29/07/2025
አልበርት አንስታይን የካቲት 5 1930 ዓ.ም ላይ ለልጁ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከለት፦
“ህይወት ብስክሌት እንደመንዳት ናት ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ። የስኬት ሰው ብቻ ለመሆን አትሞክር ይልቅ ዋጋ ያለው ሰው ለመሆን ሞክር። ምክንያቱም ስኬት የሚለካው በምትወስደው ነገር ሲሆን ዋጋ የሚለካው ደግሞ በምትሰጠው ነገር ነው።
ሞኝ ማለት አንድ አይነት ነገርን ደጋግሞ ሰርቶ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነው። የተለየውን መንገድ ተከተል አዲስ ነገር ታገኛለህ። አትቀመጥ ምክንያቱም ምድራችን አደገኛ የሆነችው በክፉ ሰዎች ስራ ሳይሆን ምንም በማይሰሩ ሰዎች ውጤት ነው።
ትምህርት እውነትን አያስተምርም ይልቅ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበልጸጊያ ልምምድ ነው። የሌሎች ጫጫታ የአንተን የውስጥ ድምፅ እንዲውጠው ማድረግ የለብህም። ማንም ሰው ባንተ ላይ ገደቦች እንዲጥል አትፍቀድ፤ ገደብህ በራስህ ያወጣኸው የህይወት መመርያ መሆን አለበት!።”