
​በመጀመሪያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።
​የትንሳኤ በዓል የድል፣ የሰላም እና የብርሃን ተምሳሌት ነው። ሞት በህይወት፣ ጨለማ በብርሃን የተሸነፈበት ይህ ታላቅ ዕለት፤ እኛም እንደ ህዝብ በአንድነት ቆመን ካለፈው ተምረን ወደ ተሻለ ብሩህ ምዕራፍ የምንሻገርበት ተስፋችን ነው።

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች፤
​አዴት ከተማችን በተፈጥሮ የታደለች፣ ለራሷ ተርፋ ለሌሎች የምትሆን የትረፈረፈ የሰብል ምርትና የእንስሳት ሀብት ማዕከል መገኛ ናት። ገበያችን ከራሳችን አልፎ የተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎችን የሚመግብ የብልጽግና ተምሳሌት ሆኖ መቆየቱ የታወቀ ነው። ይህ በረከት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ከተማችን የንግድና የግብርና ኮሪደር ሆና እንድታድግ የሁላችንም ሰላም እና ትጋት ወሳኝ ነው።

​የትንሳኤ በዓል ምንነት መስዋዕትነት ነው። ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ ሁሉ፣ እኛም በዓሉን ስናከብር ያለው የሌለውን በማሰብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና በመተጋገዝ ሊሆን ይገባል። እውነተኛው የበዓል ደስታ የሚገኘው በጋራ ስንበላና የተራቡትን ስናጠግብ በመሆኑ፣ ይህን የታላቅነት እሴታችንን እንድናሳድግ አሳስባለሁ።

​በተጨማሪም፣ በዓላትን ስናከብር ከአቅም በላይ ለሆኑ አላስፈላጊ ወጪዎች ራሳችንን ባለማጋለጥ፣ ቁጠባን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲሆን ይመከራል። ያለንን በቁጠባና በሥርዓት በመጠቀም ለነገው ህይወታችንና ለከተማችን ልማት የሚሆን አቅም መገንባት ይኖርብናል።

በመጨረሻም፤
​ለከተማችን ሰላም፣ ለነዋሪዎቻችን ደህንነትና ለሁለንተናዊ ዕድገታችን በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ። ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነውና፣ አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅና ለልማት ስራዎች እጅና ጓንት በመሆን የአዴት ከተማን ብልጽግና እናረጋግጥ።

​በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የጤና እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ!

መልካም የትንሳኤ በዓል!
​የአዴት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ማንችሎት ባለው

የአዴት ከተማ የማዕድን ምርቶች የግብይት መረጃ ሚያዚያ 01/2018 ዓም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን)
09/04/2026

የአዴት ከተማ የማዕድን ምርቶች የግብይት መረጃ ሚያዚያ 01/2018 ዓም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን)

በአዴት ዘመናዊ የከብት ገበያ ማዕከል የፋሲካ በዓል የእርድ እንስሳት ግብይት በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ ​አዴት | መጋቢት 30/2018 ዓም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን)— የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል...
08/04/2026

በአዴት ዘመናዊ የከብት ገበያ ማዕከል የፋሲካ በዓል የእርድ እንስሳት ግብይት በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ

​አዴት | መጋቢት 30/2018 ዓም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን)— የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዴት ዘመናዊ የከብት ገበያ ማዕከል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የእርድ እንስሳት ግብይት ሲከናወን ውሏል። በሀገሪቱ ካሉ የእንስሳት መገበያያ ስፍራዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የአዴት ገበያ፣ ዘንድሮም ለበዓሉ የሚሆኑ በርካታ እንስሳትን አስተናግዷል።

​እንደ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት መረጃ ከሆነ፣ ለዘንድሮው የፋሲካ በዓል ከ160 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳት ወደ ገበያ የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ የግብይት ፍሰት የታየበትና በሰላማዊ መንገድ የተጠናቀቀ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘላለም አዲስ ገልጿል።

​በገበያ ማዕከሉ የታየው የእንስሳት ዋጋ እንደየደረጃቸውና እንደ መጠናቸው ልዩነት የታየበት ሲሆን፣ አማካይ የዋጋ ተመኑም የደለበ በሬ ከ70 ሺህ እስከ 350 ሺ በግ ከ8 ሺህ እስከ 25 ሺህ ፍየል ከ10 ሺህ እስከ 30 ሺህ ብር ሲገበያይ ውሏል።

የዘንድሮው የፋሲካ ገበያ ካለፉት ዓመታት በተሻለ የእንስሳት አቅርቦት የታየበት ሲሆን፣ የግብይት ስርዓቱም ምንም አይነት የጸጥታ ችግር ሳያጋጥመው በሰላም ተጠናቅቋል።

​የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አክለውም፣ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ የተቸገሩትን በመርዳት፣ በሰላም፣ በፍቅርና በመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል

የአዴት ከተማ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲጠባበቁት የነበረው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ አገኘ ​መጋቢት 29/2018 ዓም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን) በሰሜን ጎጃም ዞን አዴት ከተማ አስተዳደር ለረጅም...
07/04/2026

የአዴት ከተማ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲጠባበቁት የነበረው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ አገኘ

​መጋቢት 29/2018 ዓም (አዴት ከተማ ኮሙኒኬሽን) በሰሜን ጎጃም ዞን አዴት ከተማ አስተዳደር ለረጅም ዓመታት ዋነኛ የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየው የመኖሪያ ቤት ችግር ምላሽ አግኝቷል። የከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ዛሬ ባካሄደው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት፣ የቤት ፈላጊ ማህበራት የቦታ ድልድል የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በይፋ ተከናውኗል።

​በዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ማንችሎት ባለው፣ ወቅቱ ፈታኝ ቢሆንም የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል። ከንቲባው አክለውም "ይህንን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ከአመራር እስከ ባለሙያ፣ እንዲሁም የጸጥታ መዋቅሩ ሌት ከቀን በቅንጅት ሲሰሩ መቆየቱን ገልፀዋል። በዕለቱ ከ1 ሺህ 800 በላይ ለሚሆኑ ቤት ፈላጊዎች የቦታ ርክክብ ለማድረግ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማካሄድ መቻሉንም ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።

​የከተማና መሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው፣ ቦታውን አዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በሂደቱ ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶችና ውጣ ውረዶች ማለፋቸውን አስታውሰዋል። ሆኖም በአመራሩና በባለሙያው መካከል በነበረው ጠንካራ መናበብ ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል። በዚህም ለ84 የመኖሪያ ቤት ማህበራት እና ከ7 መቶ 60 በላይ ባለይዞታዎችና ልጆቻቸው የቦታ ጥያቄያቸው ምላሽ ማግኘቱን አረጋግጠዋል።

​የከተማ አስተዳደሩ የፕላን ባለሙያ አቶ ባያቸው አይቸህ ስለ ቦታው አደረጃጀት ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የተዘጋጀው የመኖሪያ ቤት ቦታ በ4 ዋና ዋና ሳይቶች የተከፈለ ሲሆን፣ በውስጡ 1 መቶ 67 ብሎኮችን የያዘና በአጠቃላይ ለ1 ሺህ 8 መቶ 20 ተጠቃሚዎች የሚሆን የፓርስል/ክፍልፋይ መሬት የተዘጋጀለት ነው ብለዋል።

ይህ የቦታ ድልድል መከናወን በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት በከፍተኛ ደረጃ የሚቀርፍና ለከተማዋ እድገት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።

Address

Adet

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adet Town Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share