
15/09/2025
🚨 አስደንጋጭ ዜና፡ የቻርሊ ኪርክ ግድያ ምርመራ 🚨
ብዙ ጊዜ ፍልስጤማውያንን ባልተገባ ቃላት ሲናገርና የእስራኤልን እርምጃ በመደገፍ የሚታወቀው እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ ቀኝ እጅ የሆነው የአሜሪካው ወግ አጥባቂ ተጽዕኖ ፈጣሪው አክቲቪስት ቻርሊ ኪርክ በሴፕቴምበር 10፣ 2025 በዩታ ሸለቆ ዩኒቨርሲቲ (Utah Valley University) በኦሬም፣ ዩታ (Orem, Utah) ውስጥ ንግግር ሲያደርግ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ አልፏል።
የግድያ ወንጀል ከተፈጸመበት ቦታ የተገኘው የዲኤንኤ ማስረጃ የ22 ዓመቱን ታይለር ሮቢንሰንን ከግድያው ጋር እንደሚያገናኘው ኤፍቢአይ (FBI) አረጋግጧል። መርማሪዎች አሻራውን መሳሪያ ላይ ተጠቅልሎ ከነበረ ፎጣ ላይ እንዲሁም ገዳይ ጥይት ከተተኮሰበት የህንጻ ጣሪያ ላይ ከተገኘ ዊንተር ሾፌር (screwdriver) ላይ ዲኤንኤ አግኝተዋል። በተጨማሪም ሮቢንሰን መኖሪያ ቤት ውስጥ ኪርክን ለመግደል ፍላጎቱን የሚገልጽ የተቀደደ ማስታወሻ ተገኝቷል።
ሮቢንሰን በዶናልድ ትራምፕ መንግስት ላይ የግራ ዘመም አክራሪ የፖለቲካ አመለካከቶችን እንደያዘ እና በመስመር ላይ ጽንፈኛ እንደሆነ ተዘግቧል። በኪርክ ላይ ያተኮረ እና በእሱ ላይም ርዕዮተ ዓለም ጥላቻን ሲገልጽ ነበር። ሮቢንሰን ከ33 ሰዓት ፍለጋ በኋላ ሴፕቴምበር 12 ቀን ተይዞ አሁን በዩታ ካውንቲ እስር ቤት (Utah County Jail) በልዩ ቁጥጥር ስር ይገኛል። በእሱ ላይ የሞት ፍርድ የሚያስከትል ግድያ ወንጀል ክስ እንደሚመሰረትበት ትራምፕ ጠይቀዋል፣ እና የመጀመሪያ የፍርድ ቤት ቀጠሮውም ለሴፕቴምበር 16፣ 2025 ተይዟል።
ምርመራው አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ምንጮች:
* AP News
* The Guardian
* Reuters