25/09/2025
የመደመር መንግስት መጽሐፍ ገቢው ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድርጎት የሚውል ነው::
የመደመር መንግስት መጽሀፍ ተቋማት ሰራተኞቻቸው እንዲገዙ እያደረጉ ነው የሚል ክስ እየተነሳ ነው። ይሄን መጽሐፍ የሚገዛ ማንኛውም ዜጋ ለበጎ አድራጎት የበኩሉን እንዳበረከተ ማሰብ አለብን። ታድያ ተቋማት ፍላጎት ያላችሁ አካላት ግዙ ቢሉ፣ ለምን አላችሁ ማለት ነውር እንጂ ፅድቅ አይደለም። በትብብር ተሸጦ ገቢው ከፍ ብሎ የበጎ አድራጎት ስራው በተጨባጭና በትልቅ አቅም ቢሰራ ማን ይጎዳል?
መፅሐፉን የመግዛት ፍላጎት ያላቸው ሰራተኛች በቀላሉ መግዛት እንዲችሉ በሁሉም የመንግስት ተቋማት ማቅረብ ተገቢ ነው። የመጽሐፍ ማንበብ ፍቅር የለለው ሰው እንኳን ቢገዛ ለበጎ ነገር ድጋፍ የማድረግ ባህላችንን ከፍ እናደርግበታለን።
የህዳሴ ግድብ ቦንድን በግድ የገዙ የነበር። የገባቸው በእርግጥ ከሚጠበቅባቸው በላይ በፍቃደኝነት ገዝተዋል። ህዳሴ ግድብ ስንት ፈተናን አልፈው ግንባታው ተጠናቅቀው ሲመረቅ ቦንዱን በግድ የገዛም፣ በፍላጎት የገዛም፣ ጭራሽ ያልገዛም እንዲሁን ግድቡን ሲቃወሙ የነበሩም ደስታቸውን ሲገልፁ ነበር።
ለበጎ አድራጎት መፅሃፉን ብንገዛ በረከቱ አይደርሰንም እንዴ? መፅሃፉን ዛሬ ገዝቶ ነገ የበጎ አድራጎቱ ሲፈፀም እኔም የድርሻው ተካፋይ ነኝ ብሎ ማሰብ የተሻለ ነው። እነ አጅሬ የበጎ አድራጎት ባህላችን እንዲጠፋና ዐቢይ ያሰበው እንዳይሳካ ለማድረግ ነው ለምን ይገዛሉ የሚሉት። እንገዛለን፣ እናነባለን፣ ባጎ አድራጎት ላይም እንሳተፋለን!