28/07/2023
2% የመኖር እድል!😥
አለም በመገረም ሚያስታውሰው ፈገግታ
________________________________________________
ጄን ማርክዚውስኪ (Night bird) American got talent በተባለው በዓለም ታዋቂ ውድድር የቀረበችበት ቪድዮ ለስርጭት ከበቃበት August 21/2021 ጀምሮ ባየሁት ቁጥር እምባ ይቀደመኛል፤ የመደመምና የመደነቅ ነው የማለቅሰው፤ በእርግጥ አዝኜላትም አለቅሳለሁ። በዋነኝነት ግን ጽናቷ፣ የእምነት ጥንካሬዋ፣ ተስፋዋ . . . ይደንቀኝና ሳላስበው እምባዬ ይወርዳል።
የሰው ልጅ እንዴት ይህን ያህል ይጸናል? "ከእንግዲህ የመኖር እድልህ 2% ነው" ሲባል ሁለት በመቶማ ዜሮ ማለት አይደለም - It is OK? ለማለት ምን ያህል የውስጥ ጥንካሬ ይጠይቃል?
የሆነው ሆኖ ከትናንት በስቲያ የከፋኝ ጊዜ ያቺን የመጀመሪያ የመድረክ ቪድዮዋ ዳግም YouTube ከፍቼ አየኋት - እንባዬ እየወረደ። እናም ያቺን ቅጽበት ላስቃኛችሁ ወደድኩት - እንደሚከተለው . . . ጄን ማርክዚውስኪ (Night bird)
~ የጽናት ተምሳሌት ~
(ዳኞች ተሰይመው አይኖቻቸው ወደመግቢያ በር እያማተሩ ተረኛ ተወዳዳሪ ይጠብቃሉ።
አንዲት ቀጠን ያለች መልከ መልካም ወጣት ወደመወዳደሪያ መድረኩ አመራች። ሉጫ ፀጉሯ ግንባሯ ላይ ተደፍቷል፤ ጂንስ ሱሪ በጥቁር ቲሸርት ለብሳለች። ፊቷ ላይ በሚያበራው ፈገግታ ደስተኛ ትመስላለች። )
💃 እንደቆመች - Hi, አለቻቸው
🕴ከዳኞቹ መካከል ሃዊ ማንደል/Howie Mandel 'Hi, How are you? ' አላት።
💃 I am awesome, I am happy to be here ብላ መለሰች
🕴 'ደስተኛ በመሆንሽ እኛም ደስተኛ ነን። ስምሽ ማነው? ' የሚል ጥያቄ አስከተለላት።
💃 "ጄን ማርክዚውስኪ እባላለሁ። ስዘፍን ግን የሌሊት ወፍ (Night bird) ልትሉኝ ትችላላችሁ" ብላ መለሰች።
🚶ሲሞን ጣልቃ ገብቶ 'በጣም ጥሩ፣ የሌሊት ወፍ?' ከማለቱ
🕴 ዳኛ ማንደል "ለመኖር ነው የምትዘፍኚው?" በማለት አከለ።
😁 ፈገግታዋ እየፈካ "አይ አሁን እንኳን አይደለም" ብላ ስትመልስ ሁሉም ዳኞች ስለማንነቷ ለማወቅ እንደጓጉ ቢያስታውቅባቸውም ለዓለም ህዝብ የጽናት፣ የስነ ልቦናና የአካል አሸናፊነት ተምሳሌትና ሀውልት ሆኖ ለዘላለም የምትኖር ወጣት ከፊታቸው መቆሟን ግን አላወቁም ነበር።
🕴 አሁንም ሲሞን ከየት ነው የመጣሽው? ሲል ጠየቃት፤ ከኦህዮ መምጣቷን ስትናገር ይበልጥ ትኩረቱን የሳበችው ማንደል "እሺ እድሜሽስ ስንት ነው?" በማለት ጠየቃት።
💃 ማርክዚውስኪ እድሜዬዬ 30 ነው" አለች።
🕴(ማንደል ቀጠለ) "እናም በ30 ዓመትሽ ህልምሽ ዘፋኝ መሆን ነው? እሺ ዛሬ ምንድነው የምትዘፍኝልን" በማለት ጥያቄ አስከተለ።
💃 "የምዘፍነው የራሴን ዘፈን ነው። ርዕሱ Its_ok_its_alright ይላል" አለች።
🕴(እንደመደንገጥ ብሎ) 'Its_ok?
