Mizan News

Mizan News News

የመጀመሪያው የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ!!በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉባዔው በአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና የልማት አጀንዳዎ...
20/06/2022

የመጀመሪያው የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ!!

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉባዔው በአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና የልማት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል። ኮንፈረሱ የሚካሄደው ባሳለፍነው ወርኃ የካቲት ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግ ከሾመች በኋላ ሲሆን ጉባዔው የቀንዱ አገራት አንድነት እንዲጠናከር፣ ለረጅም ጊዜያት ግጭትና ብጥብጥ ባልተለየው ቀጣና ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ ቻይና ከአገራቱ ጋር በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎት ታላሚ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን በአጠቃላይ 8 አገራትን ያጠቃለለ የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና ነው። ቻይና በቀጣናው መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሲሆን አፍሪካን ከመካከለኛው ምስራቅ የሚያስተሳስረው የቤልትና ሮድ ፕሮጀክትም ግዙፉ ተጠቃሽ ነው። በጉባዔው የቀንዱ አገራት እና የቻይና መንግስት ልዑካን ታድመዋል።


t.me//hanisje

በህንድ እና ባንግላዲሽ በከባድ ዝናብና አውሎ ንፋስ በተከሰተ የመብረቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የ59 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተጎዱት ሰዎች...
20/06/2022

በህንድ እና ባንግላዲሽ በከባድ ዝናብና አውሎ ንፋስ በተከሰተ የመብረቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የ59 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተጎዱት ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል ተብሏል። የጎርፍ አደጋው በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሊባባስ እንደሚችል የአየር ንብረት ትንበያ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ይገኛል። የባንግላዲሽ መንግስት ባለስልጣናት የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ እ.ኤ.አ በ2004 በሀገሪቱ ከደረሰው አደጋ በኃሏ የከፋ ነው ሲሉ ገልፀውታል። ትምህርት ቤቶች ወደ ጊዜያዊ መጠለያነት የተቀየሩ ሲሆን ከውሃው መጨመር የተነሳ ከአጎራባች ነዋሪዎች ጋር የተቆራረጡ አባወራዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ወታደሮች ተሰማርተዋል።በህንድ አጎራባች አሳም ግዛት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ የተጎዱ ሲሆን በግዛቲቱ ለአምስት ቀናት ያለማቋረጥ ከፍተኛ ዝናብ ጥሏል።


t.me//hanisje

በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ኳስ ለማወጣት ወደ ወንዝ የገቡ ሁለት ታዳጊዎች ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አስር ...
20/06/2022

በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ኳስ ለማወጣት ወደ ወንዝ የገቡ ሁለት ታዳጊዎች ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አስር በተለምዶ ቀይ አፈር በሚባለእ አካባቢ አደጋው ከቀኑ 9ሰዓት ላይደርሷል። የዘጠኝ እና የአስራ አራት ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎቹ ኳስ እየተጫወቱ ሳለ ኳሱ ወደ ወንዝ ሲገባባቸው ለማውጣት በሚያርጉት ጥረት በውሃው ታፍነው መወሰዳቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። አንዱ ታዳጊ ወዲያው ህይወት ሲያልፍ ሁለተኛው ደግሞ ሆስፒታል ከገባ በኃላ ህይወቱ ማለፉን ተነግሯል፡፡ምክትል ኢንስፔክተር ማርቆስ የተያዘው የክረምት ወቅት በርካታ ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ መሆናቸውን እና የወንዞች ዳርቻ ጥንቃቄ ካልተደረገባቸው በርካታ ችግር ሊፈጥሩ እንሚችል በመግለፅ ወላጆች እና ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡

t.me//hanisje

የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ::በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና መተዳደሪ...
20/06/2022

የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ::

በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና መተዳደሪያን ማውደም ተቀባይነት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች፥ ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በሆነ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊትን መንግስት እንደማይታገስ አስታውቀዋል። ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደህንነትን መመለስ አሁንም ቅድሚያ የሚሰጠው ተግብር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

t.me//hanisje

20/06/2022

መግለጫ!

