
09/08/2025
ድንቅ ተግባር የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና የስልጤ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ 👏👏!!
ትላንት ለሊት 8:00 ሰዓት ገደማ ሹፌሩን እና ረዳቱን በማገት ሳንኩራ ረግዲና ቀበሌ ላይ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-ET/ኢት A-18706 የሆነ ሲኖ ትራክ ( ካሶኒ ) መኪና🚛 ከእነ ጭነቱ በሌቦች/በሽፍቶች ተሰርቆ የነበረ ሲሆን
በዛሬው እለት በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ በሻሸመኔ ከተማ የተገኘ ሲሆን ለዚህም የመልካ ሲርባ ክፍለ ከተማ የፖሊስ፣ የሃላባ ዞን፣ የሃላባ ቁሊቶ ከተማ ፣ የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ፣የስልጤ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ፣የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ሊገኝ ችሏል ።
ሁሉንም የፀጥታ አካላት ላደረጉት ድንቅ ተጋድሎና ርብርብ ከልብ ሊመሰገኑ ይገባል👏👏