💃 አዎ 'Its_ok'
🕴 አሁንም ማንደል ቀጠለ 'Its_ok ምንድነው መልእክቱ?" ሲል ጠየቃት።
😁 ጄን ማርክዚውስኪ ፈገግታዋና በራስ መተማመንዋ እየጨመረ "Its ok ያለፈው አንድ ዓመት የራሴ ታሪክ የሚገልጽ ነው" ከማለቷ
🕴(በዚህች ልጅ ጀርባ ያለው አስደናቂ የታሪክ ቋጠሮ ተሎ እንዲፈታለት የጓጓው ማንደል) " It is ok. እዚህ ከፊታችን የቆምሽው አንቺ ማነሽ?" በማለት ጥያቄ አቀረበላት።
💃 'እኔ በራሴ እዚህ የቆምኩ ነኝ/I am her by myself.'
🕴 ማንደል It is OK የሚለው ርዕስ በጣም መስጦታል። አሁንም 'It is OK, በምን ሥራ ነው ምትተዳደሪው?' በማለት ጠየቃት።
💃 ማርክዚውስኪ ምላሿን ቀጠለች "ላለፉት ጥቂት ዓመታት ምንም ሥራ አልሰራም፤ በካንሰር ተይዤ ለመኖር እየታገልኩኝ ነው"
🕴ማንደል ባነሳው ጥያቄ ተፀፀተ፤ በካንሰር ተይዛ ለመኖር የምትታገልን ወጣት ስለመተዳደሪያ ሥራ በመጠየቁ ራሱን ለመውቀስ አንገቱን ደፍቶ "ኦው በጣም አዝናለሁ" አለ።
😁 ማርክዚውስኪ ግን እሱን ለማጽናናት ይበልጥ ደስተኛ መስላ እየሳቀች 'ምንም ችግር የለም፣ It is OK፣ እኔ በጣም ደህና ነኝ' አለችው።
🚶ሲሞን አሁንም "እኔ ልጠይቅሽ እችላለሁ? አሁን እንዴት ነሽ?" ሲል ጠየቃት።
💃 በቅርቡ ታይቼ ነበር፣ ሳምባዬና የጀርባ አጥንቴ በካንሰር እንደተጎዳ ተነግሮኛል፤ በአጠቃላይ የመኖር እድሌ ከ2% እንደማይበልጥ ሀኪሞች አረጋግጠውልኛል።"
🚶 ሲሞን በሰማው ነገር በጣም ደንግጦና አዝኖ "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነው?"
💃 አይ በጣም ደህና ነኝ፣ በየትኛውም መንገድ ደህና ነኝ" ብላ ስትመልስ
🕴"የውብ ፈገግታሽ፣ የሚያበራ ፊትሽና የደስታሽ ምንጭ አሁን ማንም ማወቅ አይችልም" አለ ማንደል።
💃 ማንም ቢሆን እኔ የደረሰብኝን ያህል ተደራራቢ ከባድ ችግር ሊደርስበት አይችልም። ነገር ግን ምንም ቢደርስበት የውስጥ ጥንካሬና ጽናት አስፈላጊ ነው"
🙉 ከረጅም ቃለ ምልልስ በኋላ ሁሉም ደኞች በተቀላቀለ አድናቆትና ሀዘኔታ ተመስጠው ይታያሉ።
🕴 ማንደል "በጣም ጥሩ፣ እሺ አሁን ያዘጋጀሽውን ሙዚቃ አቅርቢልን" በማለት ጋበዛት።
በሚስረቀረቅ መረዋ ድምጽ:-
"I moved to California in the summer time
I changed my name thinking that it would change my mind
I thought that all my problems they would stay behind
I was a stick of dynamite and it was just a matter of time, yeah
Oh dang, oh my, now I can't hide
Said I knew myself but I guess I lied
It's okay, it's okay, it's okay, it's okay
If you're lost, we're all a little lost and it's alright
It's okay, . . . " አስተጋባች። ዳኞችና አዳራሹን የሞላው ህዝብ በጸጥታ፣ በአግራሞት፣ በመደነቅ፣ በመመሰጥ ስሜት ፀጥታን ቢያነግስም ብዙዎች እንባቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ነበር። . . .
