
17/04/2025
ከዲላ ማረሚያ ተቋም 200 የሕግ ታራሚዎች በክልሉ መንግስት ይቅርታ ተለቋል
#ዲላ ፤ ሚያዝያ 9/2017
የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ተከትሎ ከዲላ ማረሚያ ተቋም 200 ታራሚዎች መለቀቃቸውን የዲላ ማረማ ተቋም አስታውቋል ።
ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ሽብሩ የዲላ ማረሚያ ተቋም ተወካይ እንደገለጹት የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የደቡብ ኢትዮጵያ የክልሉ መንግስት የይቅርታ ማድረጉን ተከትሎ ከዲላ ማረሚያ 200 ታራሚዎች የይቅርታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጿል ።
ይቅርታ ያገኙ ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት በቆዩበት ወቅት ጥሩ ስነ ምግባር ያሳዩና በሕግ አግባብ የይቅርታ መስፈርትን የሟሉ ታራምሆች በማረሚያም ተቋሙ ስለመታረማቸውና ስለመታነፃቸው ተረጋግጦ መፈታታቸውን ተናግሯል።
ከተለቀቁ ከ200 ከህግ ታራሚዎች መካከል 12ቱ ሴቶች መሆናቸውን ከጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው ዘገባ ያመላክታል።