ኢሰመኮ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመዘዋወር ላይ የሚገኘውን እና በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ በማድረግ በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ሁኔታ መርምሯል።

በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየው ከሕግ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት ኢሰመኮ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ የአፋርና የአማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶችና የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ ምርመራ ሪፖርት” ላይ ከተዘረዘሩት ክስተቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ተረድቷል።

በዚሁ የኢሰመኮ የምርመራ ሪፖርት ከምስክሮች እና በስፍራው በመገኘት በመስክ ምልከታ ያሰባሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ፣ ድርጊቱ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ልዩ ቦታው እንቶሊ አካባቢ በታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት (ቀኑ በትክክል ያልታወቀ) መፈጸሙን፤ እንዲሁም በወቅቱ በነበረው መረጃ መሰረት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሁለት የጭነት መኪኖች ጭነው ያመጡዋቸውንና ወደ 30 የሚጠጉ የኦነግ ሸኔ አባሎች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች በጅምላ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን ይገልጻል።

ኢሰመኮ ተንቀሳቃሽ ምስሉን ከተመለከተ በኋላ ባደረገው ተጨማሪ ማጣራትና የቴክኒክ ምርመራ፣ በመስክ ምርመራ በለየው ስፍራና በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ያለውን ስፍራ በቴክኒክ ምርመራ በማነጻጸር፣ እንዲሁም ምስሉ የተቀረጸበትን ቦታ ለማነጻጸርና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቴክኒክ ምርመራዎችን በማድረግ፤ ከዚህ በላይ የተገለጸው በኢሰመኮ ምርመራ የተዘገበው ከፍርድ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት የሚያመለክት ተጨማሪ ማስረጃ ስለመሆኑ በምክንያታዊ አሳማኝነት አረጋግጧል

ስለሆነም ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሟላ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በድጋሚ ያሳስባል።

ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ።በትላንትናው ዕለት   ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያ...
20/06/2022

ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ።

በትላንትናው ዕለት ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ የሸሹ ስለመኖራቸውን ገልፀዋል። ከሟቾች መካከል ህፃናት እና ሴቶች እንደሚበዙ ፤ ቤቶች መንደዳቸውንም ፤ ጥቃቱ ሲፈፀም የነበረው በከባድ መሳሪያ ጭምር እንደነበር አመልክተዋል።

ለሚመለከተው የወረዳው አካል በሰዓቱ ጥቃት መኖሩን ጥቆማ ቢያደርሱም በቶሎ የደረሰ አካል እንዳልነበረ አስረድተዋል። የትላንቱን እጅግ አሳዛኝ ጥቃት ክልሉም አምኖ አረጋግጧል። ጥቃቱን ጭካኔ የተሞላበትም ነበር ብሏል። ክልሉ ባወጣው መግለጫ " የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ባደረሰው ጥቃት በንጹሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል" ብሏል። "ቡድኑ መንግሥት እየወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት አድርሷል" ሲል ገልጿል። በቡድኑ ላይ የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉም ብሏል። ክልሉ ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ እንዲሁም ታፍነው ስለተወሰዱ ሰዎች ምንም ያለው ነገር የለም።


t.me/hanisje

በመስቀል አደባባይ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ለማዘጋጀት እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር እንደሚያስከፍል የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ገልጿል። በአደባባዩ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ለማድረግ የኪራዩ...
18/06/2022

በመስቀል አደባባይ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ለማዘጋጀት እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር እንደሚያስከፍል የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ገልጿል።

በአደባባዩ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ለማድረግ የኪራዩ ዋጋ የተለያየ ነው የተባለ ሲሆን፤ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማድረግ ክፍያው እስከ 2 ሚሊዮን ብር መሆኑን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የገበያ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ታደሰ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ክፍያው ሁለት ሚሊዮን የሆነው ኮንሰርት ብዙ ወጪ ስለሚጠይቅ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው አክለው ተናግረዋል። ኮንሰርቶችን በተመለከተም ብዙ ሰዎች እየጠየቁና ፕሮግራም እየተያዘላቸው መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል።


t.me//hanisje

ፕሬዚዳንት ቪላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን አገራቸውን በኢኮኖሚ ማዕቀብ ጫና ውስጥ ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ሀገራቸው እንደምትቋቋመው ተናገሩ።ፕሬዚዳንቱ ትናንት በቅዱስ ፒተርስበርግ በተካሄደው...
18/06/2022