ስትጭርስ በጸጥታ ድባብ ሰው አልባ መሰሎ የነበረው አዳራሽ በጭብጭባ ተናጋ። ታዳሚውና ዳኞች ለክብሯ ከመቀመጫቸው ተነስተው ረጅም ጭብጨባ . . . ።
እጅግ የላቀ ተሰጥኦ ላላቸው ተወዳዳሪዎች የሚሰጠው የgolden buzzer ደወል የውድድሩ ባለቤትና ዳኛ ሲሞን ኮውል ተጫነ። አዳራሹ በእልልታና ፌሽታ ተናወጠ። . . .
ይህ ትዕይንት የተቀረጸበት ቪዲዮ በYouTube ከተጫነ ወደአንድ ዓመት ሆነው። እስከአሁን ከ60 ሚሊዮን በላይ የዓለም ህዝብ ተመልክቶታል።
ከዛች ቅጽበት ወዲህ CNN, CNBC እና BBCን ጨምሮ ይህቺ የዘመኑ አብሪ ኮኮብ የሆነች ወጣት የሚዲያዎች አጀንዳ ለመሆን በቅታ ነበር። ከዚህ መደረክ በኋላ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደገለጸችውም ሀኪሞች "ከዚህ በኋላ የመኖር እድልሽ ከ2% አይበልጥም" ካሏት ወዲህ በውስጣዊ ጽናትና ጥንካሬዋ ጥቂት ዓመታትን ኖራለች። ሁልጊዜ ስለ መኖር እንጂ ስለበሽታዋና ስለመሞት አታስብም። በዚህ ላይ የካንሰር ህመምተኛ በመሆኗ ባለቤቷም ጥሏት ሄዶ ነበር።
በየአጋጣሚው "2% ማለት ዜሮ ፐርሰንት ማለት አይደለም ትላለች፤ የያዘኝ በሽታ ከእኔ አይበልጥም። በፍፁም ነገን አጨልሜ መመልከት አልፈልግም። ተስፋ ሳልቆርጥ ህይወትን መኖር ነው የምፈልገው። ተስፋ ተቆርጦ መኖር ህይወትም አይደለም። የአቅምን እየሞከሩ ችግሮች ቢኖሩም It's ok, it's alright እያሉ መኖር ይገባል" ትል ነበር።
ጄን ማርክዚውስኪ (Nightbird) ለአጭር ጊዜ ብቅ ብላ February 19, 2022 ከዚህ ዓለም ከመለየቷ ቀደም ብሎ ለፈረንጆች 2022 ዘመን መለወጫ CNN ላይ ቀርባ ነበር። ጋዜጠኛው በመደነቅ እስኪደመም ድረስ የደስታና የመኖር ተስፋ፣ የጽናትና በራስ የመተማመን ጣራ ላይ ሆና ማንም ሰው የመኖር እድሉ ተጠናቅቋል ቢባል እንኳን ያቺን ቅጽበት ከውስጥ በሚፈነቅል ፈገግታ ሊያሳልፋት እንደሚገባ ገልጻለች። ይህም በመጪው ዘመንም በዓለም ዙሪያ ሚሊዮኖችን ሲቀሰቅስ ብሎም ጽናትና ጥንካሬን ሲያላብስ ይኖራል።💩
ሃና ፌዴራሊትሶል ኤንጅል
©Hassen M.