ፕሬዚዳንት ቪላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን አገራቸውን በኢኮኖሚ ማዕቀብ ጫና ውስጥ ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ሀገራቸው እንደምትቋቋመው ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት በቅዱስ ፒተርስበርግ በተካሄደው የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ “እኛ ጠንካሮች ነን እና ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን፤ ማንኛውንም ችግር እንፈታዋለን፤ የአገራችን የሺህ አመት ታሪክ ስለዚህ ጉዳይ ይናገራል” ነው ያሉት። በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ወደ ዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ ከማዘዛቸው በፊት ፑቲን ዩክሬን ወደ ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ እንደማትገባ ከአሜሪካ ዋስትና ጠይቀው እንደነበር አስታውሰዋል።

“በእኛ ላይ ዛቻዎች እየጨመሩ ከሚሄዳቸው የተነሳ ሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ተገዳለች ያሉት ፑቲን ውሳኔው ግን ከባድ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በትናንቱ መድረክ ላይ የሀገሪቱን “ግዙፍ አቅም” እውን ለማድረግ እና ምዕራባውያን የሩሲያን ኢኮኖሚ ለማዳከም የሚያደርጉትን ጥረት ለማክሸፍ የሩሲያ ኩባንያዎች የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያሳድጉ ማሳሰባቸውን FBC ዘግቧል።

t.me/hanisje

የመሶብ ታወር ፕሮጀክት በኹለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግበት ሁኔታ ይፋ ይደረጋል ተባለ!! የአዲስ አበባ ልዩ መገለጫ ይሆናል ተብሎ ከአምስት ዓመት በፊት የታቀደው የመሶብ ታወር ፕሮጀክ...
18/06/2022

የመሶብ ታወር ፕሮጀክት በኹለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግበት ሁኔታ ይፋ ይደረጋል ተባለ!!

የአዲስ አበባ ልዩ መገለጫ ይሆናል ተብሎ ከአምስት ዓመት በፊት የታቀደው የመሶብ ታወር ፕሮጀክት በመጪዎቹ ኹለት ወራት ውስጥ መቼ ወደ ተግባር እንደሚገባ ይፋ ይደረጋል ተባለ። የመሶብ ታወር ፕሮጀክት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ፀጋዬ ተክሉ፣ ከኹለት ዓመት በፊት ይጀመራል ተብሎ የነበረው የመሶብ ቅርፅ ያለው የአዲስ አበባ ልዩ መገለጫ መሶብ ታወር፣ በተለያዩ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች እንዲሁም ለሽርክና ሽያጭ ሰነድ በማዘጋጀት እስከ አሁን መጓተቱን ገልጸዋል። ሆኖም በሚቀጥሉት ኹለት ወራት ውስጥ መቼ ወደ ተግባር እንደሚገባ የምናሳውቅ ይሆናል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

t.me/hanisje

በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራውን የጀመረው አማራ ባንክ አ.ማ የከፈታቸው 72 ቅርንጫፎች ዝርዝር!   የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች1. አዲሱ ገባያ2. አድዋ ድልድይ3. አራት ኪሎ4. አያት አደባባይ5...
18/06/2022

በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራውን የጀመረው አማራ ባንክ አ.ማ የከፈታቸው 72 ቅርንጫፎች ዝርዝር!

የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች
1. አዲሱ ገባያ
2. አድዋ ድልድይ
3. አራት ኪሎ
4. አያት አደባባይ
5. በቅሎ ቤት
6. ቦሌ 24
7. ቦሌ ቡልቡላ
8. ቦሌ መድሃኒዓለም
9. ቦሌ ሚካኤል
10. ኮሜርስ
11. ዱባይ ተራ
12. እህል በረንዳ
13. ፈረንሳይ ለጋሲዮን
14. ጎጃም በረንዳ
15. ጎተራ
16. ሃና ማርያም
17. ጀሞ
18. ላፍቶ
19. ለም ሆቴል
20. ልደታ
21. ሳርቤት
22. ሸማ ተራ
23. ጦር ኃይሎች
24. ለገሀር (ዋና መስሪያ ቤት)

የባህርዳር ቅርንጫፎች
1. ባህርዳር
2. ደ/አዝማች በላይ ዘለቀ
3. ደንገል
4. ፋሲሎ
5. ግዮን
6. ሸምብጥ
7. ዘንባባ

የጎንደር ቅርንጫፎች
1.ጎንደር
2.አባ ሳሙኤል
3.አራዳ
4.ማራኪ
5.አፄ ፋሲለደስ

የደሴ ቅርንጫፎች
1.ደሴ
2.ጦሳ

የደብረታቦር ቅርንጫፎች
1.ደብረታቦር
2.ጉና

የደብማርቆስ ቅርንጫፎች
1.ደብረማርቆስ
2.መንቆረር

የሌሎች ከተሞች ቅርንጫፎች
1. ገንዳ ውሃ
2. ሸዋ ሮቢት
3. ሆሳህና
4. ቢሾፍቱ
5. ይርጋለም
6. ዳባት
7. ሀይቅ
8. ዳንግላ
9. ቢቸና
10. ዳንሻ
11. ወሊሶ
12. ደብረ ብርሃን
13. ፍኖተ ሰላም
14. አረርቲ
15. ኮምቦልቻ
16. ሐዋሳ
17. ሎጊያ
18. ከሚሴ
19. መካነሰላም
20. ሞጣ
21. ማክሰኝት
22. ደብረወርቅ
23. መራዊ
24. ደጀን
25. ሰቆጣ
26. ወልድያ
27. ወልቂጤ
28. ድሬዳዋ
29. አዳማ
30. እንጅባራ

የምንጋራው ወንድ አንቺ ጋር ለምን ቆየ በሚል ግድያ የፈፀመችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለችድርጊቱ በደቡበ ምዕራብ ኦሞ ዞን በማራሺማ ማምቹዋ እና አልማዝ ዳራቡቲ በተባሉ ግለሰቦች መካከል የተ...
17/06/2022

የምንጋራው ወንድ አንቺ ጋር ለምን ቆየ በሚል ግድያ የፈፀመችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

ድርጊቱ በደቡበ ምዕራብ ኦሞ ዞን በማራሺማ ማምቹዋ እና አልማዝ ዳራቡቲ በተባሉ ግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ሲሆን የሁለቱ የጋራ የትዳር አጋር ሆኖ የሚኖረው ግለሰብ አንዷ ጋር አንድ ሳምንት አንዷ ጋር አንድ ሳምንት እያሳለፈ የሚኖር ሲሆን ባላቸውን ሊጋሩ ተስማምተው ከውሳኔ ደርሰው ነበር፡፡ በመሀል ታዲያ የግል ተበዳይ ማራሺማ ማምቹዋ ጋር በመጀመሪ 15 ቀናት ያሳልፋል፡፡ከዛም አልፎ 21 ቀናት ይቀመጣል በዚህ ጊዜ አልማዝ ዳረቡቲ የተባለችው ግለሰብ እንዴት ይሄ ሁሉ ቀናት ከእኔ ውጪ ያሳልፋል በሚል ቂም በቀል አንገቷን በገጀራ ቆርጣ በመግደል በፍጥነት ከአካባቢው ትሰወራለች፡፡ በሰዓቱ የአካባቢው ሰው ድርጊቱን ተመልክተው ለፖሊስ በማሳወቃቸው ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዋ በህግ ቁጥጥር ስር ዉላለች። የክስ መዝገቧ ለፍትህ አካል እንደቀረበ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ገፅታ ግንባታ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
t.me//hanisje

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሀዋሳ ገቡ!!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሀዋሳ ገብተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ሲ...
17/06/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሀዋሳ ገቡ!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሀዋሳ ገብተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የባህል አባቶችና ወጣቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወቃል። በጉብኝታቸውም በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውን የዳቦና ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

!!

Address

Sudan Avenue
Ak'ak'i Besek'a

Telephone

+251945496289

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mizan News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share